ዛሬ ጠዋት ከመኖሪያዬ ወጥቼ ጥቂት እንደተጓዝኩ ሁለት አሜሪካዊያን ወጣቶች ከፊት ለፊቴ ሲመጡ ተመለከትኩ። እጅ
ለእጅ ተያይዘዋል…በጥንቃቄ ምስላቸውን ለማስቀረት ሞከርኩ።… ( ወንድ ከወንድ- ሴት ከሴት፣ እጅ – ለእጅ መያያዝና
መተቃቀፍ ግብረ-ሰዶማዊነትን ያመለክታል በአሜሪካ)… ታዲያ ምንድነው?.. ትለኝ ይሆናል፤… ይህ «ሰይጣናዊ»
የነአሜሪካ «ቁሻሻ» በአገራችን መስፋፋቱ አሳስቦኝ ነው። የ11 እና 10 አመት ታዳጊ ሕፃናት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ
ት/ቤት ዳይሬክተሩን ጨምሮ 6 አስተማሪዎች እየተፈራረቁ «ሰይጣናዊ» ድርጊት ሲፈፅሙ እንደከረሙ መስማት
አያስጨንቅም?… ለትምህርት የላከው ልጅህ
No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.
Tuesday, 18 June 2013
አስመላሽ ወልደስላሴም በቁጥጥር ስር ዋለ!
(EMF) የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ የፓርላማ ተመራጭ እና በፓርላማው የህግ እና አስተዳደር ሃላፊ ናቸው። ሁልጊዜ ከቀድሞው ሟች መለስ ዜናዊ ኋላ ነበር ፓርላማ ውስጥ የሚቀመጡት። ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ጀርባ ሰውን ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። ምናልባት ጥቃት እንዳይሰነዘርባቸው በማለት የቅርብ ሰው ካልሆነ በስተቀር የሚቀመጥ ሰው የለም ነበር። አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ግን የህወሃት አባል ከመሆናቸውም በተጨማሪ አይነ ስውር በመሆናቸው፤ በመለስ ዜናዊ ኋላ እንዲቀመጡ ይደረግ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ከላይ የጠቀስነው ዝርዝር አንባቢዎች ግለሰቡን እንዲያስታውሱ ያህል እንጂ፤ ካነሳነው ርዕስ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ላይኖረው ይችላል።
Asmelas Woldeselassei
ሆኖም ከአገር ቤት ያገኘነው ተጨማሪ ዜና እንደሚያመለክተው ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሏል። ትላንት እሁድ ከጠዋት ጀምሮ፤ ቤቱ በፌዴራል ፖሊሶች ተከቦ የነበረ ሲሆን፤ አመሻሽ ላይ በፖሊሶች መወሰዱን ለማወቅ ችለናል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋይ የተባለችው የህወሃት አባል እና በቁጥጥር ስር ውላለች። ግለሰቧ የታሰረችው ከጥቂት ቀናት በፊት የታሰረው የባለቤቷን አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ መረጃዎችን በማሸሽ በመደበቋ መሆኑ ተገልጿል።
Monday, 17 June 2013
የቢሮ ኃላፊው በሙስና ላይ ምስክር ሳይሆኑ ተገደሉ “ብዙ ሳይታወቅ የተገደሉ ተስፋዬዎች አሉ”
በነበራቸው የስራ ሃላፊነት በድብቅ መረጃ ሲያሰባስቡ ቆይተው ለመንግስት ካጋለጡ በኋላ ራሳቸውን ደብቀው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሣ ምሳ እየተመገቡ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። አቶ ተስፋዬ ሰኞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ከኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ጋር ቀጠሮ ይዘው ነበር።
በቅርቡ ወደ ፌደራል መንግስት የተዛወሩት የጋምቤላ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኡሞት ኦባንግ፣ ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር በማደራጀት ለኢህአዴግ ያቀረቡት አቶ ተስፋዬ አሟሟታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን፤ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” በሚል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ በ (ጥቅምት 19፤2005/October 29, 2012) መዘገቡ ይታወሳል።

Sunday, 16 June 2013
UDJ urges Ethiopia and Egypt to cease bellicosity
June 16, 2013ESAT News June 15, 2013
The Ethiopian opposition political party, Unity for Democracy and Justice (UDJ), has released a press release titled “A Party committed to use everything for political consumption, endangers a country’s sovereignty”. The Party’s presser urged Ethiopia and Egypt to cease making bellicose statements, stop spreading propaganda that could harm the people to people relations of the two countries and work for a diplomatic relation and focus on round table discussions.
UDJ said Ethiopia has a natural right to use Abay River. It added both countries should stop using the Dam and the river as a means of calming down internal political tensions. It also called for the immediate start of a “national consensus”. UDJ also accused the Ethiopian government of using the
በአባይ ግድብ ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ማድረግ ተጀመረ
ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው የደህንነት መረጃ እንዳመለከተው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ቻይና እና ሩሲያ ሰራሽ ራዳሮች ሰሞኑን በአካባቢው ተተክለዋል።
መንግስት ማንኛውንም አይነት ድንገተኛ የአየር ወይም የሰርጎ ገቦች ጥቃት ለመከላከል ዘመናዊ ራዳሮችን ከመትከል በተጨማሪ የተወሰኑ የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት በአስችኳይ ወደ አካባቢው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል። በፌደራል ፖሊስ ሲደረግ የነበረው ጥበቃ በመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲጠናከር ያደረገው መንግስት ፣ በሻለቃ አበራ ወረታው አዛዥነት የሚመራው የምእራብ እዝ የ44ኛ ዳሎል ክፍለ ጦር አራተኛ ሪጂመንት በቤንሻንጉል እንዲቀመጥ ተወስናል።
በደቡብ ሱዳን ያለው ጦር የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኝም አብዩታዊ ዴሞክራሲ እና ወታደራዊ አመራር የሚል ርእስ ያዘለ የመወያያ ጽሁፍ ተዘጋጅቶ በ ስልጠና ዋና መምሪያ. ሌ/ጅኔራል ታደሰ ወረደ የሚመራ ቡድን ወደ አብየ አቅንቷል፡፡

ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ ከኢየሩሳሌም አርአያ
የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ምክትል ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ « ..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል…የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል…ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል። ..
ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ «..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል… የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል… ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል።…
Subscribe to:
Posts (Atom)