No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday, 5 July 2013

ድምጻችን ይሰማ፡በደሴ የደሴ ሙስሊም አሁንም ድረስ ባልፈፀመው ወንጀል እየተሰቃየ ይገኛል!

ትላንት ማታ ሰኔ 27/05 ከኢሻ ሾላጽ በኋላ በሸዋበር ሸኽ ያቁት መስጂድ አካባቢ ሸኽ ኑሩ የተባሉት ግለሰብ በመገደላቸው ዛሬ የደሴ ሙስሊም ባልሰራው ወንጀል መሰቃየት ጀምሯል፡፡ ጧት በ06 ማእከል የከተማዋ ሚኒሻዎችና የፌደራል ፖሊሶች ዝግ ስብሰባ አድርገው የነበረ ሲሆን ከአሱር ሶላት በኋላ የጅምላ አፈሳ ጀምረዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ በደረሰን መረጃ አህመድ ኢንጂነር፣ አህመድ አሊ፣ ከድር አሊ እንዲሁም ሌሎች ወንድሞቻችን ከሚሰሩበትና ከቤታቸው ባልታወቁ የፌደራል ፖሊሶች ታፍሰው ተወስደዋል፡፡ከግድያው በኋላ ትላንት ምሽት መንገድ ላይ ካገኟቸው ሰዎች ሶስት ሰዎችን እንደያዙም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰሞኑን ከደህንነት አካላቶች ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው የሚታወቁትና በመንግስት አካሄድ ላይ ቅሬታና አስተያየት ሲሰጡ የነበሩት ሸኽ ኑሩ ትላንት ምሽት ተገድለው ለገኝተዋል፡፡ ግድያው በደህንነት አካላቶች እንደተፈፀመ የሚያሳዩ ምልክቶች የታዩ ሲሆን ይህ ነገር ተሸፋፍኖ እንዲያልፍ ሬሳቸው ሆስፒታል ቢሄድም አስክሬኑ ያለምንም ምርመራ ከሆስፒታል ወጥቶ ለቤተሰቦቻቸው በፌደራል ፖሊሶች መኪና ተመልሷል፡፡

Thursday, 4 July 2013

! ...... What Is Missing In Egypt Politics? ....! Abraha Desta


 After having accumulated political grievances, Egyptians have already overthrown the Authoritarian Mubarek regime by a ‘popular uprising’. By doing so, Egyptians were expecting to have ‘more democratic’ government, elected by the peoples themselves.

Then a ‘new constitution’ was/is ratified. Egyptians had elected another president thereby a change from ‘authoritarian’ to ‘theocratic’ regime. Yet, Egyptians are still unhappy about the changes. As a result, the ‘uprising’ resumed.

Now, Egyptians turned against the president whom they had elected themselves. President Morsi was ‘democratically’ elected. Yet, the ‘elected president’ has recently been removed from his position by another ‘popular revolt’ accompanied with a ‘military coup’.

Wednesday, 3 July 2013

አቶ ታምራት በንግድ ተሰማሩ፤ ቢተው ስልጣን ያዙJuly 3, 2013 ከኢየሩሳሌም አርአያ

 
Former Prime Minister Tamrat Layneበአሜሪካ ዴንቨር ከተማ ከቤተሰባቸው ጋር የሚኖሩት አቶ ታምራት ላይኔ የጋዝ እስቴሽን በመክፈት በንግድ ስራ መሰማራታቸውን ምንጮች ገለፁ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ለአስራ ሁለት አመት ታስረው የወጡት አቶ ታምራት ከተፈቱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፥ አማኝ ሆነው እንደሚቀጥሉና ነገር ግን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከማንም ፖለቲካ ድርጅት ጋር ሳይወግኑ ለአገር ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ እንደሚያካፍሉ፣ መፅሃፍ እንደሚያዘጋጁ…ገልፀው እንደነበር ያስታወሱት እነዚህ ወገኖች፣ ታምራት ያንን ቢናገሩም በቃላቸው ግን እንዳልተገኙ አስረድተዋል። « የኢየሱስ አገልጋይ ሆኜ እኖራለሁ» ያሉት ታምራት አሁን ወደ ንግድ አለም መግባታቸው እንዳስገረማቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ሌላው ቢቀር በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ለሰሩት ጥፋት ህዝብን ይቅርታ ያለመጠየቃቸው አስገራሚ ነው ያሉት እነዚህ ወገኖች፣ በይፋ አደባባይ ወጥተው ህዝብን ይቅርታ የጠየቁት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ገብሩ ብቻ እንደሆኑ አስታውቀዋል። አቶ ታምራትና አቶ ስዬ ግን ይህን ለማድረግ ጨርሶ እንደማይፈልጉ ከያዙት አቋም በቀላሉ መረዳት ይቻላል ብለዋል።

የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አዋጅ ጸደቀ ኢሳት ዜና


 ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-በሚኒስትር ማእረግ ደረጃ እንዲቋቋም የታሰበው የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት መ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ዛሬ ለፓርላማው ቀርቦ ...
እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡

የኣመቱ ሥራውን ሰኔ 30 የሚያጠናቅቀውና ለዕረፍት የሚዘጋው ኢህአዴግ መራሹ ፓርላማ በተጣደፈ አሰራር ያጸደቀው በዚሁ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው መ/ቤት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተንና የማቅረብ እና የደህንነት አገልግሎት የመስጠት እንዲሁም በአገር ውስጥ የጸረ ሸብርተኝነት እና የበረራ ደህንነትን የማስጠበቅ ሥራዎችን በኃላፊነት
ይሰራል።

መ/ቤቱም ካለበት ህገመንግስታዊና አገራዊ ሃላፊነት እንዲሁም ካለው ስልጣንና ተግባር በመነሳት በሚኒስቴር መ/ቤት ፕሮቶኮል ደረጃ እንደሚሰራ በአገሪቱም የተለያዩ ቅርንጫፍ መ/ቤቶችን ከፍቶ እንደሚንቀሳቀስ አዋጁ ያስረዳል፡፡

ማንኛውም ሰው በመ/ቤቱ መረጃ ሲጠየቅ የመተባበር፣ የሠጠውንም መረጃ በሚስጢር የመያዝ ግዴታ የተጣለበት ሲሆን ይህንን የተላለፈም በወንጀል እንደሚጠየቅ ደንግጓል፡፡

Tuesday, 2 July 2013

“Ethiopia After Meles” Testimony of Berhanu Nega , Ph.D

June 26, 2013

Dr. Berhanu Nega's SpeechTestimony of Berhanu Nega,
Ph.D Associate Professor of Economics, Bucknell University
Before the House Committee on Foreign Affairs
Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations
June 20, 2013

“Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights”

Good Morning Chairman Smith, Ranking Member Bass, Distinguished Members of the House Africa Subcommittee. Thank you for inviting me to speak with you today. It is indeed a great honor and privilege to have the opportunity to appear before you to discuss issues related to the future of Democracy and Human Rights in Ethiopia.

ኢትዮጲያ ፍረጂ!!….(ከኢየሩሳሌም አርአያ)



ኢትዮጲያ ፍረጂ!!
እነዚህ ሁለት ሕፃናት በቅዳሜና እሁድ የእረፍት ቀን ከወላጆቻቸው ጋር « አንበሳ ግቢ፣ ህፃናትና ወጣቶች ትያትር፣ መጫወቻ ባለባቸው የመዝናኛ ስፍራዎች…» ወዘተ ለመሄድ አልታደሉም። ይልቅስ በነዚህ ቀናት ሕፃናቱ ቃሊቲና ዝዋይ እስር ቤቶች እንዲመላለሱ ተፈርዶባቸዋል። ንፁሃን በሆኑት የሁለቱ ሕፃናት አባቶች ላይ ሕገ-ወጥና ጭርሶ ተቀባይነት የሌለው የፈጠራ ክስና ፍርድ በማሳለፍ – በነዚህ ሕፃናትም ላይ በቀጥታ ፍርዱ እንዲያርፍ ተደርጓል። ሕፃናቱ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ልጆች ናቸው። እነዚህን ሕፃናት የሚቀጡት ወይም የሚያሰቃዩት የገዢው ባለስልጣናት በአንፃሩ ልጆቻቸውን ከአገርና ህዝብ

!...... ወይ የሀገር ባህል .............! Abraha Desta

'ኦሾ' የተባለው ህንዳዊ ፈላስፋ ግሪክ ሀገር ሂዶ ለማስተማር በሚዘጋጅበት ሰዓት የሀገሪቱ ዋና ዋና የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ተሰብስበው መንግስት ኦሾ የተባለውን ሰው ከሀገራቸው ባስቸኳይ እንዲያስወጣ ወተወቱ። ያቀረቡት ምክንያት "የልጆቻችን አስተሳሰብ ይቀይራል፣ ባህላችን ያበላሽብናል" የሚል ነበር። ኦሾ ከግሪክ ሀገር እንዲወጣ ታዘዘ። ኦሾ አስተያየት ሰጠ። "ግሪካውያውን ከሁለት ሺ ዓመት ቆይታም ለውጥ አላመጡም። ለሶቅራጠስ መርዝ ያጠጡበት ምክንያታቸው እስካሁን ድረስ አለ። ይሄው ለኔ ትምህርትም ተመሳሳይ ምክንያት ሰጡ" አለ።

ከሁሉም በላይ የከፋ ዕንቅፋት የሰው አስተሳሰብ ነው። አይሁዳውያን ኢየሱስ የተለየ ሓሳብ ስላራመደ ሰቀሉት። የኢየሱስ ተከታዮችም በክርስትና ስም የስንት ንፁህ ሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኑ። ዓረቦች ነብይ መሓመድን ከሀገር አባረሩ (ከባህላቸው ውጭ ስላስተማረ ነበር)። ባህል ዕዳ ነው።

ቤቲ ስለተባለች ልጅ ለመክሰስ ዓቃብያን ሕግ እንቅስቃሴ እንደጀመሩ ሰማሁ። እነዚህ ሰዎች ይህን ያህል ስራ አጥተው ነው? በኢትዮዽያ ክስ ለመመስረት የሚያስችል ብዙ የፍት ሕ ችግር የለም? ብቻ ይገርማል።

ለማንኛውም ሰሚር ዓሊ የፃፈውን ልጋብዛቹ።

Monday, 1 July 2013

አቶ ስዬ በተመድ ተቀጠሩ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)




አቶ ስዬ አብርሃ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አሰከባሪ ተቋም ውስጥ በወታደራዊ አማካሪነት በጥሩ ደመወዝ መቀጠራቸውን ምንጮች ጠቆሙ። በሙስና ወንጀል ተከሰው ከወንድሞቻቸው ጋር ለስድስት አመት ታስረው የተፈቱት ስዬ በተፈቱ ማግስት የአሜሪካን ድምፅ ራዲዬን ጨምሮ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ « ፖለቲካ ከልጅነቴ ጥርሴን የነቀልኩበትና አብዛኛው እድሜዬን ያሳለፍኩበት በመሆኑ ከትግሉ መድረክ ልርቅ ጨርሶ አልችልም» በማለት አስረግጠው መናገራቸውን እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ። « መድረክ » የሚል የፖለቲካ ስብስብ ከፈጠሩና የአንድነት አባል መሆናቸውን በይፋ ካወጁ በኋላ «ለትምህርት» በሚል ወደ አሜሪካ የመጡት ስዬ ከአንድነት ፓርቲ ሪፖርት እንዲያደርጉ የቀረበላቸውን ተደጋጋሚ ጥያቄና ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን አመልክተዋል። በመጨረሻ « በቅርቡ አገር ቤት ተመልሼ ትግሌን እቀጥላለሁ » ማለታቸውን ያልሸሸጉት ምንጮቹ ስዬ ይህን በተናገሩ ሰሞን በሲያትል በተደረገ ስብሰባ ላይ « ለ21 አመት የተጀመረውን ልማትና ዲሞክራሲ እናስቀጥላለን» በማለት ብዙዎችን አንገት ያስደፋና ያሳዘነ ንግግር ማሰማታቸውን አስታውሰዋል። በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን ለመግለፅ አደባባይ መውጣታቸው ብሎም « ያሰራቸውን ስርአት ዲሞክራሲያዊ » አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው አስገራሚ ነበር ብለዋል።

Sunday, 30 June 2013

ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!? (ከአቤ ቶኪቻው)

ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!?
ባለፈው ጊዜ አንድ ወዳጄ ጋር አዲሳባ ስልክ ደውዬ ሳናግረው በአካባቢው ከእርሱ ድምጽ ጎልቶ የሚሰማ የመኪና ጥሩንባ ሰማሁና ይሄ ሁሉ የመኪና ጥሩምባ ምንድነው… ብዬ ጠየኩት፡፡
Journalist Temasegan Dasalegሃይለማሪያም ደሳለኝ እየገቡ ወይም እየወጡ ነው መሰለኝ መንገድ ተዘጋግቷል፡፡ አለኝ፡፡
ወዲያውም ቀጠል አድርጎ፤ እንደ ሀቁ ቢሆን ኖሮ መንገድ መዘጋጋት የነበረበት ለሀይለማሪያም ደሳለኝ ሳይሆን ለተመስገን ደሳለኝ ነበር… አለኝና በቁጭት፤ ይሄው የሚያጅቡትን አያቀውቁምና… እልኩ እያታዘብኩ ነው…! ሲል አወጋኝ!
ተመስገን ደሳለኝ ገዢውም ተገዢውም ፓርቲ ሊያመሰግነው የሚገባ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ነገር ግን ገዢዎቻችን ማመስገን የሚቆጥር ይመስል ሰውን ማመስገን አይወዱም፡፡ ስለዚህ ተሜንም በማመስገን ፈንታ ከሰሱት፡፡ ጎሽ በማለት ፈንታ እንደ ጎሽ ሊወጉት ቀንዳቸውን አሾሉበት፡፡ እሰይ በማለት ምትክ ሰይ ባንከረባብት ብለው ለሁለቱም አሰቡት፡፡ (ለማሰርም ለማሰደድም) (ሰይ ባንከረባብት በልጅነታችን ብይ ጨዋታ ላይ ተወርዋሪዋ ብይ ጉድጓዳ ውስጥ ብትገባም የተቃራኒውን ብይ ብትመታም ነጥቡ እንዲያዝልን ውል የምንገባባት ቃል ነበረች፡፡)
ተመስገን ደሳለኝ እንዲሰደድ መንግስት ከፀሎት ጀምሮ ሁሉንም አይነት የትግል ስልቶችን እንደተጠቀመበት ትዝ ይለኛል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ጊዜ ምንም የቀጠሮ ወረቀት ወይም መጥሪያ ሳይሰጠው በራዲዮን፤ “ተመስገን ደሳለኝ በሌለበት የፍርድ ሂደቱ ታየ

ጄ/ል ክንፈ ተመለሱ፤ መከላከያ ውጥረት ነግሷል – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


 የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላለፉት ሶስት ወራት ገደማ ከስልጣናቸው ታግደው ከቆዩ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ሃላፊነት መመለሳቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ታግደው ከቆዩት ከፍተኛ ጄነራሎች መካከል አንዱ ጄ/ል ክንፈ እንደሚገኙበት የጠቆሙት ምንጮቹ ስልካቸውን በመጥለፍ በእንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር አስታውቀዋል። ጄ/ል ክንፈ በሳሞራ ታግደው የቆዩት

! .... ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ ......!



አንድ ጓደኛየ አንድ የተቀናበረ ቪድዮ በፌስቡክ ገፄን ለጠፈልኝ፤ እንዳነበው እየጋበዘኝ መሆኑ ነው። ቪድዮው ስለ ጀዋር ነው። ግን የሌሎች ሰዎች ስሞችም (የኔን ጨምሮ) ተጠቅሷል። ልጁ ቪድዮውን ሲጋብዘኝ አንዳንድ ዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ስለኔ ያላቸው አመለካከት እንዳውቅና ኢህአዴግ መቃወሜን እንዳቆም 'በአሪፍ' ተፅዕኖ ማሳደሩ ነው፤ ይህን ድምዳሜ የመጣልኝ ልጁ (ቪድዮው የላከልኝ) ከዚህ በፊት ይልክልኝ በነበሩ ተመሳሳይ መልእክቶች በመነሳት ነው። ይህን የፖለቲካ ስትራተጂ እንደማይሰራ በተደጋጋሚ ለማረጋገጥ ሞክርያለሁ።

ግን ...

ሰዎች በኔ ሓሳብ ሊደሰቱ ወይ ሊናደዱ ይችላሉ፤ መደሰትም መናደድም መብታቸው ነው። እኔ ደግሞ የፈለኩትን የመፃፍ መብት አለኝ። ስለዚህ የኔ አቋም ሌሎች ሰዎች በሚሰጡኝ ምላሽ የተንጠለጠለ አይደለም።