No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday, 5 July 2013

ድምጻችን ይሰማ፡በደሴ የደሴ ሙስሊም አሁንም ድረስ ባልፈፀመው ወንጀል እየተሰቃየ ይገኛል!

ትላንት ማታ ሰኔ 27/05 ከኢሻ ሾላጽ በኋላ በሸዋበር ሸኽ ያቁት መስጂድ አካባቢ ሸኽ ኑሩ የተባሉት ግለሰብ በመገደላቸው ዛሬ የደሴ ሙስሊም ባልሰራው ወንጀል መሰቃየት ጀምሯል፡፡ ጧት በ06 ማእከል የከተማዋ ሚኒሻዎችና የፌደራል ፖሊሶች ዝግ ስብሰባ አድርገው የነበረ ሲሆን ከአሱር ሶላት በኋላ የጅምላ አፈሳ ጀምረዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ በደረሰን መረጃ አህመድ ኢንጂነር፣ አህመድ አሊ፣ ከድር አሊ እንዲሁም ሌሎች ወንድሞቻችን ከሚሰሩበትና ከቤታቸው ባልታወቁ የፌደራል ፖሊሶች ታፍሰው ተወስደዋል፡፡ከግድያው በኋላ ትላንት ምሽት መንገድ ላይ ካገኟቸው ሰዎች ሶስት ሰዎችን እንደያዙም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰሞኑን ከደህንነት አካላቶች ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው የሚታወቁትና በመንግስት አካሄድ ላይ ቅሬታና አስተያየት ሲሰጡ የነበሩት ሸኽ ኑሩ ትላንት ምሽት ተገድለው ለገኝተዋል፡፡ ግድያው በደህንነት አካላቶች እንደተፈፀመ የሚያሳዩ ምልክቶች የታዩ ሲሆን ይህ ነገር ተሸፋፍኖ እንዲያልፍ ሬሳቸው ሆስፒታል ቢሄድም አስክሬኑ ያለምንም ምርመራ ከሆስፒታል ወጥቶ ለቤተሰቦቻቸው በፌደራል ፖሊሶች መኪና ተመልሷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ሰኔ 28/05 ከአሱር ሶላት በኋላ ደሴ ከተማ ማንነታቸው ባልታወቁና በከተማይቱ ታይተው በማይታወቁ የፌደራል ፖሊሶች እየታመሰች ትገኛለች፡፡ ወንድሞቻችን በጅምላ እየታፈሱ ይገኛል፡፡ ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣም አንዳንድ ወንድሞቻችን ቤቶች እየተበረበሩ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካከል የወንድም አህመድ ኢንጂነሩ ቤት በፌደራሎች እየተበረበረ እንደሆነ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡

መንግስት ግለሰቦችን እንደፈለገ ከተጠቀመባቸውና ከእነርሱ የሚፈልገውን ነገር ካገኘ በኋላ አላምጦ እንደሚተፋቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ከእዚህ በፊት እንኳን በእነ አቶ ጁነዲን ሳዶና በሌሎችም ታላላቅ ባለስልጣናቶች ይህን እኩይ ተግባሩን በግልፅ አሳይቶናል፡፡ ሸኽ ኑሩንም ሊገድል እንዳሰበና በሙስሊሙ ላይ የጅምላ አፈሳ ለማድረግ እንዳሰበ ከእዚህ በፊት መረጃ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ይህን አሳፋሪ ተግባር ማን እንደፈፀመው ለማንም ግልፅ ስለሆነ ሙስሊሙ ባልሰራው ተግባር ተጎጂ እንዳይሆን የበኩላችንን ጥንቃቄ እንድናደርግ እናስገነዝባለን!

‹قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا
በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡» (ኢስራዕ ፤ 81)
source:-

No comments:

Post a Comment