No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday, 13 January 2014

የህወሓት መፈክር፡ ‘የአማራ የበላይነት ይውደም!’ By Abraha Desta.


ግርማይ ገብሩ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የአሁን የቪኦኤ (VOA) ዘጋቢና ደራሲ ነው። ዓላማዬ ስለ ግርማይ ገብሩ ለመፃፍ አይደለም፤ ግርማይ በፌስቡክ ገፁ ስላሰፈረው መረጃ ለመዋስ እንጂ። መረጃው ከዚህ በፊትም አውቀው ነበር። ግን ለማስረጃ ያህል ግርማይን ልጥቀስ: ምክንያቱም ግርማይ የህወሓት ታጋይ ነበርና።

ግርማይ በ1969 ዓም የህወሓት (ተሓህት) ሦስቱ መፈክሮች ሲጠቅስ የመጀመርያውና ዋነኛው አድርጎ የፃፈው “አፄነት፣ መስፍንነትና የአማራ የበላይነት ይወድማሉ” ይላል።
በትግርኛ “ካብ ጭርሖታት ህወሓት 1969 ዓም: ሃፀይነት፣ መስፍንነትን ናይ አምሓራ ዕብለላን ዓነውቲ እዮም!” ይላል። ግርማይ ገብሩ አልተሳሳተም። ከህወሓቶች ጋር የማልስማማበት ግን ነጥብ አለኝ።

እኔና አፄ ምኒሊክ By Abraha Desta


ቆይ ግን እኔ የምኒሊክ 'አድናቂ' ነኝ እንዴ? ባጋጣሚ ስለ አፄ ምኒሊክ ጥሩም መጥፎም ፅፌ አላውቅም። ግን ብዙ የህወሓት ደጋፊዎች የምኒሊክ አገዛዝ እንደምደግፍ አድርገው ለህዝብ ይነግራሉ። የፌስቡክ ጓደኛዬ ዳንኤል ብርሃነም "የምኒሊክ ቲፈዞነትህ ለማስቀጠል ከፈለክ የሱ ወራሾች የሆኑ 'አንድነቶች' (ፓርቲው መሆኑ ነው) አሉልህ፤ ከነሱ ጋር ተቀላቀል" የሚል መልእክት ያለው አስተያየት ሰጠኝ።
...
የህወሓት ደጋፊዎች ከምኒሊክ ጋር የሚያገናኙኝ ምናልባት ህወሓት ስለምቃወም ይሆን? ወይስ እንደነሱ 'ሸዋ አማራ ጠላታችን ነው' ብዬ አለመፃፌን ነው? ህወሓትን መቃወም ከምኒሊክ አገዛዝ ጋር ምን ያገናኘዋል? ግን'ኮ ህወሓቶች በስልጣን ለመቆየት የሚጠቀሙት ስትራተጂ 'ከፋፍለህ ግዛ' ነው። 'እኛና እነሱ' ብለው ይከፋፍላሉ። በዚህ መሰረት 'ህወሓት ከተቃወምክ የሸዋ ፖለቲከኞች ትደግፋለህ ማለት ነው' ይሉሃል። ቆይ የሸዋ ፖለቲከኞች ሳንደግፍ ህወሓትን መቃወም አንችልም ማለት ነው?