No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday, 1 December 2012

የአዜብ-በረከት የተንኮል እቅድ (ከጋሻ ለኢትዮጵያውያን)


መለስ ዜናዊ የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም ከተጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱና ዋናው “የትግራይ ህዝብ የሥርዓቱ ልዩ
ተጠቃሚ”እንደሆነ አድረገው በካድሬዎቻችው በኩል ያለመሰልቸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ማካሄድ ነበር። ይህ ዘዴ የትግራይ ህዝብ
ተጠቃሚ፤ የኢትዮጲያ ህዝብ ግን የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲሰማው አድርጎታል። አቶ መለስ “ነፃ ሚድያ” ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻል ሁኔታ ስላጠፉትና የኢትዮጵያ ህዝብም የሳቸው የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ስላደረጉት እሳቸው የሚናገሩት እና የሚያወሩት እውነት ይሁን ውሸት ለማወቅ ይቸገራል። ያ ውሸት ተደጋግሞ ሲነገረው ውሸቱን እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል። አቶ መለስ ኢኮኖሚህ 11 በመቶ አድጓል እያሉ ነጋ ጠባ ሲወተውቱት፣ ከአመት ወደ አመት ኑሮው እየከፋ፣ ጉልበቱ በረሀብ እየደከመ የሄደው ወገን ውሸቱን እውነት አድርጎ ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭ የለCም።

Friday, 30 November 2012

ESAT Daliy News-Amsterdam Nov. 30 2012 Ethiopia


የእስላም ኢትዮጵያውያን የትግል ስልት ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በአለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ እስላም ኢትዮጵያውያን ማካሄድ የጀመሩት ትግል በዓይነቱም፣ በስፋቱም፣ በአስተሳሰቡም፣ በስሜቱም እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ከአገዛዙ ጋር ከተደረጉ ትግሎች በጣም የተለየ ነው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትግሉ ለሃይማኖት ነጻነት ነው፤ ስለዚህም በአገዛዙ በኩል የፖሊቲካ ዓላማና የፖሊቲካ መልክ እየተሰጠው ሲሆን በእስልምና ምእመኖቹ በኩል ግን ትግሉን ከፖሊቲካ የጸዳ ለማድረግ ግሩም የሆነና የተሳካ ጥረት እያደረጉ ነው፤ ሁለተኛ የትግሉ ስልት ፍጹም ሰላማዊ በመሆኑ የአገዛዙን የጉልበት ስልት እያከሸፈ ያጋለጠው ይመስላል፤ አንዱና ዋነኛው የትግሉ ሰላማዊነት መግለጫ በቤተ መስጊድ መወሰኑ ነው፤ ይህ ስልት አዲስ አይደለም፤ በብዙ የአረብ አገሮች የሚጠቀሙበት ነው።

Thursday, 29 November 2012

ህወሃት አረጋግቶ አገገመ ብቸኛው ተቃዋሚ የንግድ ሚኒስትሩን ሹመት ኮነኑ



Assigned EPRDFist

ኢህአዴግ “አረጋግቶ አገገመ” ከተባለው አዲሱ “ምደባ” መካከል የንግድ ሚኒስትር  ተብለው በተሰየሙት ላይ ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ጠንካራ መከራከሪያ በማቅረብ ተቃወሙ። አቶ ግርማ የሚሾሙ ብቻ ሳይሆን የሚነሱ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም ለህዝብ መቅረብ እንዳለበት አሳሰቡ። አቶ ሃይለማርያም ተቃውሞውን “መክረንና ገምግመን ያደረግነው ነው” ሲሉ ተከላከሉ። አቶ ግርማ ብሩ (አሁን አምባሳደር) ሲመሩት የነበረውን ሚኒስቴር መ/ቤት “ስያሜና ምልክት መለየት የማይችል” በማለት አንቋሸሹት።

አይ.ኤል.ኦ ኢትዮጵያን ለሠራተኞች መብቶች “ክፉ” ሃገር ሲል ፈረጀ



የአይኤልኦ የመደራጀት ነፃነት ኮሚቴው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ፖል ፋን ደር ሃይደን
ከእነዚህ ዋና ዋና እና ቁልፍ ከሚባሉ ስምምነቶች መካከል በማኅበር የመደራጀት ነፃነት ስምምነት፣ ለመደራጀት መብት የሚሰጥ ጥበቃ ስምምነት፣ የወል ድርድር መብት ስምምነት የሚጠቀሱ ሲሆን ኢትዮጵያም እነዚህንና ሌሎቹንም ስምምነቶች ተቀብላ ፈርማቸዋለች፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ስምምነቶቹን የማክበር ግዴታ እንደሚጠበቅባት የአይኤልኦ የመደራጀት ነፃነት ኮሚቴው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ፖል ፋን ደር ሃይደን ገልፀዋል፡፡የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የሥራ ድርጅት – አይኤልኦ ኢትዮጵያን የሠራተኞችን መብቶች በማክበር በኩል የከፋች ሃገር ናት ሲል

ESAT Daliy News-Amsterdam Nov. 29 2012 Ethiopia


EPRDF GTP Plan includes the election of three Deputy Prime Ministers?



Reading the lips of Hailemariam Desalegn
Ethiopian ruling junta showed progress in the 5 year GTP plan by electing 3 Deputy prime minister. We don’t have any constitutional provision that allow the parliament to elect three deputies prime minister though the ruling junta doesn’t respect their own constitution. There is only one Deputy Prime minister as stipulated under the constitution. The constitution states “the deputy Prime Minister… not the Deputy Prime ministers… ”.
Read Article 75 the Deputy Prime Minister:

A man got beaten up for handing out flyers for Zenawi memorial

Meles and the Deconstruction of EthiopiaAn Ethiopian-American man handing out flyers for a memorial service for Ethiopia’s recently deceased prime minister, Meles Zenawi, claims he was assaulted by a countryman who reviled the repressive leader, according to criminal and civil court documents.
The victim and plaintiff, Tesfai Tsadik, is suing both Wossenu Gizaw, the alleged assailant, and Debre Salam Medahnealem Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, the Fondren Southwest house of worship near which the alleged assault took place.

Wednesday, 28 November 2012

አጫጭር የሀገር ቤት ወሬዎች (ከአዲስ አባባ) ቁጥር 2


ይነጋል በላቸው

ከአዲስ አባባ
Addis Ababa is the capital city of Ethiopia.ባለፈው የዜና ዕወጃችን ይህን መሰል የሀገር ውስጥ አጫጭር ወሬዎች ዘገባ ቢያንስ በሣምንት አንድ ጊዜ እናቀርባለን ብለን ቃል ባልገባነው መሠረት ከመጀመሪያው የቀጠለውን የዛሬውን ዝግጅት ቀጥለን የምናቀርበው በታላቅ  የደስታ ስሜት ነው፡፡ እነዚህ ወሬዎች በምናባዊ የአቀራረብ ፋሽን በመዋዛታቸው የአንዳንዶችን አመኔታ በቀላሉ ላያገኙ እንደሚችሉ ቢጠረጠርም ሀሰት እንዳልሆኑ ግን ለተከታታዮቻችን በዚህ አጋጣሚ ልናስታውስ እንወዳለን፡፡ የዜና ማዕከሉ ውሸትን በመዘገብ የሚያገኘው ቅንጣት ትርፍ አለመኖሩን በሚገባ ስለሚገነዘብ ጥቂቶቹን የሥነ ጽሑፍ አላባውያንና ነገር ማስዋቢያ ግብኣቶችን(literary flavors) ከመጠቀም ውጪ ያልተሰማና ያልተደረገ ወይም ከነአካቴው ‹ይህን ዓይነቱ ነገር ሊደረግ አይችልም!› ተብሎ የሚገመትን ክስተት በዜና ፋይል ውስጥ እንደማያካትት በትህትና ያስታውቃል፡፡ ሃሳብን በተፈለገው መንገድ ማቅረብ ይቻላል፤

Monday, 26 November 2012

ESAT Daliy News-Amsterdam Nov 26 2012 Ethiopia


የሱዛን ራይስ ሸፍጥ በቤንጋዚው ጥቃት ላይ! ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

በሴፕቴምበር 2 2012 የአሜሪካዋ አምባሳደር በተባበሩት መንግስታት: ሱዛን ራይስ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ስርአት ላይ ስሜታዊ ሆና የሚያቅለሸልሽ ቃላት ያዘለ ንግግር አነብንባ ነበር፡፡ መለስን፤ ‹‹የማይደክምና ራሱን የማይወድ››በአጠቃላይ እሱነቱ ለስራውና ለቤተሰቡ የሆነ ብላዋለች፡፡ ‹‹ጠንካራ፤ በእምነቱ የጸና እና በእርግጥም ለጂሎችና ለደደቦች እሱ እንደሚጠራቸው ትእግስቱ ትንሽ ነበር፡፡ ሱዛን ራይስ ይህን ቅጥ ያጣና ከአንድ አሜሪካን ከሚያህል ሃገር ወኪል ጨርሶ ሊሰማ የማይገባ ያልተገራ ንግግር ስታደርግ ጅልና ደደብ የሚለውን ቃል በድፍረትና በአጥንኦት የለጠፈችው በኢትዮጵያዊያን ነጻ ጋዜጠኞች፤የተቃዋሚ መሪዎች፤ተሟጋቾች፤የፖለቲካ እስረኞች፤የሲቪል ማሕበረ ሰብ መሪዎች፤እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ነው፡፡ የንግግሯን ቪዲዮ በመመልከት ሴትዮዋ ይህን ንግግር የመለስን ተቃዋሚዎች በመጨረሻ ጡጫ ደረታቸዉን ብላ ለመለስ የአስከሬን መሸኛ አድርጋ ማቅረቧ እንደነበር ያስታውቃል፡፡

የ‹ትግላችን› አሣር ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ከደቂቃዎች በፊት የኤሊያስ ወንድሙን የኢሣት ቃለ ምልልስ እየተከታተልኩ ነበር፡፡ ያን ቃለ መጠይቅ እንዳገባደድኩ ኤልያስ የሚመራው የፀሐይ አሣታሚ ድርጅት እስካሁን ካሣተማቸው 60 ያህል መጻሕፍት ለየትኞቹ ይበልጥ ክብደት እንደሚሰጥ ሲጠየቅ ከጠቆማቸው ሥራዎች መካከል በሁለተኛነት የጠቀሰው የቀድሞውን መሪ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያምን(ባሉበት ሰላምታዬ ይድረሳቸው) ‹ትግላችን› የሚል መጽሐፍ ነበርና ጀማምሬው ሳበቃ ሁሉንም ሳላነብ ዴስክቶፕ ላይ ያኖርኩት ይሄው መጽሐፍ ትዝ አለኝ፡፡ ከጅምሩ እንደገና ላነበው ፈቀድኩናም ወደንባብ ክፍል አመራሁ፡፡ ግን እውነት ልናገርና ሸከከኝ፤ ዱሮውንም ሸክኮኝ ነበር ሳልጨርስ የተውኩት፡፡ እናገራለሁ፡፡

የወቅቱ የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታና የወደፊት የትግል አቅጣጫ – በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር

መግቢያ

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

Sunday, 25 November 2012

ለመሆኑ አባ ገብርኤል ስንት ምላስ አላቸው? ዘመነ ካሳ ፍራንክፈርት ጀርመን


በቀደመ ስማቸው ኢያሱ ተፈሪ ተብለው ይጠሩ የነበሩት አባ ገብርኤል በቀድሞው ፓትርያርክ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፈቃድ አባ ገብርኤል በመባል የዽዽስና ማእረግ
 ተቀበሉ ከዚያም በተለያዩ የኢትዮዽያ አሕጉረ ስብከቶች በሊቀ ጳጳስነት አገልግለዋል በተለይም የቀደመችው የኢትዮጵያ አካል የነበረችው የኤርትራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ ከተዋሕዶ ትምህርት የወጣ የምስጢረ ሥላሴን ትምሕርት የሚያፋለስ መጽሐፍ በመጻፋቸው ምክንያት ተወግዘውና ተሽረው በቀደመው አለማዊ ሥማቸው አቶ ኢያሱ ተፈሪ ተብለው በቅዱስ ሲኖዶስ ተለይተው እንደነበር ታሪክ መዝግቦት የተቀመጠ መሆኑ የታወቀ ጉዳይ ነው
አባ ገብርኤል በአቋማቸው ወላዋይነት በተናገሩበት የማይጸኑእንደ ገበታ ውኃ የሚዋልሉ ይህን ብየ ነበር ብለው ይሉታና ትዝብት የሌላቸው እና ጠንካራ ነው ብሎ