የሃይማኖት አክራሪነት እና ልማታዊ እንቅስቃሴዎች በሚል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመንግስት ሃይሎች የተከናወነው ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው ።
በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ከሰኞ እስከ ረቡእ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በህክምናና ጤና ኮሌጅ ካምፓስ ሳይንስ አምባ አዳራሽ ውስጥ የተከናወነው አጠቃላይ የአክራሪነትን እና የልማታዊ እንቅስቃሴ ስብሰባን አስመልክቶ ስብሰባውን ይመሩት የነበሩት የወያኔ አባላት በሙሉ ተቃውሞ የገጠማቸው ሲሆን የስብሰባው ዋነኛ አቀንቃኝ እና የቀድሞው የትምህርት ሚንስትር ዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካዔል ባደረጉት ንግግር ከፍተኛ ተቃውሞ ሲገጥማቸው ፤በፕሮፌሰር ይግዛው ከበደ የተባሉት የዩኒቨርሲቲው መምህር ማለትም የቀድሞው ዩኒቨርሲቲው ፕረዚዳንት “ግንቦት ሃያ እና ግንቦት ሰባት እኩል ሊታዩ ይገባል” ሲሉ ገልጸዋል ።
![71-university-of-gondar-stadium](http://www.maledatimes.com/wp-content/uploads/2012/09/71-university-of-gondar-stadium-300x200.jpg) |
university-of-gondar-stadium |
በስብሰባው ወቅት በተነሳው አምባጓሮ የስልጣን ማን አለብኝነታቸውን ለማሳየት የሞከሩት ዶ/ር ስንታየሁ ወልደሚካዔል አይናቸውን ወደ መምህራኑ በማፍጠጥ የማስፈራሪያ ዛቻ እስከመስጠት ድረስ ደርሰዋል።በሌላም በኩል ከተሰብሳቢዎች በተነሱ ጥያቄዎች እና መልሶች በመነሳት መንግስት አሸባሪ የሚለዉን ተራ ቃል እየተጠቀመበት እሱ እራሱ ዜጎቹን እያሸበረ እንደሆነም ተናግረዋል ለምሳሌም ያህልም የእስቴ ህዝቦች ተትቅሰዋል።ፕሮፌሰር ይግዛው ከበደ ከስልጣናቸው ዝቅ እንዲደረጉ የተደረገበት ዋነኛ ምክንያት የወያኔ አባል ሁን በሚለው የወያኔ ካድሬዎች ግብዣ ባለመቀበላቸው ከቀድሞው የዩኒቨርሲቲው ማህበር እና ከአመራር አካልነታቸው እንዲነሱ አድርገዋቸዋል ። በዚህ