No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday, 22 March 2013

የትግራይ ህዝብ ስማ!!

ሰሞኑን በውዴታም ይሁን በግዴታ በመቀሌ እጅግ ከፍተኛ የሚባል ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲጨፍሩ፣ ሲዘሉ፣ ከበሮ እየመቱ የባህላቸውን ዘፈንና ውዝዋዜ ሲያወርዱ አይተናል። ምክንያቱ በግልጽ ባይነገርም ሲደበቅ የነበረው የህወሃት ሃብትና ንብረት ውጤት የሆኑ፣ በልዩ የመንግስት ድጋፍ የተከናወኑ ግዙፍ ተቋሞች በጎዳና ለህዝብ ሲቀርቡም ተስተውሏል። ልማቱ መልካም ነው። ደስ ይለናል። ምንም ተቃውሞ የለንም። ግን መልዕክት አለን።
ለማን?
ምሬትን፣ ጭቆናና መንገፍገፍ ሲበዛ በፍቃደኛነት በቦንብ ላይ እንደሚያስሮጥ ለሚያውቀው የትግራይ ህዝብ!! የትግራይ ህዝብ ስማ!!
ሰሞኑን ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ሪፖርት የትግራይ ክልል በትምህርት፣ በኤሌክትሪክ፣ በመንገድ፣ በእርሻ፣ በደን፣ በኢንዱስትሪ፣ በጤና፣ ወዘተ ከሌሎች ክልሎች ሁሉ ርቃ መሄዷን ይፋ አድርጓል። በዚህም ደስ ይለናል። አይከፋንም። ከዚህ በላይ እንዲሆን እንመኛለን። ነገር ግን አንድ መልዕክት አለን።

“የመለስ አስተምህሮት” ጉባኤ ታዳሚዎች

ኦህዴድ ዘግይቶ ምርጫውን ይፋ ያደረገበት ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ባህር ዳር ለሚካሄደው ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ የተሰየሙትን የየድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስም ዝርዝር ኢህአዴግ ይፋ አድርጓል። ጉባኤው “በመለስ አስተምህሮዎች ጠንካራ ድርጅትና የልማት ሃይሎች ንቅናቄ ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል ከቅዳሜ ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ ነው የሚካሄድ ሲሆን ጉባኤው አራት ቀናት እንደሚፈጅ ይፋ ተደርጓል። በጉባኤው ያለፉት ሁለት ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸምና ቀጣይ እቅዶች ላይ ይወያያል፣ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ምርጫን አስመልክቶ በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ ይኖራል ተብሎ እንደማይጠበቅ ከወዲሁ ለማወቅ ተችሏል።
ፋና ያወጣው የኢህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡ
1. ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል
2. አቶ አባይ ወልዱ
3. ወ/ሮ አዜብ መስፍን
4. አቶ አባይ ፅሃየ
5. ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል

“በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።
ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው አውሮፓዊቷ አገር መሆኑን አብራርተዋል።
49 በመቶ ተብሎ የተገለጸው የድርሻ መጠን ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የተቀራመቱት መሆኑን ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ አገር ውስጥ ካሉት የንግድ ተቋማት መካከል ኤፈርት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።

The outdated Tigray People’s Liberation Front (TPLF) fired top warlords

The Horn Times Breaking News March 21, 2013
by Getahune Bekele

Panicking and in state of collapse, one of Africa’s criminal political organizations, the TPLF has fired top genocidal warlords who are wanted by the people of Ethiopia for war crimes, crimes against humanity and genocide committed since May 1991.

All four who played a crucial role in creating the world’s brutal apartheid state in east Africa and accused of building Tigrai republic, the home province of TPLF with skin, flesh and bones of oppressed Ethiopians; are expected to flee the country dreading the total collapse of the party which provides all warlords with protection from prosecution.

! …… የትግራይ ህዝብና ህወሓት ………….!


እውነት ነው። የህወሓት መሪዎች የትጥቅ ትግሉ ጀመሩት። ደርግ ዓማፅያኑ ለማጥፋትና ትግራይን ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃ መውሰድ ጀመረ። ትግራይ የጦርነት ኣውድማ ሆነች። የትግራይ ገበሬዎች በሰላም የእርሻ ስራቸው ማከናወን ኣቃታቸው። የደርግ ወታደሮች ገበሬዎቹን ማስፈራራት፣ ሴቶችን መድፈር፣ ወጣቶችን በግደል (በጥርጣሬ) ተያያዙት።

በደርግ ኣሰራር የተማረረው የትግራይ ገበሬ ጫካ ገባ። እዛው ጫካ ከህወሓቶች ጋር ተቀላቀለ። ኣብዛኛው ታጋይ (ገበሬ ወይ ኣርሶ ኣደር) ደርግን ለመታገል ጠመንጃ ያነሳው በደርግ ስርዓት በነበረ ጥሩ ያልሆነ የሰለማዊ ሰዎች ኣያያዝ እንጂ እንደሚነገረን እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ። በዚ ምክንያት በትግራይ ከኣንድ ቤተሰብ ቢያንስ ኣንድ ታጋይ (የተሰዋም በህይወት ያለም) ነበር (ኣለ)።

ነገር ግን ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የህወሓት ደጋፊ ኣይደለም። ምሳሌዎችን ልጥቀስ።

ምሳሌ ኣንድ

የትግራይ ኣርሶ ኣደር የታገለበት ዓላማና የመሪዎቹ ለየቅል ነበር። በ1983 ዓም የህወሓት መሪዎች ኣራት ኪሎ ቤተ መንግስት ከገቡ በኋላ የመሪዎቹ ዓላማ ለታጋይ ገበሬዎቹ ግልፅ ሆነ። በታጋዮቹና መሪዎች የዓላማ ልዩነት ግልፅ ሆነ። ታጋይ ገበሬዎቹ ጥያቄ ኣስነሱ። ጥያቂያቸው ምን ነበር??? ስድስት ጥያቄዎች:

Thursday, 21 March 2013

! …….. “ኣሸባሪ” ነኝ ………..!

 

ትናንት በሰሩት ነገር ገርሞኝ ወድያ ወዲህ ስል ስለ ህወሓት ጉባኤ መረጃ ኣላሰባሰብኩም ነበር። ወደ ማታ ኣከባቢ በማላውቀው ስልክ ተደወለልኝ። ከተወሰነ ሰጣገባ በኋላ “ኣንተ ኣሸባሪ ነህ። በኣሸባሪነት እንደምንትያዝ ኣትጠራጠር” ኣለኝ።

“ኣዎ ኣሸባሪ ነኝ። ያሸበርኳቹ ያህል ነው የሚሰማኝ። ምክንያቱም ባላሸብራቹ ኑሮ የኔን ፌስቡክ ለማስዘጋት ባልተረባረባቹ ነበር” መለስኩለት።
...

ስልኩን ጀሮየ ላይ ጥርቅም ኣድርጎ ዘጋው።

“ለካ እንዲህ ለነፃነት የሚቆሙ፣ የፈለጉትን የሚፅፉ፣ ስለ ፍትሕ የሚዘምሩ ግለሰዎች ናቸው ‘ኣሸባሪ’ ተብለው በኣምባገነን ገዢዎች የሚሰየሙት” ስል ኣሰላሰልኩ። “ኣሸባሪ” የሚለውን ስም ወድጀዋለሁ። “ኣሸባሪ” መሆን ደስ ይላል። ጥያቄው መሆን ያለበት ‘የሚሸበረው ኣካል ማነው?’ (ሰለማዊ ህዝብ ወይስ ገዢው መደብ) ነው። ምናልባት እኔ “ኣሸባሪ” ከተባልኩ በኔ የተሸበረው ገዢው ፓርቲ ብቻ ነው።


ግን ገዢው መደብ የሚያሸብሩ ሰዎች ሌላ ስም ሊሰጣቸው ይገባል እላለሁ። ምክንያቱም መሪዎቻችን ስልጣናቸውን ያለ ኣግባብ ተጠቅመው ሰለማዊ ህዝብ ሲያሸብሩ ምን ብለን ልንሰይማቸው ነው? መንግስትን የሚቃወም “ኣሸባሪ” ከተባለ፣ ህዝብን በጭቆና የሚያሸብር ባለስልጣንስ ????

Wednesday, 20 March 2013

30 000 ኢትዮጵያውያንን ለጨፈጨፈው ለግራዚያኒ የተሠራውን ኃውልት መቃወም ያስከብራል!

ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ
4002 Blacksmith Drive, Garland, TX 75044, USA
መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ/ም

መግለጫ

በኢጣልያ፤ ከሮማ ወደ ምሥራቅ ደቡብ በምትገኝ፤ አፊሌ በምትሰኝ ትንሽ ከተማ፤ “የኢትዮጵያ ጨፍጫፊ” ለተሰኘው፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ ነሐሴ 4 ቀን 2004 ዓ/ም የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት የተመረቀለትን የክብር መታሰቢያና መናፈሻ በመቃወም፤ እስከ የኢጣልያ ኤምባሲ ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ/ም ስድስት ኪሎ የተሰበሰቡትን 43 ሰዎች፤ ዶር. ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጭምር፤ ፖሊስ አፍሶ ማሰሩና በማግስቱ፤ መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ/ም መልቀቁ ታውቋል።

አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን፤ ከነዚሁ ውስጥ በሶስት ቀኖች ብቻ፤ በአዲስ አበባ ከተማ 30፣000 ሕዝብ ላስጨፈጨፈው፤ እነአቡነ ጴጥሮስን፤ የደብረ ሊባኖስን መነኮሳትና ሌሎችንም በጭካኔ ለረፈረፈ፤ እንዲሁም 2000 ቤተክርስቲያኖችንንና 525፣000 ቤቶችን ላስወደመው፤ በተጨማሪም በብዙ አይሮፕላኖች ባስነሰነሰው የመርዝ ጋዝ ብዙ ሕዝብ ከመግደሉ በላይ እጅግ የከፋ የአካባቢ ብክለትና 14 ሚሊዮን እንስሶችን ላወደመው የጦር ወንጀለኛ፤ ለሮዶልፎ ግራዚያኒ የተሠራውን መታሰቢያ መቃወም ለሐገር የሚያኮራና የሚያስመሰግን እንጂ የሚያሳስር አይደለም።

Tuesday, 19 March 2013

! …….. ኣንድ ለ ኣምስት በህወሓት ጉባኤ: ‘የድርጅት ሥራ’ …..!


ትናንት ማታ ግርማይ ገብሩ (የVOAው የመቐለ ዘጋቢ ጋዜጠኛ) የህወሓት ስብሰባ ኣስመልክቶ ባጠናቀረው ዘገባ ብርሃነ ኪዳነማርያም የተባለ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል በህወሓቶች የመከፋፈል ኣደጋ ስለመኖሩና ኣለመኖሩ እንዲያብራራ ተጠይቆ ሁሌም እንደሚሉት ኣፉን ሞልቶ ‘በፍፁም የለም’ እንደ ሚል ኣልተጠራጠርኩም ነበር። ምክንያቱም መሪዎቻችን በ1993 ዓም ‘በህወሓት መከፋፈል ኣልነበረም’ ብለ...
ው የሚከራከሩኮ ናቸው። ደግሞ ኣደጋው ቢኖርስ እንዴት ለሚድያ ሰው ‘ኣዎ የመከፋፈል ነገር ኣለ’ ብሎ ሊናገር ይችላል? ግን ኣደጋው መኖሩ ኣልደበቀም ……. ‘ መከራከር ያለ ነው…. ምናምን …. ዙርያ ጥምጥም …. ። እኛስ ገብቶናል፤ እናውቀዋለንም።

የመሪዎቹ ኣለመግባባት በጉባኤውም እንደቀጠለ ነው። ስብሓት ነጋ ያለ ድምፅ እንዲሳተፍ ተደርገዋል። ሙሁራን (በተለይ ደግሞ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ኣባላት) ጥያቄ ሊያስነሱ ይችላሉ በሚል ስጋት በጉባኤው እንዳይሳተፉ ተደረገዋል (ሁለት ብቻ ያለ ድምፅ እየሳተፉ ነው)።

Monday, 18 March 2013

The selling of Ethiopia. By Yilma Bekele

Actually that statement might not be true. We do know our country is being sold but we have no idea if the bidding has been open or closed. We have sold almost all of Gambella, we have leased half of Afar and Oromia has been parceled out bit by bit. Our Beer factories are under new owners, our gold mines belong to the fake Ethiopian sheik, Telephone is under the Chinese and our Airlines is looking for a suitor. Have we always looked for outsiders to own us?
Not really when you consider that we celebrated the victory at the battle of Adwa a few weeks back and that was the mother of all wars that made it clear this African country is not for sale. We might not have contributed much to the industrial revolution but we did manage to rely on our own

Sunday, 17 March 2013

የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው! ሰማያዊ ፓርቲ

ዛሬ መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡
እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡

በሚዲያ መረሳት ያስፈራል “ነጻ ፕሬስ ከሌለ አገር አደጋ ላይ ነው”

“ከምድር በታች ጨለማ ቤት ውስጥ የታሰሩትን በቀን ለ10 ደቂቃ እናያቸዋልን። ልብ የሚነካ ነው። የብርሃን ማነስ አይናቸውን እንደጎዳቸው ያስታውቃሉ … ሴቶችን በተገኘው ሰበብ ያስሯቸዋል። ምክንያት ፈልገው እስር ቤት ይከቷቸዋል። ከዚያም ይደፍሯቸዋል። በርካታ የተደፈሩ እህቶች አሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና መንግሥት ያሰማራቸው ሚሊሻዎች ይህንን አሳዛኝ ድርጊት እንደፈጸሙ ተነግሮናል” ይህ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ፣ ችግሩ ባለበት ቦታ ተገኝቶ የነበረው ስዊድናዊ የፍሪላንሰር ጋዜጠኛ ማርቲን ካርል ሻቢዬ ቃል ነው።
ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት መስማት ይጨንቃል። ሰዎች በሲቃ የሚያሰሙት የጣር ድምጽ ለጆሮ  የተለመደ ነው። ከመሬት በታች የጨለማ ክፍል አለ። በዚህ መታጎሪያ ውስጥ ሆነው ስቃይ የሚፈራረቅባቸው ወገኖች ጥቂት አይደሉም። ማዕከላዊ ብዙ ጉድ ያለበት ሲኦል ነው። የሰው ልጆች በግፍ ማቅቀውበታል። እየማቀቁበትም ነው። ለውጥ እስከሌለ ድረስ የሚቆም አይመስልም። በመሃላ የሚነገርለት ውርስና ይቀጥላል የሚባለው የመለስ ራዕይ አንዱ ክፍል ይህ ነው።