No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday 28 December 2012

በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ

ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።
40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።

Monday 24 December 2012

ከእሁድ እስከ እሁድ (የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

ኢህአዴግን በኃይል ለማስወገድ ጥሪ ቀረበ
በኢትዮጵያ ያለውን አገዛዝ ለመጣል ይቻል ዘንድ ለቀድሞው ሰራዊት፣ አሁን በስራ ላይ ላሉት የመከላከያ አባላትና በአገር ውስጥና በውጪ ስደት ላይ ላሉ ዜጎች ሁሉ የትግል ጥሪ ቀረበ። “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” በሚል ስያሜ ጥሪውን ያስተላለፈው ክፍል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሚመሩት ድርጅት ጋር ግንኙነት እንዳለው ለማጣራት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ኢሳት ዘወትር እሁድ በሚያቀርበው የሳምንቱ ዜናዎች ላይ አስታውቋል።
ኢሳት በሰበር ዜና ያቀረበው ይህ ዜና ከዋናው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ግንኙነት እንዳለውና እንደሌለው ለማጣራት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው ባይሳካለትም፣ በቅርቡ ግን መረጃዎችን በማሰባሰብ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ የሚያቀርብ መረጃ ለመስጠት እንደሚተጋ አስታውቋል።

Sunday 23 December 2012

የባህርዳር ሹማምንት በከፍተኛ ሙስና ተዘፍቀዋል ተባለ


ኢሳት ዜና:-ለአቶ በረከት ስምኦን የተጻፈ ሚስጢራዊ ደብዳቤ እንዳመለከተው በባህርዳር ከተማ ከንቲባ በአቶ ፋንታ ደጀን አማካኝነት በርካታ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ናቸው።
ደብዳቤው በብአዴን ውስጥ ሁለት በጥቅም የተሳሰሩ ቡድኖች መፈጠራቸውን ያመለክታል። አንደኛው ቡድን ደጀኔ ሽባባው በተባለው የብአዴን ጽሀፈት ቤት ሀላፊ የሚመራ ሲሆን በዚህ ቡድን ውስጥ የገቢዎች ጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆነው ክብረት ሙሀመድ፣ የከተማ አግልገሎት የቴክኒክ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅር መኮንን፣ የቤቶች ልማት ስራአስኪያጅ አቶ ክንድይሁን እገዘው፣ የንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መንግስቴ አምሳሉ እና የጥቃቅን ምክትል ሀላፊ አቶ ሙላቱ ጸጋየ ይገኙበታል።
አቶ ስማቸው ወንድማገኘሁ በተባለው ሰው በሚመራው ቡድን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ቢያድግልኝ

“የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” የምሥረታ መግለጫና ሃገራዊ ጥሪ ቀን ታህሳስ 11 2005


የወያኔን ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ “የግንቦት7 ሕዝባዊ ኃይል” የሚል ስያሜ የሰጠነውን፣ በሃገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ወጣቶች፣ ምሁራንና ዜጎች የተሞላውን ድርጅት መመሥረታችን በዛሬው እለት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እናበስራልን።
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል፣ የሕዝብ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የዜጎች መብቶች፣ ሃገራዊ አንድነት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበሩባት ጠንካራና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን ሆና የማየትን ራዕይ የሰነቀ ድርጅት ነው።