No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.
Saturday, 29 June 2013
ከ 110 በላይ ኢትዮጵያዊ ባህር ላይ ቀሩ
ስለ ስደተኛው የቁራሌው ጩኸት እስከ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ….
በግሩም ተ/ሀይማኖት
…ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ተቃዋሚ ሀይሎች ከጅቡቲ ወስደው መጠቀሚያ ሊያደርጓቸው ነበር፡፡ ብዙ እናውቀለን…›› ይህን በስደት ዙሪያ የአዞ እንባ ያነባው ኢቲቪ ለውይይት ከጋበዛቸው ውስጥ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ያዳለጣቸው ነው፡፡ ያዳለጣቸው ያልኩት መንግስት ያን ሁሉ ማስመሰያ ያደረገበት ምክንያት ምን እንደሆነ አባሳደሩ በግልጽ ሳያውቁ ስላስቀመጡት ነው፡፡ የስደተኛው ህይወት አሳዝኗቸው አይደለም፡፡ ተቃዋሚዎች ይዘው ሊጠቀሙባቸው ስለሚፈልጉ ወይም ስለሞከሩ ነገ ስልጣናቸውን ላለማጣት ነው፡፡ ያ-ካልሆነማ ስንት አመት በሙሉ በስደት ወገን ረገፈ ሲባል…ሲጮህ ዝም በዝምታ ብለው በስደተኛው የጣር ድምጽ ባላላገጡ ነበር፡፡ ግን የፈሩት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የትጥቅ ትግል ሊያደርጉ መሰናዶ ላይ ስለሆኑ ከሆነ አንድ ሰሞን አራግበው ዝም ማለት ጦሱ እንደሚብስ ለምን ልብ አላሉትም? የወጣውስ በአግባቡ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ካልተደረገ ወዴት እንደሚያቀና እንዴት አላገናዘቡም? ይገርማል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ እየተሰቃየ ያለው ህዝብ ወዴት እያመራ
Friday, 28 June 2013
ይድረስ ለኢትዮጵያው ሥውር መንግሥት ይነጋል በላቸው
ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ኢትዮጵያን ማን እየገዛ እንደሆነ ከግምት ያለፈ ዕውቀት የለኝም፡፡ በመለስ ጊዜም ቢሆን ሀገሪቱ በዕውር ድንብርና በነሲብ ነበር የ…የሚገርም አጋጣሚ ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና በዚያ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ኃላፊዎች ጸሎት በቶሎ እንዲድኑ ሲጸልዩላቸው የሀገሪቱ የሃይማኖት ታዋቂ አባትና ተከታይ ምዕመኖቻቸው ግን በሰላም እንዲያርፉ ነው ጸሎት እየተደረገ ያለው – ለኔልሰን ማንዴላ፡፡ ይህ ነገር የሥልጣኔ ልዩነት ይሁን የባህል አልገባኝም፡፡ ይህን የዜና ሽፋን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በሚሰራጭ አንድ የተቃውሞው ጎራ ቴሌቪዥን አማካይነት እየተከታተልኩ ነኝ – ልክ አሁን፡፡ በመሠረቱ ከ94 ዓመታት ምድራዊ የሥጋ ለባሽ ሕይወት በኋላ አንድ ብዙ የሕይወት ውጣ ውረድ ያሳለፈና በእሥርም ብዙ የተሰቃዬ ሰው ዕድሜ እንዲረዝም መመኘት ከፍቅር ብዛት የሚመነጭ የዋህነት ይመስለኛል፡፡ በጀመርኩት ሃሳብ ትንሽ ልቆይና ወረድ ብዬ በዚህ ላይ እንደመጠቅለያነት እመለስበታለሁ፡፡
በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው ከኢየሩሳሌም አርአያ
በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
Thursday, 27 June 2013
“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”
“ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”
“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል” ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ? ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር አሰሩኝ ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር ዝዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
Tuesday, 25 June 2013
ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ (ፕ/ሮ መስፍን ወ/ማርያም)
በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት አስተሳሰብ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰው ዓላማ ለአውሮፓ ቄሣራውያን ዋና ግባቸው ሆኖ እስከሃያኛው ምዕተ-ዓመት ዘልቆአል፤ አሀን ፈጽሞ በተለየ ዘመን አሜሪካ ይህንን አስተሳሰብ ይዞ የተነሣ ይመስላል።
ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ ዓባይን ይቆጣጠራል፤ ዓባይን የተቆጣጠረ ግብጽን ይቆጣጠራል፤ ግብጽን የተቆጣጠረ ኃይል ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር ይቆጣጠራል፤ ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር የተቆጣጠረ ኃይል ዓለምን ይቆጣጠራል።
ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ ዓባይን ይቆጣጠራል፤ ዓባይን የተቆጣጠረ ግብጽን ይቆጣጠራል፤ ግብጽን የተቆጣጠረ ኃይል ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር ይቆጣጠራል፤ ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር የተቆጣጠረ ኃይል ዓለምን ይቆጣጠራል።
አሜሪካ በግብጽ ላይ የተከለው ጥፍሩ ሲነቃነቅ መነቀሉ አለመቅረቱን ስላወቀው ሌላ የሚተክልበት አገር ይፈልጋል፤ በአካባቢው የግብጽን ነፍስ የሚነካ ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም፤ ለአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ዓላማ ኢትዮጵያ ስትመረጥ የአሁኑ የመጀመሪያው አይደለም፤ በመሀከለኛው ምሥራቅ የአረቦችን የተባበረ ኃይል ለመቋቋም የተመረጡ ሦስት አረብ ያልሆኑ አገሮች — ቱርክ፣ ኢትዮጵያና ፋርስ (ኢራን) — ነበሩ፤ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የአሜሪካ ዓለም-አቀፍ ኃይል
The Heat is on! Ethiopians no longer allowing Woyane to play on the bottom of the pits by Teshome Debalke
June 23, 2013
Clash of Civilization between those that stand for Democracy and universal suffrage and others that submit for tyranny is reaching the tipping point. What remained for the rest of spectators is to take side. On one hand, there are those that declared tyranny must be dismantled as it should by all means necessary to replace it with the people government. On the other hand, there are those that accepted ethnic tyranny as their savior signing their death wish. The choice is clearer than ever. The difference is, the former have everything to live for to see the dawn of freedom playing on the higher ground while the later have no life worth living; except to preserve tyranny one more day… by all means necessary playing on the bottom of the pits.
Fortunately, everybody must take side. As they saying go, ‘life is a bitch’ but, we have to live it. Those that attack the messenger instead of challenging the message are on the bottom of the pits. No sane Ethiopian would play at the bottom with tyranny unless…
The US Congressional hearing this week on The Future of Democracy and Human Right in Ethiopia is another millstone; exposing further the self-declared ethnic minority tyranny in Ethiopia has no creditability or redemption value. The hearing, not only exposed Woyane’s atrocities and corruption but the complicity of the US Administrations that supported and armed it in the name of fighting terrorism; leaving the defenders of ethnic tyranny striped necked.
Fortunately, everybody must take side. As they saying go, ‘life is a bitch’ but, we have to live it. Those that attack the messenger instead of challenging the message are on the bottom of the pits. No sane Ethiopian would play at the bottom with tyranny unless…
I choose side, have you?
The fall out from the hearing and the subsequent bill that will be introduced shortly will open the
Sunday, 23 June 2013
Subscribe to:
Posts (Atom)