No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 4 May 2013

ኢህአዴግ በኖርዌይ ገንዘብ ማሰባሰብ ተሳነው

በስደት አገራቸውን ለቀው የወጡ ሰዎች ያለመሰለል መብት አላቸው። በህግም የተደነገገ ነው። ከለላ የሰጣቸውም አገር ይህንን የመከላከልና የመቃወም ግዳጅም አለበት። ከለላ ያገኙ ስደተኞችም ሆኑ ከለላ እንዲሰጣቸው ያመለከቱ ወገኖች ስለመሰለላቸው ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ ህጉን ጠቅሰው የመከራከር መብት አለቸው። ለመብታቸው ሲከራከሩ በመደራጀት ቢሆን ይበልጥ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አውሮፓ በስደት ያሉ ቀድሞ የውጪ ጉዳይ የዲያስፖራ ኢንጌጅመንት ዳይሬክቶሬት ዲፓርትመንት ኤክስፐርት ይናገራሉ።

ከፖለቲካ ፍጥጫው በስተጀርባ ( ከኢየሩሳሌም አርአያ )

በገዢው ሰፈር ጎራ ለይቶ ከተለኮሰው የቡድን ፖለቲካዊ ፍጥጫ እና ሴራ ጀርባ አገር እና ህዝብን የሚጎዳ አደገኛ ተግባር በግልጽ እና በስውር እየተካሄደ እንዳለ ከተለያዩ የፓርቲው ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ።
በተለይ በብአዴን እና በህወሃት ቱባ አመራሮች መካከል ስር ሰዶ የቆየው እና የአቶ መለስን ህልፈት ተከትሎ ያገረሸው የውስጥ ሽኩቻ ሁለት ቡድኖች የሃይል አሰላለፋቸውን ለማጠናከር «ይረዱናል » የሚሏቸውን የሌሎች ፓርቲ ሹማምንት እና የመከላከያ የጦር አዛዦች ከጎን የማሰለፉን ተግባር ቀጥለውበታል።ለግንዛቤ እንዲረዳ የሃይል አሰላለፉን በጥቂቱ በመዳሰስ ወደ ዋናው ነጥብ እናምራ ።

አሁንም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በአፋጣኝ እንዲፈቱ እንጠይቃለን! (አንድነት)

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
Unity for Democracy and Justice (UDJ) partyፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በሰላማዊና ህጋዊ የትግል መንገድ ለውጥ ማምጣት ይቻላላል፤ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንፈጥራለን፤ ስልጣንም በግለሰቦች ወይም በቡድኖች ይሁንታ የሚገኝ ሳይሆን በህዝቡ በልካም ፈቃድ ይሆናል የሚል ጠንካራ እምነት በመያዝ ከአምባገነኑ ስርዓት ጋር እየታገለ የሚገኝ ነው፡፡
ይሄ ጠንካራ የትግል መነሳሳታችን እና ያለን  የህዝብ ድጋፍ ጠንካራ ተቃዋሚ በዓይኑ ማየት የማይፈልገው ገዥ ፓርቲ ጥርስ ውስጥ የከተተን በምስረታችን ማግስት ጀምሮ ነው፡፡ በርካታ አባሎቻችንንና አመራሮቻችንን ተልካሻ ምክንያት እየተለጠፈባቸው ታስረዋል፣ ተሳድደዋል፣ ተደብደበዋል፡፡
በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ ጠንካራ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችና ተቃውሞዎች ሁሉ የሚሰጣቸው ስም ሽብርተኝነት የሚል ነው፡፡ የስርዓቱ የስልጣን ማቆያ፣ የሀቀኛ ተቀናቃኞችና ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞች ማሸማቀቂያ ብሎም ማስወገጃ መሳሪያ ሽብርተኝነት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡
ፓርቲያችን አንድነትም ጠኋትና ማታ እየተጠቀሰ ዜጎች እንዲሸማቀቁ የሚደረግበትና የፖለቲካ አመራሮች የሚታሰሩበት

Thursday 2 May 2013

Breaking News: TPLF sentenced Eskinder Nega and Andualem Arage

ADDIS ABABA (AFP) — An Ethiopian court on Thursday dismissed the appeal of blogger Eskinder Nega and opposition leader Andualem Arage who were jailed last year for terror-related offences.
“The sentencing is still correct so there is no reduction,” said Supreme Court judge Dagne Melaku, confirming Eskinder’s jail term of 18 years and Andualem’s life sentence.
One of the charges — serving as a leader of a terrorist organisation — was dropped, but had no affect on sentencing.



After the ruling, Eskinder made an emotional appeal to the court which was crowded with family, friends and diplomats.
“The truth will set us free,” he said. “We want the Ethiopian public to know that the truth will reveal itself, it’s only a matter of time.”
Both men are accused of links to the outlawed opposition group Ginbot 7.
“The walls of justice will be demolished,” Andualem told AFP.

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በነ አንዷለም አራጌ፣እስክንድር ነጋ በፍርድ ቤት ውሳኔ ስቅስቅ ብለው አነቡ !

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አነቡ !
በኢትዮጵያ እንባ እንግዳ ነገር ባለመሆኑ የዶክተሩን ማልቀስ ምን የተለየ ያደርገዋል የሚለኝ አይጠፋም፡፡ነጋሶ በጀርመን አገር የሞቀ ኑሮና የሚያስመካ መተዳደሪያ ነበራቸው፡፡ኢህአዴግ ይዟቸው ከመጣ በኋላም ወደ ቤተመንግስት አስገብቶ በፕሬዘዳንትነት ሰይሟቸዋል፡፡ህገ መንግስቱ ሲረቅም ነጋሶ ከአርቃቂዎቹ አንዱ ነበሩ፡፡እነዚህ ነገሮች ዶክተሩን በአጀብ ለማኖር ከበቂ በላይ ነበሩ፡፡ነገር ግን አንድ ማለዳ ነጋሶ መለስን‹‹መንግስቱ ኃይለማርያምን መሰልከኝ ››በማለት መናገራቸው እንደ ሃጢአት ተቆጥሮባቸው የቤተመንግስት ቆይታቸው ተቀጨ፡፡ከስንብቱ በኋላ የተቆረጠላቸውን ጡረታ እየተቀበሉ አንደበታቸውን በመሸበብ መኖር እንደሚችሉ የሚገባቸው ቢሆንም ነጋሶ በግላቸው ተወዳድረው የህዝብ ድምጽ ማግኘት በመቻላቸው ፓርላማ ገቡ፡፡በዚህ ያልተደሰተው ኢህአዴግ ጡረታቸውን በመንጠቅ የሰጣቸውን የመኖሪያ ቤት ነሳቸው፡፡ምንም ያጡት ነጋሶ ኦነግን ወይም አንዱን የብሄር ድርጅት ይቀላቀላሉ ተብለው ሲጠበቁ ህብረ ብሄራዊ የሆነውን አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲን ተቀላቀሉ፡፡

ማርስ ላይ መኖር ይፈልጋሉ?

ማርስዋን (Mars One) የተባለ የሆላንድ ኩባንያ እ.ኤ.አ በ2023 እንዲካሄድ ላቀደው ወደ ፕላኔት ማርስ ጉዞ የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞችን መመዝገብ እንደሚጀምር ዛሬ ይፋ አደረገ። ጉዞው ለየት የሚያደርገው ሰዎቹ ወደ ምድር ተመልሰው የማይመጡ ሲሆን እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ ማርስ ላይ ለመኖር ተስማምተው ጉዞውን ይጀምራሉ።
የመንኮራኩር ጉዞዎችን እጅግ ውድ ከሚያደርጋቸው ነገሮች አንዱ ደርሶ መልስ ጉዞ ሲሆን ይህኛው ግን የመመለሻ ጉዞ ስለሌለው ዋጋው አነስተኛ የሆነ እና በዛ ያሉ ሰዎች ሊከፍሉት የሚችሉት እንደሆነ ተነግሮአል። በርካታ መኩራኩሮችን በአንድ ግዜ በማምጠቅ ብዙ ሰዎችን ወደ ማርስ ለማጓጓዝ እቅድ የተያዘ ሲሆን በማርስ ላይ የሰው ልጅ ኑሮውን እንዲመስርት እና ግዛት እንዲኖረውም ሰፊ እቅድ ይዘዋል። ማንኛውም ለጉዞው ጤናማ የሆነ ሰው ማመልከት የሚችል ሲሆን የማመልከቻ ክፍያ እንዳለው ታውቋል።

ሁሉም ሰው ሊያየው የሚገባ ነገር ትግራያኒያን ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደማንችል ሲነግሩን Tigrays insulting Ethiopians

Tigres are telling us that we Ethiopians can enter Ethiopia or live in Ethiopia at their will?????…..mmmmmm…yes, I am the Amara-Oromo-Gurage, my parents MADE ETHIOPIA, now the bantu race Tigres (central African-Sudan immigrants to Ethiopia) are tell us we do not have any right in Ethiopia .himmmmm ;) DENQORO TIGRE HULA, Ayit mot siyamrat ye dimet afincha tashetalech…!
Ethiopians are now aweknening from the deep sleep…..! We will consider weather Tigres can hold Ethiopian passport anymore!

የመጨረሻው መጨረሻ ጥላሁን ከስዊዘርላንድ

አብዮት በእያንዳንዱ ብሶተኛ ልብ ውስጥ ተፀንሶ በጋራ ይወለዳል፣ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ስር-ነቀል አብዮት ሊፈጥሩ የሚችሉ ተጨባጭና መሬት የያዙ ምክንያቶች አሉ፣ ስር-ነቀል—እደግመዋለሁ—ስር-ነቀል—አብዮት በኢትዮጵያ እንደማይታሰብ የወያኔ ጭፍራዎች ሲለፍፉ ቆይቶአል በመሆኑም እነሱ ባሰመሩት መስመር ብቻ ተከበን በፈቀዱልን ክበብ ብቻ ተወስነን በጉንጭ አልፋ ክርክሮችና ንትርኮች ተወጥረን በትናንሽ ሃሳቦች ላይ ከትናንሽ ካድሬዎቻቸው ጋር ስንሻኮት ከሕዝብና ከሀገር በልብም በአስተሳሰብም በአካልም ተደብቀው የሚገኙት የህወሓት(ወያኔ) መሀንዲሶች ባሻቸው ሰዓትና ቀን ከመጋረጃው ጀርባ ተደብቀው የጥፋት መርዛቸውን ከመጋረጃው ጀርባ ተደብቀው እየረጩ ሲያሻቸው የዘረኝነት መርዝ፣ ሲላቸው የሃይማኖት ጂሃድ ለማቀጣጠል የሚያስችል “ጅሃዳዊ ሐረካት” የመሰለ መርዝ፣ የኢትዮጵያዊነት ማንነትን በማጥፋት በትናንሽ ጎጠኝነት ጥንባት በማጀል ከዚህ የጎጠኝነት ክበብ እንዳንወጣ የጥፋት ሰንሰለቱን በዚህ ልክ በማጠር፣ በተሳከረ የኢኮኖሚ ፍልስፍናና ያሻቸውን ቁጥር እየመዘዙ 11 በመቶ አድገናል፣ 20 በመቶ የኑሮውን ውጣ ውረድ(ግሽበት) ቀንሰናል፣ የተራበው 12ሚሊዮን ሳይሆን 7ሚሊዮን ነው፣ የተፈናቀለው አማራ ብቻ ሳይሆን ኦሮሞም አለበት፣ ምናምን—ምናምን—እያሉ እነሱ በሚመዙልን ርዕሰ-ጉዳይ ብቻ ተጠምደን የእሳት ማጥፋት የጉንጭ ማልፋት ሥራ የምንሰራበት፣ እነሱ የሚሰጡንን የቤትስራ ተቀብለን የምንጨናበስበት ጊዜ የጨለመ ይመስላል።

መንግስት በድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች ላይ በድጋሜ ዘመቻ ሊከፍት ነው::


ኢሳት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት በየሳምንቱ የሚያቀርቡት ተቃውሞ የስርአቱን ህልውና እየተፈታተነው በመምጣቱ መንግስት ችግሩን በድርድር ከመፍታት ይልቅ በከፍተኛ እና መካከለኛ እንዲሁም በቀበሌዎች አካባቢ ያሉ የተቃውሞ አስተባባሪዎችን በመለየት ሰብስቦ ለማሰር እና ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ክስ ለመመስረት ማቀዱ ታውቋል።
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ታማኝ የኢህአዴግ ካድሬዎች በቅርቡ በጦላይ እና በብርሸለቆ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግል ስልጠና ለመውሰድ እንደሚገቡ ታውቋል። ከህብረተሰቡ፣ ከቀበሌ አመራሮች እና ከአባላት የሚውጣጡት ሰልጣኞች ስልጠናቸውን እንደጨረሱ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ይመራሉ የሚሉዋቸውን ሰዎች በመለየት ለዚህ ስራ ተብሎ ለተቋቋመው አካል ሪፖርት ያደርጋሉ።

Tuesday 30 April 2013

ግጭቱን ማን ለኮሰው? (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

Addis Ababa, Ethiopia 2005 protestቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ… አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈ ቁልቁል ወርዶ ..ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ።…በዚህ ቅፅበት አንዲት ነጭ ቶዮታ ፒካፕ (ታርጋ የሌላት ወይም ያለጠፈች) ከሱማሌ ተራ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈች ከመጣች በኋላ < በላይ ተክሉ ኬክ> ቤትን አለፍ ብላ ቆመች። ከሹፌሩ ጎን ሲቪል የለበሰና ኮፍያ ያጠለቀ ሰው የተቀመጠ ሲሆን ከመኪናው ጋር ከተገጠመው ሬዲዮ መገናኛ በተጨማሪ ሁለት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ይዟል።… 25 ወጠምሻዎች፣ ሁሉም ረዘም- ወፈር ያሉ ዱላዎችን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ገጀራ እንደጨበጡ እንዲሁም ከመካከላቸው ሁለቱ አነስተኛ ጀሪካን እንደያዙ…ከመኪናዋ ዘለው ወረዱ። ሁሉም የተቀዳደ ተመሳሳይ ድሪቶ አጥልቀዋል፤ « አደገኛ ቦዘኔ» መሆናቸው ነው። ነገር ግን « ሆን ተብሎ » የተዘጋጀ ድሪቶ እንደሆነ የሚያሳብቀው ….በግልፅ የሚታየው የሁሉም ፈርጣማ ጡንቻ ከጥሩ እንክብካቤ ጋር በስፖርት የዳበረና ወታደራዊ አቋም እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ነበር።
ከመኪናዋ ዘለው ከወረዱ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ « አትነሳም ወይ…አትነሳም ወይ …ወያኔ…ወያኔ..» እያሉ በመጮህ አንበሳ አውቶብሱን ተጠጉ። በያዙት የብረት ዱላና ስለታማ ገጀራ አውቶብሱን እንክትክቱን ካወጡ በኋላ በያዙት ነዳጅ አርከፍክፈው አቃጠሉት፤…ተመሳሳይ ጩኸትና ቅስቀሳ እያሰሙ ሽቅብ ወደ ሲኒማ ራስ አመሩ። ነጯ መኪና ከኋላ ደርሳ ሁሉንም ጫነች…ከዛም ወደፊት በፍጥነት እየካለበች አዲስ ከተማ ት/ቤት አካባቢ ደረሰች። ወጠምሻዎቹ ..የ <አትነሳም ወይ…> ቅስቀሳቸውን ሲቀጥሉ.. እግረመንገዳቸውን በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቴሌ መ/ቤት ላይ ድንጋይ በመወርወርና ከደጃፍ ቆመው የነበሩ ሁለት መኪኖችን መሰባበር ይዘዋል። ከዚሁ ጐን ለጎን በመ/ቤቱ ግቢ የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ከድራማው መጀመር ቀደም ብሎ እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ያ ድርጊት ወይም ድራማ ሲፈፀም አይተው እንዳላዩ በማለፍ ቀጣዩን ይጠብቁ እንደነበረ በሰአታት ልዩነት አፈሙዝ በንፁሃን ላይ ሰድረው ይወስዱት የነበረው የጭካኔ እርምጃ በቂ ማመላከቻ ነበር፤ ዘግይቶ የሆነውም ይኸው ነው።..

በሰኔ ወር ግድያ ሲፈፀም በመጀመሪያ ኢላማ የነበረው ይህ ት/ቤት ነበር፤ በዛ ድርጊት ገና ያልሻረ ቁስል አለ። በሌሎች አካባቢዎችና ከተሞች የነበረው የተዳፈነ የተቃውሞ ቁስል ከዚህ የተለየ አልነበረም። በሕወሐት/ኢህአዴግ አስተዳደር የተንገሸገሸው ሕዝብ..እንኳን ቀዳዳ አግኝቶ ቀርቶ እንዲሁም፥ ትንሽ ነገር ቁጣውን እንደሚያገነፍለው ግልፅ ነበር። የተሰረቀ ድምፁን ለማስከበረም በፅኑ ይፈልጋል።.. በዚሁ መሰረት በአዲስ ከተማ ተማሪው ከአካባቢው ህዝብ ጋር በአንድነት ሆኖ.. <በተለኮሰው> ተቃውሞ ውስጥ ሰተት ብሎ ገባበት።.. የተዳፈነው የሕዝብ እሳት በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተዛመተ ሔደ።

ያቺ ነጭ መኪና <ሴራዋን> ከውና በጎጃም በረንዳ በኩል ወደ ግራ ታጥፋ እየከነፈች…አባኮራን ሰፈርን እያሳበረች በዮሃንስ ቤ/ክ አድርጋ ወደ ሰሜን ሆቴል አመራች።.. <ቅልቦቹ> ተመሳሳይ የተቃውሞ ድራማ አቀጣጠሉ። ከዚህ በተጨማሪ መንግስት በቦዘኔነት <ሽፋን> ያሰማራቸው ቅልብ ሃይሎች በኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ አሰማርቶ ተመሳሳይ <ድራማ> እያቀጣጠለ ነበር። ..የተቃውሞ እሳት የጫረችው ነጯ ቶዮታ ..የማሳረጊያ ግዳጇን በሰሜን ሆ/ል አካባቢ ከተወጣች በኋላ ወጠምሻዎቹን ጭና ቁልቁል በመውረድ ወደ ማእከላዊ ወንጀል ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ነበር ሰተት ብላ የገባችው። በዚች መኪና ከፊት ተቀምጦ ትእዛዝ በመስጠትና ከበላይ አለቆቹ ጋር መረጃ ልውውጥ በማድረግ ሴራውን ሲመራና ሲያከናውን የነበረው ግርማይ (በቅፅል ስሙ ማንጁስ) የተባለ የሕወሐት አባልና በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊ እንደሆነ በወቅቱ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ ባሻገር በአንዱ ስልክ ከጠ/ሚ/ሩ ጋር በቀጥታ ይገናኝ እንደነበረ ተረጋግጦዋል። (በነገርራችን ላይ ስለዚህ ጉዳይ መረጃው ለህዝብ ሳይደርስ ጋዜጦች ወዲያው ተዘጉ)

…ባጠቃላይ በዚህ መልክ በገዢዎቹ ሆነ ተብሎ በተለኮሰው የጥፋት <ሴራ> በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን በአደባባይ በጥይት እንዲቀጠፉ ሲደረግ፣ በ10ሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ እስር ቤት ተጋዙ። የነመለስ/በረከት ቀጣዩ <ኢላማ> የቅንጅት አመራሮችንና ደጋፊዎችን፣ጋዜጠኞችን እንዲሁም ሌሎች ወገኖችን ማሰርና ማሰቃየት ስለነበር፥ ያሰቡትን ተግባራዊ አድርገዋል። ከትግራይ ሃውዜን የጀመሩት ህዝብን በጅምላ የማስፈጀት አረመኒያዊ የሴራ ተግባራቸው፥ በአርባባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ ትግራይ ሆቴል(ፒያሳ)፣ ጋምቤላ …እያለ በመቀጠል የ97/98 ምርጫን ተራምዶ እነሆ በህዝበ ሙስሊሙና በአማራ ተወላጆች ላይ ቀጥሎ ይገኛል። ከቤኒሻንጉል እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች በተራ የወረዳ ካድሬዎችና ሹሞች ትእዛዝ እንደማይፈፀም በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። ለዚህ ማስረጃው በጋምቤላ አሰቃቂ ፍጅት እንዲደርስ የተደረገው በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሹማምንት በነበሩት አባይ ፀሃዬና በምክትላቸው ዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ሰጪነት እንደሆነ የተረጋገጠና በወቅቱም የሁለቱ የሕወሐት ሹሞች ስም ጭምር ተጠቅሶ በኢትኦጵ ጋዜጣ ይፋ መደረጉ ነበር። እንዲያውም አባይ ፀሃዬ በግምገማ ላይ ዶ/ር ገ/አብን ጥፋተኛ ከማድረጋቸው በተጨማሪ < አብሬው መስራት አልችልም፤ ስለዚህ በአስቸኳይ ይነሳልኝ> በማለት የጋምቤላውን ፍጅት በዶክተሩ ላይ ከመደፍደፋቸው ባሻፈር ለ/ጠ/ሚሩ ጥያቄ አቅርበው ይኸው ተፈፀሚ ሆኗል። …ይህ በሆነበት ሁኔታ በቤኒሻንጉል በወገኖቻችን ላይ የደረሰውና ሆን ተብሎ እንዲደርስ የተደረገው መሰሪ ተግባር ከሕወሐት/ኢህአዴግ ቱባ ሹማምንት እውቅና ውጭ ብቻ ሳይሆን የነርሱ ቀጥተኛ ትእዝዛ ያለበት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።

በመጨረሻም ፥ በህዝበ ሙስሊሙ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ የመብት ጥያቄና ተቃውሞ ውስጥ የተስተዋለው ጉዳይ፥ ህዝብ ምን ያክል ገዢዎቹን በአስተሳሰብ በልጦ እንደሄደ የሚያመላክት ጭምር ነው። ይኸውም በአንዋር መስጊድና ሰላማዊ ተቃውሞ በሚሰማባቸው አካባቢዎች አንበሳ አውቶብሶችን ሆን ተብሎ በማቆም ሙስሊሙ እንዲሰብራቸው በገዢዎቹ ሲሞከር ታይቶዋል፤ ገዚዎቹ እንዳቀዱት አውቶብሶቹ ሲሰባበሩ… የ97/98 ድራማ ለመድገምና በለመዱት ጭካኔ በጥይት የጅምላ ግድያቸውን ለመተገበር ነው። የሃይማኖቱ ተከታዮች ግን « አንሰብርም….አንሰብርም…» እየሉ በአንድ ድምፅ የነበረከትን የሴራ ድራማ በማክሸፍ ለመብታቸው መቆምንና ሰላምዊ ጥያቄ ማቅረብን ነው የቀጠሉት። ህዝብ ምን ያክል ቀድሟቸው እንደሄደ ጥሩ ማሳያ ነው።
source> http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/7438

Sunday 28 April 2013

የዘረፋ ውሎ በእንዳማሪያም (ገብረመድህን አርዓያ)

ገብረመድህን አርዓያ
ፕርዝ፣ አውስትራሊያ

ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት:: ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል ፣ ይፎክራል፣ ይሸመጥጣል፣ ያቀረሻል፣ በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል:: ብዙም አልደነቀኝም:: ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል ፣ ታሪክ አውድመዋል ፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል ፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል:: በጣም ከፍተኛ ወንጀል የሰሩ ሰዎች እንደመሆናቸው በአገሪቷ የፖለቲካ ለውጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ መቀጣጠሉ እንቅልፍ እንደነሳቸው እያየን ነው:: አዎን ስብሃት ገና ፣ ገና ከዚህም በላይ ብዙ ይናገራል ፤ ቁጣው እያየለ በሄደ ቁጥር ብዙ ወንጀሎችም ይሰራል::

ዛሬ ወያኔ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በበዛ ፍጥነት እና ማን አለብኝነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ መሰረቶችን የመናዱን ስራ አጠናክሮ እየሰራ ለመሆኑ በየእለቱ የምንሰማቸው ዜናዎች እና ዘገባዎች ያሳያሉ:: እንደ እኔ ፣ እንደ እኔ የወያኔ የጥፋት ስራ ሳይሆን የጨመረው ይልቁንስ ረጅም እድሜ ለኢሳት ይስጠውና የዜና ዘገባ ብዛት እና አይነቱ መጨመሩ ይመስለኛል:: ወያኔ

! …….. “ኣሸባሪ” ነኝ ………..!

ትናንት በሰሩት ነገር ገርሞኝ ወድያ ወዲህ ስል ስለ ህወሓት ጉባኤ መረጃ ኣላሰባሰብኩም ነበር። ወደ ማታ ኣከባቢ በማላውቀው ስልክ ተደወለልኝ። ከተወሰነ ሰጣገባ በኋላ “ኣንተ ኣሸባሪ ነህ። በኣሸባሪነት እንደምንትያዝ ኣትጠራጠር” ኣለኝ።

“ኣዎ ኣሸባሪ ነኝ። ያሸበርኳቹ ያህል ነው የሚሰማኝ። ምክንያቱም ባላሸብራቹ ኑሮ የኔን ፌስቡክ ለማስዘጋት ባልተረባረባቹ ነበር” መለስኩለት።

ስልኩን ጀሮየ ላይ ጥርቅም ኣድርጎ ዘጋው።

“ለካ እንዲህ ለነፃነት የሚቆሙ፣ የፈለጉትን የሚፅፉ፣ ስለ ፍትሕ የሚዘምሩ ግለሰዎች ናቸው ‘ኣሸባሪ’ ተብለው በኣምባገነን ገዢዎች የሚሰየሙት” ስል ኣሰላሰልኩ። “ኣሸባሪ” የሚለውን ስም ወድጀዋለሁ። “ኣሸባሪ” መሆን ደስ ይላል። ጥያቄው መሆን ያለበት ‘የሚሸበረው ኣካል ማነው?’ (ሰለማዊ ህዝብ ወይስ ገዢው መደብ) ነው። ምናልባት እኔ “ኣሸባሪ” ከተባልኩ በኔ የተሸበረው ገዢው ፓርቲ ብቻ ነው።

ግን ገዢው መደብ የሚያሸብሩ ሰዎች ሌላ ስም ሊሰጣቸው ይገባል እላለሁ። ምክንያቱም መሪዎቻችን ስልጣናቸውን ያለ ኣግባብ ተጠቅመው ሰለማዊ ህዝብ ሲያሸብሩ ምን ብለን ልንሰይማቸው ነው? መንግስትን የሚቃወም “ኣሸባሪ” ከተባለ፣ ህዝብን በጭቆና የሚያሸብር ባለስልጣንስ ????

ከጭቆና በላይ ሽብር የለም። ምክንያቱም ጭቆና ማስፈራራት፣ ግድያ ……… ምናምን (ሰው ፈርቶና ተሸብሮ ሳይቃወም እንዲገዛ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች የሽብር ተግባራት ናቸው)። “ሽብር” ማለት’ኮ ኣንድ ኣካል ራሱ የሚፈልገውን ተግባር በሌሎች ሃይል በመጠቀም ወይ በማስፈራራት ለመጫን ሲሞክር ነው። ሌሎችን እያስፈራራ ያለው ማነው??? እኔ ወይስ ገዢው ፓርቲ? ኣሸባሪ ማነው? ማነው ሰለማዊ ዜጎችን በማፈን እያሸበረ ያለው?

ይሄንን ሳስብ ከቆየሁ በኋላ ትንሽ ቀለል ኣለኝ። ‘መንግስትን መቃወም ትክክል ነው’ ማለት ነው ብዬ በራሴ ተፅናናሁ።

የህወሀት ጄኔራሎች በአለም ላይ ውድ የሆነውን የታንታለም ማእድንን በህገወጥ መንገድ እየዘረፉ ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ነው


Image


ኢሳት ዜና:-ኬንቲቻ ቦረና የኢትዮጵያ ማእድን ልማት አክሲዮን ማህበር የተባለ መንግስታዊ ድርጅት ከአመታት በፊት በጉጂ ዞን በሻኪሶና አናሶራ ወረዳዎች 2ሺ 500 ቶን የሚጠጋ ንጹህ የታንታለም ማእድን ማግኘቱ የመገናኛ ብዙህንን ትኩረት ስቦ ነበር።
ኩባንያው ምንም አይነት የማጣሪያ ስራ ሳይሰራ ይህን ውድና ስትራቴጂክ ማእድን በርካሽ ዋጋ መሸጡ አገሪቱን እንደሚጎዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደጋግመው አቤቱታቸውን በማቅረብ ፣ ጥሬ እቃውን ወደ ውጭ መላኩ እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ፕሮፌሰሩ እና የመርከቡ ተሳፋሪዎች ታምራት ነገራ

ፕሮፌሰር መስፍንን እስከ ምርጫ 97 ድረስ የማውቃቸው ከውጭ እና በሩቁ ነበር፡፡ ምርጫ 97 ሲመጣ እርሳቸው እና ጓደኞቻቸው የመሠረቱት ቀስተ ዳመና ፓርቲ ከሌሎቹ ሦስት ፓርቲዎች ጋራ በመኾን ቅንጅትን የመመሥርት ጥሪ ማድረጉ ፕሮፌሰርን የማወቅ አጋጣሚ ፈጠረልኝ። በወቅቱ እኔ የኢዴሊ አባል ነበርኹ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ፕሮፌሰርን እንደ ፖለቲከኛም፤ ከዚያም አለፍ ሲል ደግሞ እንደ አዲስ ነገር ጋዜጠኛ (አዲስ አበባ ሳለች) በቅርበት ለማየት እና አብሬያቸው ለመሥራትም ዕድል ፈጥሮልኛል። በእነዚህ ዓመታት ስለ ፕሮፌሰር ሐሳቦች እና ጽሑፎች ያለኝ አመለካከት ተለዋውጧል፤ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ወሳኝ ወሳኝ የሚባሉት የፕሮፌሰር መስፍን ሐሳቦች ግን አልተለወጡም፤ እርሳቸውም መጻፍ አላቋረጡም፡፡

ከቅንጅት በፊት ፕሮፌሰር በተለያዩ ጋዜጦች የሚያሳትሟቸውን ጽሑፎች አልፎ አልፎ ገረፍ ገረፍ ከማድረግ በስተቀር ቋሚ አንባቢያቸው አልነበርኩም፡፡ በወቅቱ በአይዲዮሎጂ ልዩነት ምክንያት ፕሮፌሰር መስፍን የሚጽፉትን ጽሑፍ ማንበብም ኾነ ሐሳባቸውን ማስተናገድ ለእኔ የሚዋጥልኝ አልነበረም፡፡ ኢዴሊ ለቅንጅት መሥራችነት ሲጋበዝ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ ለማስተላለፍ በጠራው ስብሰባ ላይ “ብርሃን ከጨለማ ጋራ ምን ኅብረት አለው?!” ለማለት እስኪዳዳኝ ድረስ ከእነ ፕሮፌሰር መስፍን ጋራ ተባብረን መሥራት እንደሌለብን ወጥሬ ተከራከርኩ፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በኦሮሞ ብሔርተኝነት ጀምሬው ወደ መሀል ለማፈግፈግ ኢዴሊን እንደቤቴ ብመርጥም፤ ተዐምር ካልተፈጠረ በቀር ከፕሮፌሰር መስፍን ጎን የሚሰለፈውን እኔን ማየት አልኾነልኝም።

በወቅቱ የፓርቲያችን ሊቀመንበር የነበረው ዶ/ር ዓለማየሁ አረዳ እና ሌሎች ጠና ያሉት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ግራ ዘመም ኾነን ያስቸገርነውን ወጣቶች ወደ ቅንጅቱ እንግባ ብለው ማሳመን አቃታቸው። ውሳኔ ለማሳለፍ በጭንቅ በተወጠረው ስብሰባ መካከል ከእኛው (ከረባሾቹ