No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday 2 November 2012

Mr Obang Metho held a meething in Oslo

Mr Obang Metho is the dirctor of the Solidarity Movement for the new ethiopia

Tuesday 30 October 2012

የኢትዮጵያዋ፡ ርእዮት ‹‹የጥንካሬዬ ዋጋ››ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ስለስልጣን ብልግና አለያም ስለ ስልጣንን በማንአለብኘነት አለ አግባብ ስለ ከመጠቀም ከመናገር ይበልጥ አስቸጋሪ የሆኑ bezu ነገሮች yelum፡፡ ለ31 ዓመቷ ወጣት ኢትዮጵያዊት አይበገሬ ርዕዮት ዓለሙ ግን፤ የመጻፍ ነጻነት፤ የመናገር ነጻነት፤ ሃሳብን በነጻ የማንሸራሸር ነጻነትን ድምጻቸው በመሳርያና በስለላ መዋቅር ለታፈነባቸው ድምጽ ከመሆን ምንም አይነት ጋሬጣ ቢደረደር ሊያደናቅፋት ጨርሶ አይችልም፡፡ አሁንም ቢሆን ባለችበት ክፉ ሁኔታም ሆና ስለግፍ ስልጣን ቁልጭ ያለ ሃቅን ትናገራለች፤ ‹‹ለጥንካሬዬ ዋጋ እንደምከፍል ብገነዘብም የሚቃጣብኝን ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ››፡በማለት ካለችበት ገሃነማዊ የቃሊቲ ጉረኖ ባመለጠው የእጅ ጽሁፏ መልእክቷን ለአለም አስተላልፋለች፡፡

“ጥንካሬ ለሁሉም ድርጊት ታላቅ ዋጋ አለው፡፡ ጥንካሬ ከሌለ ማንኛውንም አይነት ዋጋ ያለው ተግባር ማከናወንም ሆነ ማቀድ አይቻልም” ያለችው ታላቋ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጸሃፊ ማያ አንጀሉ ናት፡፡ ባለፈው ሳምንት የዓለም

Monday 29 October 2012

መስማት የተሳነው፡ ስብሃት ነጋ፡( ከማተቤ መለሰ ተሰማ)

መስማት የተሳነው፡ ስብሃት ነጋ፡
  ከማተቤ መለሰ ተሰማ
በአጼ ምኒልክ ዘመን፡ አንድ ኢትዮጵያዊ፡ በድንገት መስማት ይሳነዋል አሉ፡ ሰውየው እድሜ ጠግቦ እስከሚሞት፡ የምኒልክ፣ የእያሱ፣ የዘውዲቱ ንግስና አልፎ፡ ከሀይለ ስላሴ የግዛት ዘመን አጋማሽ ድረስ ቆይቶ ነበርና፡ ጆሮው መስማት ከማቆሙ በፊት የነበረው ሁሉ እንዳለ፡ የቀጠለ መስሎት፡ በምኒልክ አምላክ እንዳለ ነው የሞተው ይባላል። በአጠቃላይ ስነምግባሩ፡ ሲታይ ከሰው ተወልዶ ከእንስሳት ጋር እንዳደገ፡ በግልጽ የሚመሰክርበት፡ ስብሃት ነጋም፡ እንዳይሰማ ጆሮው የደነቆረው፣ እንዳያነብ አይኑ የታወረው፡ ደደቢት ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም። ምክናያቱም ዛሪ ሕዋሃት የማስመሰያ ካባውን አጥልቆ፡ ኢትዮጵያዊ ለመባል እየጣረ ባለበት ወቅት ስብሃት ከ21 አመት በሗላ የሚናገረው ሁሉ፡ በምኒልክ ሲል እንዳለፈው ሰው ደደቢት በነበረበት ጊዜ ሲሰበክ የነበረውን፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ማዋረድንና አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ማጥላላት፣ ስለአከተመለት ስርአት ሰለደርግ ማውራትን ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ፡ በአሁኑ ወቅት ሰውየውን በጥሞና ለሚከታተለው ሰው፡ ዘመናት ጥለውት ከንፈው እሱ አንድ ቦታላይ ቆሞ ለብቻው እየቆዘመ እንዳለ ለመገንዘብ አያዳግተውም።
ለነገሩማ እርጅናም፡ በአንዳንድ ሰዎች ላይ የህሌና ሚዛንን ማዛባቱ ባይቀርም፡ ስብሃትን ግን ከእድሜው በላይ ያደነቆርው፡ ቀን ሲያኝከው የሚውለው ጫት፣ ማታ ተዘፍዝፎበት የሚያድረው አረቄ ነውና፡ እነዚህ ሁለት አድገኛ የሰው ልጅ የአካልም የአእምሮም ጠንቅ የሆኑና አቅልን የሚያስቱ ነገሮች፡ ማየትና መስማቱን ብቻ አይደለም፡ ህይወቱንም አለመንጠቃቸው የሚያስገርም ነው።
ውድ አንባብያን፡ በዚህ ጽሁፊ ስብሃት ነጋን አንተ እያልሁ የምገለጸው፡ የክብርን ዋጋ ለማያውቅና፡ በ90 ሚሊዮን የሚገመተውን ጭዋና አስተዋዩን የኢትዮጵያን ህዝብ በጠቅላላ ለሚዘልፍ ሰድ አክብሮት መስጠት፡ እራስን እንደማዋረድ ስለምቆጥረው መሆኑ ይታወቅልኝ። ለምን የሚል ካለ መልሴ፡ ሌላውን ትቸ 19/10/2012 የጀርመን ሶሻሊስት ፓርቲ ባዘጋጀው፡ የአፍሪካ የውይይት መድረክ ሰብሰባ ላይ ተገኝቶ በነበረበት ወቀት ከተናገረው 2ቱን ለአብነት ብጠቅስ በቂ ይመስለኛል። ስብሃት ነጋ ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ መጻሂ እድልና የፓለቲካ ምህዳር እንዲያብራራ ለቀረበለት ጥያቄ፡ በተለመደውና ስነምግባር ባልገራው አንደበቱ የሰጠው ከጥያቄው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መልስ፡ 1ኛ/ ስነስራት የሌለውን የኢትዮጵያን ህዝብ ስራት ለማስተማርና፡ የደርግ እርዝራዦችን፡ ለመቆጣጠር በዙ ጊዜ አሳልፈናል። 2ኛ/ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሴ ብቁ አይደለም የሚል ነበር። ማን ይሆን፣
አውቃለሁ መራር ነው መራብ መጠማት፣
ቁስሉ አይጸናም እንጅ ደግሞ እንደ ውርደት
ያለው? እንዲህ ተዋረደ፡ ደጉ፣ እሩህሩሁ፣ ጭዋው፣ አትንኩኝ ባዩ፡ የኢትዮጵያ ህዝብ፡ ይገርማል፡ አርቆ በማሰቡ፣ በመታገሱ፣ ከወያኔና ጋጠወጥ መሪዎቹ፡ የተመለሰለት ይህ ነው። ለመሆኑ ስብሃት ነጋ ማነውና ነው የኢትዮጵያን ህዝብ ስራት የሚያስተምረው? እሱስ ስራት ለማስተማረ ቀድሞ ነገር ስራት አለው ወይ? ይህን ያህል በእብሪት የተወጠረበትስ ምክናያት ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳት የግድ ከሚልበት ደረጃ ላይ የደረስን ይመስለኛል። ከኤርትራዊ እናቱና ከአድዋው አባቱ የተወለደው፡ የዛሪው ስብሃት የትናንቱ ወልደ ስላሴ ነጋ፡ ወደትግል ከመግባቱ በፊት የሚያከብረውና የሚያፈቅረው፡ ከአባቱ ይልቅ እናቱን እንደነበርና፡ አሁንም ሆነ በትግሉ ወቅት፡ ከምር የሰራውና እየስራ ያለው ከኢትዮጵያ የልቅ ለኤርትራ እንደነበርና እንደሆነ በብዙ ማስረጃዎች እያስደገፉ ምስክርነታቸውን ሲሰጡ የኖሩ በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች እነዳሉ አስታውሳለሁ።
ስብሃት ወይንም ወልደ ስላሴ፡ ለኢትዮጵያውያን የነበረውን ጥላቻ፡ በገቢር ማሳየት የጀመረውም፡ ሜዳ በነበረበት ጊዜ፡ ወደትግሉ የሚቀላቀሉ ሴት እህቶቻችንን አስገድዶ እየደፈረ፡ ሲያረግዙ እንዳያጋልጡት በመግደልም እንደነበር ብዙ ቀራቢው የነበሩ ሰዎች ተናግረውታል፡ ቀጥሎ ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በሗላም፡ ከመለስ ዜናዊ በስተጀርባ ሆኖ ለ21 አመታት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ ለተፈጸመው መለኪያ መስፈርት፡ መግለጫ ቃላት፡ ለማይገኝለት ግፍ፡ ቀላል ሚና አልነበረም፡፡ ሌባ ሲካፈል እንጅ፣ ሲሰርቅ አይጣላም፡ እንደሚባለው ሁሉ፣በቅርብ፡ ከአዜብ መስፍን ጋር፡ በጥቅም መጋጨት እስከጀመሩ ጊዜ ድረስ፡ መለስ ያለስብሃት ይሁንታ፡ የሰራውና የሚሰራው እንዳልነበር የታወቀ ነው።የዛሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ስራት የለውም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሴ ብቁ አይደለም ወ. የሚለው ዘለፋው፡ የመነጨውም፡ከዚያ ከቆየው የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ጥላቻው ነው።
ያረጀ የልማድ ፈረስ ጋላቢውና፡ በክፋት፣ በቅናትና በምቀኝነት፡ ለተበከለ፣ በመንፈስም የታወረ፣ በአልኮል መጠጥ ብቻም ሳይሆን፡ በእርኩስ ምኞትም የሰከረ፡ አእምሮ ባለቤት የሆነው፣ እንዲሁም ከክዕደት ጋር ጡት የተጣባው፡ ስብሃት ነጋ፡ የበቀል ጥሙን ለማርካት የነደፈው መረሃግብር ተሳክቶለት፡ ኢትዮጵያ በጥፋት፣ ህዝቧ በፍርሀት እንዲዋጡ፣ ምድሯም ሲቃይ ተዘርቶ መከራ የሚበቅልባት፣ ምሪትና ዋይታ የሚታጨድባት፣ ሞት፣ በሽታ፣ እራብና እርዛት፣ በገፍ የሚመረትባት፣ የሰው ልጅ ስብናው፡ እየበሰበሰ፣ ማንነቱ ሰርዶ እየለበሰ ያለባት፡ ምድራዊ ጋነብ እንድተሆን፡ ካደረጓት ሰዎች ግንባር ቀደሙ ለመሆን በቅቷል።
ያንን ሁሉ በደል ሲፈጽም፡ ዝም በመባሉም ነው፡ እንደዚህ ለከት የለሽ፡ አፉን ለመክፈት የበቃው፡ እኛስ መቸይሆን ትግስታችን የሚያበቃው? መቸ ይሆን ውርደቱ የሚያመን? መቸይሆን በሌሎች ኪሳራ አትራፊ ለመሆን የፓለቲካ ሂሳብ መስራታችንን፡ አቁመን የተነጠቅነውን ማንንታችነን፡ ለማስመለስ የህይወት መሷዕትነት መክፈልን፡ ምርጫችን የምናደርገው? መቸይሆን እንደዚህ እየተዋረዱ፡ ቆሞ ሲሞቱ ከመኖር ይልቅ፡ ሞትን በሞት ሽሮ ማለፍ ሃያው እነት ነው፡ የሚለውን ብሂል ስራላይ የምናውለው? ውድ አንባብያን እስኪ ለአፍታ ቆም በማለት ውስጣችነን እንፈትሽ፡ እኔም፣ አንተም ሆንህ፣ አንች፡ ከስብሃት ነጋ የምናንስበት ምን ነገር አለ?????
ጥቅምት ወር 2012
source www.maledatimes.com/

ESAT Daliy News-Amsterdam Oct. 29 2012 Ethiopia


Ethiopia charges 29 Muslims under anti-terror law

Ethiopia charges 29 Muslims under anti-terror lawADDIS ABABA (AFP) — Twenty-nine Ethiopian Muslims were charged Monday with plotting acts of “terrorism”, the majority arrested after protests accusing the government of interference in religious affairs.
According to court documents, the group is accused of “intending to advance a political, religious or ideological cause” by force and the “planning, preparation, conspiracy, incitement and attempt of terrorist acts.”
The 29 accused — including nine prominent Muslim leaders — were jailed following protests in July staged by Muslims against the government.

የ“አዲሱ መንግስት” ተግዳሮት እና የአቶ ኃይለማሪያም አጣብቂኝ

ዘሪሁን ተስፋዬ
(የቀድሞ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረባ)

አዲስ ታይምስ

mስከረም 2፤ 2005 ዓ.ም ሎንዶን። ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ የተወከሉ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል ከሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች፣ ጋዜጠኞች እና የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተወካይ ግለሰቦች ጋር ለውይይት ተቀምጠዋል። ወቅቱ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ማን ይተካ ይኾን የሚለው ጉዳይ የሚብሰለሰልበት ነበር። በርግጥ ለእንግሊዝ ተወካዮች የሚያብሰለስል ጉዳይ አልነበረም፤ ምስጢራቸውን በልባቸው ሸሽገው ከባለሞያዎቹ ተጨማሪ ሃሳቦችን ይሰበስባሉ። ሁሉም ባለድርሻ የሚመስለውን እና ጥናቱ ያመላከተውን ሐሳብ ሰነዘረ። ተንታኞችን በሚያስማማ መልኩ የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተተኪነት አነጋጋሪ አልነበረም። በጠቅላይ ሚኒስትር ተተኪ ማንነት ላይ ላይ ጥርጣሬ የነበረው ማንም አልነበረም። የድሕረ መለስ የፖለቲካ ኹኔታ እንዲሁ ትኩረት ያገኘ ነበር።

Sunday 28 October 2012

“ቃሊቲ”ን በጨረፍታ – በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ክፍል ሁለት)

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
. . . እድሜዋ በግምት ወደ 50 የሚጠጋ፤ በክንዷ ላይ የአስር አለቃ ማዕረግ የለጠፈች (ሳጅን) በጥያቄ ታጣድፈኝ ጀመር፤ ለነገሩ በጥፊ ከመጣደፍ በጥያቄ መጣደፍ በብዙ የተሻለ ነው ብዬ ስለገመትኩ ያለቅሬታ ነበር የጠየቀችኝን ሁሉ የመለስኩላት፡፡ “ስምህ ማነው?” የተረከብሽበት ወረቀት ላይ አለልሽ ልላት አሰብኩና ተውኩት፡፡ በምትኩ ሙሉ ስሜን ነገርኳት፡፡
“ብሔርህ ምንድን ነው?” “እግዜር ይይልህ ኢህአዴግ!” በሆዴ ያልኩት ነው፡፡ በአፌ ግን እንደምንም ቀጣጥዬ እና ሰፋፍቼ ብሄሬን ተናገርኩ፡፡ መቼም በብሶት ተወልዶ ለበርካታ ብሶቶች መወለድ መንስኤ የሆነው ኢህአዴግ በእግዜር ፊት ለፍርድ ቢቀርብ (በሰው ፊት እንኳ ይቀርባል ብሎ ማሰቡ አዳጋች ነው) ከሚከሰስባቸው ክሶች መሀከል ዋነኛው ሀገሬውን በአያት ቅድማያቱ (አያት ቅድማያቱን የማያውቀውን ደግሞ በሩቅ ዘመዱ) በመከፋፈሉ ይመስለኛል፡፡ አማራ፤ ኦሮማ፤ ትግሬ፤ ጉራጌ፤ ሲዳማ፤ ወላይታ፤ ሐረሪ፤ አፋር . . .
የሆነው ሆኖ የሳጅን ጥያቄ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምን አስታወሰኝ፡፡ “ፕሮፍ” ከሚጠሉት ጥያቄ ሁሉ “በሔርዎት ምንድን ነው?” የሚል እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ዛሬም ድረስ የሚጠቀሙበት የቀበሌ መታወቂያ “ብሔር” የሚለው ቦታ ላይ “ኢትዮጵያዊ”

መንግስት 2 የእስልምና ተቋማትን ጨምሮ 8 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ዘጋ

ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የየበጎ አድራጎት ማህበራት ምዘገባ ኤጀንሲ የእስልምና ጥናት ምርምር ማእከልንና የአወልያ ትምህርት ቤትን የምዝገባ ፈቃዳቸውን በመሰረዝ እንዲዘጉ ውሳኔ አስተላልፎአል።

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ “የእስልምና ጥናት ምርምር እና አወልያ ትምህርት ቤት ፣ የበጎ አድራጎት ስራ እንዲሰሩ ፈቃድ የተሰጣቸው ቢሆንም ፣ ከዚህ ሀላፊነታቸው ውጭ በመሄድ በሀይማኖት ጉዳይ ላይ ስራ ሲሰሩ በመገኘታቸው ተዘግተዋል” በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።