ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የየበጎ አድራጎት ማህበራት ምዘገባ ኤጀንሲ የእስልምና ጥናት ምርምር ማእከልንና የአወልያ ትምህርት ቤትን የምዝገባ ፈቃዳቸውን በመሰረዝ እንዲዘጉ ውሳኔ አስተላልፎአል።
የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ “የእስልምና ጥናት ምርምር እና አወልያ ትምህርት ቤት ፣ የበጎ አድራጎት ስራ እንዲሰሩ ፈቃድ የተሰጣቸው ቢሆንም ፣ ከዚህ ሀላፊነታቸው ውጭ በመሄድ በሀይማኖት ጉዳይ ላይ ስራ ሲሰሩ በመገኘታቸው ተዘግተዋል” በማለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን አወልያ በነጻነት በቦርድ እንዲደራጅና የመንግስት ጣልቃገብነት እንዲቆም በመጠየቅ ላለፉት 11 ወራት ያደረጉትን ትግል በአወልያ መጀመራቸው ይታወሳል።
ሌሎቹ የተዘጉት 8 የበጎ አድርጎት ድርጅቶች በገንዘብ አያያዝ በኩል ጉድለት በማሳየታቸው መሆኑ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ መንግስት የመንግስትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በመንቀፍ መረጃዎችን ለውጭ አገር መንግስታትና የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ያቀብላሉ በማለት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤና በኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።
ሂውማን ራይትስንና አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ በርካታ አለማቀፍ ድርጅቶች መንግስት ያወጣውን አዲሱን የሲቪክ ማህበራት ህግ ሲቃወሙ መቆየታቸው ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment