በነባር አመራሮች ሲንከባለል የኖረው “የቅንጅት ወራሽ” አንድነት
ፓርቲ ኃላፊነቱንና አመራሩን ለተተኪ ሳያስረክብ መቆየቱ በአብዛኛው ትችት ሲያሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በተለይም
አቶ ስየ አብርሃ ፓርቲውን በተቀላቀሉ ማግስት በከፍተኛ ኃላፊነት መሰየማቸው አልተወደደለትም ነበር፡፡ በአንድነት
ፓርቲ ውስጥም እስከመከፋፈል የዘለቀ ልዩነት መፍጠሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
አሁን የረገበ የሚመስለው የፓርቲው የውስጥ ልዩነት፤ በወቅቱ
“ዝም አንልም፤ መርህ ይከበር” የሚሉት ኃይሎች የወሰዷቸውን ጽንፈኛ አቋሞች ብዙዎች የሚደግፉት ባይሆኑም ያነሱትን
ጥያቄ አግባብነት ግን ይቀበላሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊመንበር የነበሩት
ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም “እኛ የማማከር አገልግሎት መስጠት አለብን፤ አመራሩን መያዝ ያለበት አዲሱ ትውልድ ነው”
በማለት ራሳቸውን በቅሬታ ከፓርቲው ማግለላቸው ይታወሳል፡፡