የተማረ ሆኖ ዕውቀቱን የማይገልጽ፣ታዋቂው ደራሲ ከበደ ሚካኤል ይህንን ብለውን አልፈዋል። ደራሲው ዕድሜ ለግሷቸው መምህሩም ለማስተማር ተማሪውም ለመማር አለመቻላቸውን ዛሬ ቢያዩ ምን ይሉ? በሃያ አንደኛው መቶ ዓመት ጉግ ማንጉጎች ተፈጥረው የዕውቀት ጮራ በሃገራችን ምድር እንዳይፈነጥቅ ጋርደዋት በጭለማ ውስጥ ትገኛለች።
ባለፀጋ ሆኖ ገንዘቡን የማይሰጥ፣
ደሃ ሆኖ መሥራት የማይሻ ልቡ፣
ሶስቱም ፍሬ ቢሶች፣
ለማንም አይረቡ።
‘እንዳያማህ ጥራው እንደይበላ ግፋው’ እንደሚባለው በአለፉት ሃያ ዓመታት ዩኒቭርሲቲዎች ተከፈቱ ቢባልም፤ የተማሪዎቹ ቁጥር ቢጨምርም፤ ተቋማቱ የመማርና የማስተማር ሥራ የሚካሄድባቸው ሥፍራዎች ሆነው አልተገኙም። የአካዳሚ ነፃነት በሌለበት በዕውቀት እድገት የለም። ተቋሞቹ የዕውቀት መገብያ ሳይሆኑ የካድሬ መፈልፈያ የስለላ ሥራ ማካሄጃ ናቸው። ይህም ሁኔታ በነፃነት መምህሩም ለማስተማር ተማሪውም ለመማር