No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday 13 September 2013

አስገራሚ የሎተሪ ታሪኮችና ገጠመኞች

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከመቋቋሙ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የሎተሪ ጨዋታ በተለያየ መልኩ ይካሄድ ነበር፡፡ ህግ ከመውጣቱ በፊት የሚካሄዱት ቁማር መሰል ጨዋታዎች በህብረተሠቡ ዘንድ “ኪሳራ” በመባል ነበር የሚታወቁት፡፡ በ1938 ዓ.ም ህገወጥ ሎተሪዎችን የሚያግድ አዋጅ ከወጣ በኋላ፣ “ኪሳራ” የሚባሉት የቁማር ጨዋታዎች ቀሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ አንዳንድ ግለሠቦች ፈቃድ እያወጡ ሎተሪ ማጫወት ጀመሩ፡፡ አንዳንዴ ገንዘቡን እየሰበሰቡ የሚጠፉ ሁሉ ነበሩ፡፡ በ1945 ዓ.ም ነው መንግስት ሎተሪ እንዲያካሂድ የሚፈቅድ አዋጅ የወጣው፡፡ በመጨረሻ በ1954 ዓ.ም የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ማቋቋሚያ አዋጅ ታወጀ፡፡ ብሔራዊ ሎተሪ ሲመሰረት የሠራተኞቹ ቁጥር አምስት ብቻ ነበር አሁንስ? የአዲስ ዓመት ዋዜማ እንግዳችን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ አቶ ቴዎድሮስ ነዋይ፤ መ/ቤታቸው

Monday 9 September 2013

እንኳንለአዲሱዓመትአደረሰህ! ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደ-ማርያም

 
 


 የሰሞኑ መልካም ምኞች የሚመስል ስሜት የምንለዋወጠው “እንኳን አደረሰሽ (አደረሰህ)” በመባባል ነው። ከየት ተነስተን ወዴት እንደደረስን ግን አናውቅም። ምኞቱ የሚገልጸው ሁላችንም በአንድነት ወደተሻለ ደረጃ መሸጋገራችንን ይመስላል፤ እውነቱ ግን ሁላችንም በአንድነት ቁልቁል ወርደናል።...


“… ጋሼ ማረኝ ማረኝ፤ ጋሼ ማረኝ ማረኝ

ዶሮ ብር አወጣች እኔን ሥጋ አማረኝ! …”

ተብሎ የተዘፈነበት ጊዜ መቶ ዓመት ሊሆነው ነው፤ ዛሬ እኛ ምን ብለን ልንዘፍን ይቃጣናል?

በስዊድን ጉተንበርግ ከተማ ሊደረግ የታሰበው የዓባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ከሸፈ (ቪዲዮ አለው!)

ተቃዋሚው ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ መድረኩን ተቆጣጠሮ ያዘ (ቪዲዮ አለው!)
 

“ይገርማል!” ብሎ መጀመር ይቻላል። አዎን ይገርማል! ከስቶክሆልም የሄድነው ወደ አዳራሹ የገባነው ጥሪ ባደረጉበት 13፡00 ሰዓት ነበር። እ.ኤ.አ ኦገስት 31 ቀን 2013.። ህዝቡ እስኪሰባሰብ ጥቂት ከተጠበቀ በኋላ ስብሰባው በአንድ የኢህአዴግ/ወያኔ ካድሬ ተከፈተ። እንዲህም አለ፤ “እዚህ እኛን ለመቃወም የመጣችሁ እንዳላችሁ እናውቃለን። ሃሳባችሁን እንድትናገሩ አንከለክልም፤ ነገር ግን ጩኸት፣ አላስፈላጊ ረብሻና ግርግር የምትፈጥሩ ከሆነ ወዮላችሁ! አስቀድመን ባዘዝነው የፖሊስ ኃይል እየተለቀማችሁ ትወጣላችሁ። መውጣታችሁ ብቻ አይደለም፤ ታሪካችሁ ይጠፋል፣ ውርደት ይከተላችኋል። በመለያ ቁጥራችሁም ላይ የሚጻፈው ወንጀል ዕድሜ ልካችሁን ይከተላችኋል።”