No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday 13 August 2012

የተሰሩት የአ.አ ሕንጻዎች ለአካል ጉዳተኞች ግልጋሎት ምቹ አይደሉም ተባለ Ethiopia News

(ዘ-ሐበሻ) የወያኔ ጀነራሎች፣ የጊዜው ባለስልጣናትና የባልስጣናት ዘመዶች የገነቧቸው ሕንጻዎች (ከወያኔ ጋር ያልተወዳጀ ሕንጻ አይደለም ራሱ ሃገር ውስጥ እንዲኖርለት አይፈቀድም) በአዲስ አበባ የገነቧቸው ግዙፍ ሕንጻዎች ምንም እንኳ በርከት ያሉ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተመዘበሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘቦች ቢፈሱባዎቸውም ህንጻዎቹ ግን የተገነቡት አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ባዳረገ መልኩ አለመገንባታቸውን የወያኔ ሚዲያዎች ራሱ አመኑ።
ራድዮ ፋና የተባለው የካድሬዎች የመፈልፈያ ራድዮ ዛሬ ባስተላለፈውና የአካል ጉዳተኞችን እያነጋገረ ባቀረበው ዘገባው በአዲስ አበባ ከሚገነቡ አብዛኛዎቹ ህንጻዎች ለአካል ጉዳተኞች የተመቸ መወጣጫ እንደሌላቸው ፥ የአሳንስሮችም ተሽከርካሪ ወንበር ፣ ዊልቸሮችን ማስተናገድ የማይችሉ ናቸው መሆናቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የህንጻ አዋጅና ደንብ በ2001 ዓ.ም ማንኛውም የሚገነባ ሕንጻ የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት ቢደነግግም ላወጡት ሕግ ቀርቶ ለራሳቸው የስነምግባር ሕግ የሌላቸው የወያኔ ባለስልጣናት ይህን ሕግ ጥሰዋል። መስሪያ ቤቱ ከአሁን በኋላ ለሚሰሩ ሕንጻዎች አስገድዳለሁ ቢልም እስካሁን ለተሰሩ ሕንጻዎች ግን
እርምጃ ለመውሰድ ድፍረት ስለሌለው ዝምታን መርጦ አልፏል።
ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ ውስጥ 17 በመቶ የሚሆኑት አካል ጉዳተኞች በሆኑባት ኢትዮጵያ ፥ 10 በመቶ የሚሆኑ ህንጻዎች ብቻ ለአካል ጉዳተኞች እንቅስቃሴ የተመቹ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲስ ኤብሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት ጥናት ያመለክታል።
አዲስ አበባ ውስጥ ካሉት ሕንጻዎች መካከል 90 ከመቶው የሚሆኑት የወያኔ ባልስልጣናት፣ የጦር ጀነራሎች፣ ከግዜው መንግስት ጋር አምቻ ጋብቻ ዝምድና ያላቸው፣ የዘመኑ ሰዎች ሕንጻዎች መሆናቸው ይታወሳል። ከነዚህም ውስጥ የተወሰኑት የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ ሃዜብ ሰርታ ለቴሌኮምዩኒኬሽን አከራይታ ገንዘብ የምትበላባቸው ሕንጻዎች ይጠቀሳሉ።

No comments:

Post a Comment