No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 17 November 2012

“ጥቁሩ ሰው” ይናገራል!


Obang Metho Solidarity Movement for New Ethiopia
“ጥቁሩ ሰው” ይሉታል። ኢትዮጵያዊያን ለሚያሽከረከራት አስፈሪ ፈተና መፍትሄው ሰብአዊነትን ማስቀደም ብቻ ነው የሚል የጸና እምነት አለው። “ከጎሳ በፊት ሰብዓዊነት” በሚል መሪ ዓላማ ከሚመስሉት ጋር በመሆን ድርጅት አቋቁሞ መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባከናወናቸው ሥራዎች ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰማው ያምናል። ኢትዮጵያዊያን ችግር ደርሶባቸዋል በሚባልበት ሁሉ ቀድሞ ደራሽ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። በዚህና በሰብዓዊ መብት ጉዳይ በሰራቸው ስራዎቹ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ደጋፊዎችና አድናቂዎች ለማፍራት ቢችልም “ከጀርባው ድብቅ ዓላማና አጀንዳ አለው፣ ብቻውን ይሮጣል” የሚሉትን ጨምሮ በግል አቋሞቹ ዙሪያ ነቀፌታ የሚሰነዝሩበትም አሉ።

Friday 16 November 2012

አጫጭር የሀገር ቤት ወሬዎች – ኢሣት ቴሌቪዥን እንዳይሠራጭ ታፈነ (ዘግይቶ የደረሰ አስደሳች ዜና፡- ኢሣት ሠራ!)

ኢሣት ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ እንዳይሠራጭ ታፈነ
Ethiopian Satellite Television, ESAT TVከአንድ ዓመት ተኩል ስኬታማ አፈና በኋላ የተጣለበትን ተደጋጋሚ የአየር ሞገድ እመቃ ተቋቁሞ ላለፉት ጥቂት ሣምንታት በኢትዮጵያ ሥርጭቱን ጀምሮ የነበረው የኢሣት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ከትናንት በስቲያ ኅዳር 4 ቀን 2005ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ዝነኛ ሥርጭቱ መቋረጡ ታወቀ፡፡ ባለፉት የሥርጭት ጊዜያት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የብሶት መተንፈሻና የታፈኑ የሀገር ቤት ዜናዎች ማወጃ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወቅ ነው፡፡
ሰሞኑን ግን ኢቢኤስ የሚባለው ወያኔ-ዘመም የቴሌቪዥን ጣቢያ ከአረብሣት ወጥቶ ወደናይልሣት መግባቱን ተከትሎ የሁለቱም ሞገድ የሚተላለፍባቸው 10815 የማሰራጫ ፍሪኩየንሲ መዘጋቱ ተረጋግጧል፡፡ ይህን የማፈን ድርጊት የፈጸሙትም የወያኔው መንግሥትና የቻይና የቴክሎጂ ጠበብት እንደሆኑ ኢንሣ (INSA) ከሚባለው ከሥራ አመራር እስከጽዳትና ዘበኛ ድረስ የተመረጡ የትግሬ የጉልበትና የኢንተሊጀንስ ባለሙያዎች ብቻ ከሚሠሩበት የወያኔው መንግሥት የፀረ ድረገፅ ሚዲያ ተቋም በፌስታል ተጠቅልሎ እንዳልባሌ ከወጣ ዕቃ መረዳት ተችሏል፡፡ አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት የኢቢኤስ ወደናይልሣት መግባት ከኢሣት መታፈን ጋር የቀረበ ግንኙነት አለው ተብሏል፡፡

Thursday 15 November 2012

ESAT Daliy News-Amsterdam Nov 15 2012 Ethiopia


ከአዲስ አበባ ውጪ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ መኢአድ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ

ህዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከአዲስ አበባ ውጪ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በኢህአዴግ ካድሬዎችና በመንግሥት ባለሥልጣናት ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ፡፡
የክልል ምክር ቤቶችና የወረዳዎች የምርጫ እንቅስቃሴ በመጀመሩ የኢህአዴግ ካድሬዎች እንደተለመደው አውሬ ባህሪያቸው ጎልቶ ወጥቷል ያሉት የመኢአድ የአሶሳ የአመራር አባል የመንግሥት ደህነቶች የተቃዋሚ ፓርቲ በተለይም የመኢአድ ፓርቲ አባላትንና ደጋፊዎችን እየለቀሙ መሬታችሁን ለቃችሁ ውጡ በማለት እያስፈራሩን ነው ብለዋል

አምባሳደር ተወልደ ዓጋመ ከፓርቲው ለቀቁ (እየሩሳሌም አርአያ)


የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ (በቅጽል ስማቸው ተወልደ ዓጋመ) በገዛ ፈቃዳቸው ከፓርቲው እንደለቀቁ ምንጮች አረጋገጡ። ባለፈው በተካሔደው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርበው ከማ/ኰሚቴ አባልነት እራሳቸውን እንዳገለሉ አስታውቀዋል። በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ተወልደ «አጋሜ» ከ 1993ዓ.ም በሑዋላ ተዛውረው በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ያለሙያቸው ተመድበው ቆይተዋል።
በተጨማሪ ባለቤታቸው ሮማን ገ/ስላሴ በፓርቲው ሊ/መንበር « አይኖዋን ማየት አልፈልግም» ተብለው ከፓርቲው ርቀው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰዋል። የሕወሃት አንጋፋ ሴት ታጋይ የነበሩት ሮማን የተሓድሶ «አቀንቃኝ» ሆነው ወደ መድረክ በመውጣታቸው በትግራይ የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ተደርገው በመለስ ከመሾማቸው ባሻገር በፓርቲው ማ/ኰሚቴ አባልነት መካተታቸውን ጠቁመዋል።

Wednesday 14 November 2012

ኢህአዴግ በፖለቲካ ወለምታ ውስጥ !!


November 14, 2012 08:59 am By EditorLeave a Comment

ኢህአዴግ በ“ፖለቲካ ወለምታ” ውስጥ እንደሚገኝ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የኢህአዴግ ዲፕሎማት ለጎልጉል
ተናገሩ። በከፊል ኢህአዴግን የተለዩ የሚስሉት ዲፕሎማት በጎልጉል የቅርብ ሰው አማካይነት ድምጻቸው ሳይቀረጽ ባደረጉት
ቃለ ምልልስ እንዳሉት የተፈጠረው የፖለቲካ ወለምታ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አመልክተዋል። የኢህአዴግ ከፍተኛ
ባለስልጣናት በመካከለኛ አመራሩ ውስጥ የመጠራጠር ስሜት መፈጠሩን በፓርቲ ግምገማ ላይ በግልጽ መናገራቸው
የዲፕሎማቱን አስተያየት የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል።

ESAT Daliy News-Amsterdam Nov 14 2012 Ethiopia


Espionage on Ethiopians in Noway has TPLF backing

‹‹ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ››

እስክንድር ነጋ
‹‹ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ››ከነገ በስቲያ (ማክሰኞ ህዳር አራት) በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት የእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ይሰየማል፡፡ በትላንትናው ዕለት የክስ ቻርጅና መንግስት እወርሳቸዋለሁ ያላቸውን የእስክንድር ሁለት ቤቶች ካርታ የተያያዙበት መጥሪያ ደርሶታል፡፡ (በነገራችን ላይ መንግስት ሊወስዳቸው ከተዘጋጁት ቤቶች አንዱ በእናቱ ስም ያለ ሲሆን የዛሬ ዓመት አካባቢ ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የቤቱን ስም ለማዞር ፈልጋ ‹‹ካርታው የለም›› በሚል አንዴ ቀበሌ፣ ሌላ ጊዜ ክፍለ ከተማ፣ ቀጥሎ አዲስ አበባ መስተዳደር ስትመላለስ ከርማ ሊገኝ ስላልቻለ ሰልችቷት ትታው ነበር፡፡

Tuesday 13 November 2012

Ethiopia: Mainstreaming Jungle Economics on the expenses of the poor


by Teshome Debalke

Congratulation African tyrants, finally a new economic disciplineWhen some of the world Media and institutions take the Ethiopian ruling regime’s propaganda at face value to claim the country is one of the fastest growing economies, it makes you pause to say a new discipline in economics designed particularly to legitimize corruption as real must be invented.
Congratulation African tyrants, finally a new economic discipline that would cover up your notoriously corrupt rule to show growth and development is invented. If reshuffling numbers of foreign aid, Diaspora remittance and selling off national resources to foreign inventors for cheap are considered growth and development we are in the new era of modern day dictatorship.  Unlike the previous era where dictators claim to protect the poor masses from the

Monday 12 November 2012

በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል

ይኸነው አንተሁነኝ
11-11-2012

በደል ይረሳል ወይስ ይለመዳል ወገን? ጉልበተኛው ወያኔ በጉልበቱ ተማምኖ በማን አለብኝነት እና በማን አህሎኝነት የምንኖርበትን ቦታና ፍላጎታችንን ሳይቀር ወስኖ በንቀት ረግጦ መግዛቱ ሳያንሰው፤ ህገመንግስታዊ መብታችን ይከበር፣ መንግስት ራሱ ላወጣው ህግ ይገዛ፣ መብታችንን ተጠቅመን የሰጠነው የምርጫ ድምጻችን ይከበር ብለው ጥያቄያቸውን ለማሰማት የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞችን እድሜ ዘመናቸውን ወስኖ፤ እንደፈለገ የሚያዛቸውን የአጋዚ ሰራዊት በመጠቀም በጠራራ ፀሐይ በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች አውራ መንገዶች ላይ ያለርህራሄ ግንባር ደረታቸውን እየቀደደ እንደ ውሻ ሬሳ እንደ አልባሌ ያጣለበት ወርሃ ትቅምት እንሆ ሰባትኛ የሃዘን ዓመት ባተ።

Sunday 11 November 2012

US concerned about worsening Muslim rights in Ethiopia By United States Commission on International Religious Freedom November 10, 2012

High-ranking TPLF official flees to Canada


Nov. 9 (ESAT News) The Director of the Federal Civil Service Agency has reportedly sought asylum in Canada. The longtime TPLF loyalist Atakliti Hagos reportedly left Ethiopia for good with his family, which is seen as a sign of frustration and division within the ruling elite after the death of former Prime Minister Meles Zenawi.
ESAT learnt that Atakliti has been absent from work for over two months but reportedly arrived in Canada a over month ago.
ESAT effort to get a statement in relation to the director’s defection from the Federal Civil Service Agency did not bear any fruits.

ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ


አማራ፣ ደቡብና ኦሮሚያ እንቅልፍ ውስጥ ናቸው

effort2
“የሙስና መርከብ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አሉ። ከተቋቋመ ጀምሮ አንድም ቀን ስለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተገልጾ አያውቅም። ከአገሪቱ ባንኮች ትልቁ ተበዳሪ ነው።የወጋጋን ባንክ ትልቁ ባለድርሻ ነው። በአንዳንድ ከፍተኛ የንግድ ተቋማት ውስጥ የንግድ ሽርክና እንዳለው ይታማል። የወርቅ ማዕድን ፍለጋው ሰምሮለታል። የግል አስመጪዎችን በመፈታተን አነካክቶ ጥሏቸዋል። አገሪቱ ላይ የገነባው የንግድ ኢምፓየር በበርካቶች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ የተቋቋሙትን የንግድ ተቋማት በመደፍጠጥ በፖለቲካው የበላይነቱ ሳቢያ ልዩ ተጠቃሚ በመሆኑ አይወደድም። ይህ ታላቅ የህወሃት የንግድ ግዛት ኤፈርት ነው።

“በአገራችን ባይተዋር ከመሆን በላይ ውርደት የለም” የስምንት ዓመቷ ታዳጊ ጥሪ አቀረበች!!

norway



ይህንን ዘገባ ሳሰናዳ በ1997 ምርጫ ወቅት አዲሱ ገበያ አካባቢ አልሞ ተኳሾች የገደሉባቸውን ልጃቸውን ስም እየጠሩ “ምን
አደረካቸው? ምን አጠፋህ? አንተኮ ትንሽ ነህ? ማንን ልጠይቅ? ማንን ላናግር? ልጄ … የኔ ባለተስፋ፣ እኔ ልደፋ፣ እኔ መንገድ ላይ ልዘረር፣ ምነው ለኔ ባደረገው? የማን ያለህ ይባላል…” የሚሉ ልብን ዘልቆ የሚገባ ሃረግ እየደጋገሙ እብደት የተቀላቀለው ለቅሶ አልቅሰው ያስለቀሱን እናት ታወሱኝ፤ ብዙዎች በተመሳሳይ አንብተዋል።ደረታቸውን ደቅተዋል። አሁን ድረስ የልጅ፣ የአባት፣ የወንድም፣

በጅጅጋ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል


ህዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች፣ ሰራተኞችና ጎብኝዎች እንደገለጹት በኢትዮጵያ የሶማሊ ክልል ዋና ከተማ በሆነው ጅጅጋም ሆነ ከጅጅጋ ከተማ ራቅ ባሉ ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተወላጅ የኦጋዴንና የሌሎችም ጎሳዎች አባላት እንዲሁም በክልሉ ውስጥ በሚኖሩ የሌሎች አካባቢዎች ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ነው።
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የመንግስት ሰራተኛ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በመሄድ በአካባቢው ይሰሩ የነበሩ ሰዎች ሶማሊኛ አትችሉም ተብለው ከስራ ተባረዋል።
እንዲሁም በቀበሌ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ከ400 እስከ 1500 ብር የሚደርስ  ኪራይ እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ምሬታቸውን እየገለጹ ነው።
የክልሉ መንግስት ልዩ ሚሊሺያ በማለት የሚጠራው፣  የፌደራሉ መንግስት ይወቀው አይወቀው የማይታወቅ፣  ታጣቂ ሀይል በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ያለተቆጣጠሪ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እየፈጸመ ነው።
ከመሀል አገር ወደ ጅጅጋ ለስራ የሄደ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ሰራተኛ  በአካባቢው የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ከተመለከተ በሁዋላ ለኢሳት እንደገለጸው ጅጅጋ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ አካል ናት ብሎ ለመናገር አያስደፍርም ብሎአል።
የክልሉ ልዩ ሚሊሻዎች በተወሰኑ ብሄር ተወላጆች ላይ አነጣጥረው ጥቃት እንደሚፈጽሙም ታዛቢው ይናገራል
ከአቶ መለስ ዜናዊ እረፍት በሁዋላ በክልሉ የሚታየው ግፍ እየጨመረ መምጣቱን ታዛቢው ገልጿል
ልዩ ሀይል እየተባለ የሚጠራው ታጣቂ ሀይል ከክልሉ አልፎ በአፋር ተወላጆች ላይ እስከ ሞት የሚደርስ ጥቃቶችን እየፈጸሙ እንደነበር በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አብዲ ሙሀመድ ኦማር፣ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ከእንግዲህ  ከማንም ትእዛዝ አልቀበልም በማለት ክልሉን ራዝ ገዝ አደርጋለሁ እያሉ ሲናገሩ እንደነበር የቅርብ ታማኝ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ የክልሉን መንግስት አቋም ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።