No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 26 January 2013

ለላሊበላስ ማን ይድረስ?

የላሊበላ ውቅር አብያተ ከርስቲያናት የመፍረስ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ መነገር የጀመረው ዛሬ አይደለም። ቢያንስ ላለፉት አስራ ሁለት ዓመታት ያካባቢው ነዋሪዎች፣ በወፍ ዘራሽ ወደዚያ ያቀኑ ጋዜጠኞችና ለልቦናቸው የቀረቡ የገዳማቱ አገልጋዮች አስጠንቅቀዋል። ማስጠንቀቂያው ግዙፍና ዕረፍት የሚከለክል ቢሆንም ተግቶ ምላሽ የሰጠ አካል ባለመኖሩ፣ ጉዳዩን በመያዝ የተከራከረና ገዢውን ፓርቲ ያስጨነቀ የህዝብና የቅርስ ጠበቃ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ባለመገኘቱ “ለላሊበላ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች አንድ ናቸው” የሚል አስተያየት እየሰጡ ነው።

Friday 25 January 2013

Open letter to Confederation of African Football (CAF)

by Kiflu Hussain
I don’t know whether CAF has a regulation that prohibits making a political statement during African Cup of Nations (AFCON) football matches. I know it’s not allowed making a political statement in Olympics.
A case in point; in 2012 a South Korean football player who made such a statement against Japan over a border dispute by revealing a symbol he hid under his official shirt after scoring a goal was banned from the medal ceremony.

Thursday 24 January 2013

ልማታዊው ኪስ አውላቂ (ክንፉ አሰፋ)

ማስታወሻ፡  ባለፉት ጊዚያት በጫጫርኳቸው አጫጭር ጽሁፎቼ፤ ገንቢ ትችቶች ለላካችሁልኝ አንባብያን ሁሉ ምስጋናዬ ላቀ ነው። በአንጻሩ አፍራሽ ትችቶች በስማችሁ ጽፋችሁ የላካችሁልኝ ወገኖችንም አደንቃለሁ። ነገር ግን በብእር ስም ራሳችሁን በመደበቅ፤ ነውር እና አሳፋሪ የሆነ የፈጠራ ስራ ለምትሰሩ ደግሞ፡ ልቦና ይስጣችሁ ከማለት ውጭ የምለው  ‘ህዳሴው ቦንድ’ ግዢ ግርግር ሞቅ ብሎ በነበረበት ሰሞን ይነገር የነበረ አነድ ቀልድ አለ። የ‘ማረሚያ’ ቤት ፖሊሶች እና ታጋዮች 500 ብር በሰረቀ ሌባ ላይ ውይይት ያደርሉ። ተከሳሹ ብሩን ያላግባብ ይስረቅ እንጂ በገንዘቡ የህዳሴውን ቦንድ መግዛቱ ነው ጉዳዩን ለውይይት የዳረገው።  ይህ ሌባ መታሰር የለበትም የሚሉት ታጋዮች፡ ለፖሊሶቹ ያቀረቡት መከራከሪያ ነጥብ ልማታዊ ሃሳብ ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት፡ ‘ይህ ልማታዊ ኪስ አውላቂ ነው። እንዲያውም እንደዚህ አይነቶቹን ሌቦች የበለጠ እንዲሰሩ ማበረታታት ነው ያለብን።…’  ሁሉም በዚህ ሃሳብ ተስማሙና ሌባውን በያዘው ልማታዊ ተግባር የበለጠ እንዲሰራበት መክረው ለቀቁት።

Wednesday 23 January 2013

ዳዊት ከበደ እየበራ ነው እየጠፋ!? ከአቤ ቶኪቻው

የቀድሞው አለቃዬ እና የአሁን ወዳጄ ዳዊት ከበደ ሰሞኑን አወዛጋቢ ሆኖ ሰንብቷል። ለምን አወዛገበ? ምን አወዛገበ? እንዴት አወዛገበ? ማንን አወዛገበ…? ወዘተ የሚሉትን ሁሉንም ዘርዝሬ መዝለቄን እንጃ ግን እስቲ ትንሽ ነካ ነካ ላድረግማ፤
ባለፈው ጊዜ ዳዊት ከበደ ስለ ኢትዮ ሚዲያው አበርሃ የፃፈውን ወቀሳ በአውራምባ ታይምስ ድረ ገፅ ላይ አንብቤ ነበር። በኢትዮ ሚዲያ ላይ ስለ ዳዊት ከበደ የወጣውን ፅሁፍ አላየሁትም። የዳዊትን ምላሽ ግን አልወደድኩትም። ይህንን ለዳዊትም ነግሬዋለሁ። ሳስበው ዳዊት ያንን ፅሁፍ ሲፅፍ ክፉኛ ተበሳጭቶ እንደሆነ እገምታለሁ። ምን መገመት ብቻ በደንብ አውቂያለሁ እንጂ…
በተናደድን ጊዜ የምንወስናቸው ውሳኔዎች ብዙ ግዜ መልከ መልካም አይሆኑም። ወይም ውጤታቸው አያምርም። በብስጭት ሲወሰን እንኳን ሌላው ቀርቶ ራስን ማጥፋት እንኳ አይሳካም። ለሁሉም ነገር ስክነት ያስፈልጋል። በስክነት ውስጥ ብስለት አለ። በጥድፊያ ውስጥ ግን ያለው ጥፊያ ነው መጥፋት እና ማጥፋት።
ይህ በሆነ በስንተኛው ቀን እንደሆነ እንጃ እንደ ገጠር ቤተክርስቲያን ሰንበት ሰንበት ብቻ የሚከፈተው አባመላ የተባለ ፓልቶክ ሩም ዳዊት ከበደን ይዞ ባለፈው ቅዳሜ ብቅ ብሎ ነበር። ወዳጄ ዳዊት ከበደ ወደዚህ ፓልቶክ ሩም ለቃለ ምልልስ ሲሄድ በፊት ከነበረው አቋሙ በአንዳች ምክንያት ለውጥ እንዳደረገ ተገንዝቤ ነበር።

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢአቸውን ለቀው ወጡ


ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ስር በሚገኙት በፔዳ ፣ ፖሊ፣ ይባብና  ዘንዘልማ  ካምፓሶች ይማሩ የነበሩ ከ95 በመቶ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢአቸውን ለቀው መውጣታቸውን የተወሰኑትም ወደ መጡበት አካባቢ መመለሳቸውን  ተማሪዎች ገለጹ። ተማሪዎቹ ግቢአቸውን በመልቀቅ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የወሰኑት ከሶስት ሳምንት በፊት የግቢው አስተዳዳሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚደረግ ጸሎት እንዲቆም፣ ሴቶች ጂሃብም ኒቃምብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን ተከትሎ ነው።

Monday 21 January 2013

መነቀል ያለበት ስር የሰደደ የወያኔ ዘረኝነት

የግንቦት 7 ንቅናቄ
ዘረኛዉ የወያኔ ስርአት የኢትዮጵያን ህዝብ ለጥቂት አመታት ኢትዮጵያዊያንን ባሰረና በገደለ ቁጥር ገንዘብ የሚሰጡትን አለም አቀፍ ድርጅቶችና አርዳታ ሰጪ አገሮች ደግሞ 21 አመት ሙሉ ካታለለበት መንገድ አንዱ የፌዴራል ስርአት መስርቼ ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር አደረኳት የሚለዉ ባዶ አባባሉ ነዉ። ይህንን ተጋልጦ እርቃኑን የቀረ አባባል የኢትዮጵያ ህዝብ ተገንዝቦ ወያኔን መታገል ከጀመረ ቆይቷል፤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ ለጋሾችም ቢሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ግድ የሌለዉ ወያኔ ወጣቶቻችንን እየገበረ ጥቅማቸዉን ስለሚያስከብርላቸዉ ነዉ እንጂ ወያኔ እንኳን እየደገፉ እርዳታ የሚሰጡት በአንድ ተርታም አብረዉ ለመቀመጥ የማይመች የእኩዮች ስብስብ እንደሆነ ካወቁ ቆይቷል።
ህወሀት በፌዴራል ስርአቱ ዉስጥ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ በሚጠራዉ ፓርላማ ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ 8 ብቻ ነዉ። እዚህ ፓርላማ ዉስጥ የትግራይን ህዝብ እወክላለሁ የሚለዉ ህወሀት ነዉ፤ ትግራይ ደግሞ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ ክልል ናት። የተቀሩት 8 ክልሎች በዚህ የእኩልነት ምልክት በሆነዉ ፓርላማ ዉስጥ ያላቸዉ የመቀመጫ ብዛት 569 ነዉ። ሆኖም በወያኔ መንደር የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ህዝብ ሳይሆን ጠመንጃ ነዉና ወያኔ ፓርላማዉ ዉስጥ 8 ወንበር ብቻ ይዞ 569 ወንበር ያላቸዉን የኦሮሚያን፤ የአማራን፤ የደቡብ ክልልንና የተቀሩትን አምስት ክልሎች እንደ መኪና ይነዳቸዋል። የየክልሉን መሪ ይሾማል፤ ይሽራል ወይም የማይስማማዉን የክልል ባለስልጣን ያስራል። ፓርላማዉ ዉስጥ አንድ መቶ ሰባ ስምንት፤ አንድ መቶ ሰላሳ ስምንትና አንድ መቶ ሀያ ሦስት መቀመጫ ያላቸዉ የኦሮሚያ፤ የአማራና የደቡብ ክልል ፓርቲዎች በራሳቸዉ ጉልበትም ሆነ ህልዉና ስለሌላቸዉ አንዱ ከሌላዉ የበለጠ ስልጣን ወይም ሹመት ለማግኘት አንጋጥጠዉ ወደ ላይ የሚመለከቱት ህወሀትን ነዉ።
ለመሆኑ ወያኔ የፌዴራል ስርዐት መስርቼ የኢትዮጵያን ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት አረጋገጥኩ ሲል ምን ማለቱ ነዉ? እኩልነቱ የፖለቲካ ነዉ የኤኮኖሚ? ወይስ በየአመቱ ህዳር ወር ላይ የፌዴራልዝም ቀን ሲከበር እንደምናየዉ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠዉ በዘፈን ብቻ ነዉ? የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስርዐት ከላይና ከታች የሚቆጣጠረዉና ይህንኑ የፖለቲካ ስርአት የሚደግፍ የኤኮኖሚ መዋቅር ዘርግቶ የአገራችንን ኃብት የሚቦጠብጠዉ ህወሀት ብቻ ነዉና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ተረጋገጠ የሚባለዉ አባባል ከተራ የቃላት ድርደራ ዉጭ ሌላ ምንም ትርጉም የለዉም።
አፄ ቴዎድሮስን እንደ ልጅነት ሞዴሉ የሚመለከተዉ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም የመጀመሪያዉን የኢትዮጰያ ዘመናዊ ወታደራዊ እንጂኔሪንግ ተቋም ሲመሰርት ስሙን “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ ነበር የሰየመዉ። ስያሜዉ የአፄ ቴዎድሮስ ስራና ስም ህያዉ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ የተደረገ ሙከራ እንደነበር ግልጽ ነዉ። የኢትዮጵያን የቀድሞ መሪዎች በጅምላ የሚዘልፈዉ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት ከአንዲት የአገር ዉስጥ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገዉ ቃለ ምልልስ አፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ ያሰሩትን መድፍና መንግስቱ ኃ/ማሪያም “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ የሰየመዉን ወታራዊ ተቋም አስመልክቶ ሁለቱንም መሪዎች ሲያንቋሽሽ ተደምጧል። የሚገርመዉ ዛሬ ወያኔ የብረታብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺን ብሎ የሚጠራዉ ግዙፍ የሲቪልና ወታደራዊ እንዱስትሪ ተቋምና በዚህ ተቋም ዉስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ፋብሪካዎች ደርግ “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ብሎ የጀመራቸዉ የከባድ እንዱስትሪ ጅምሮች ናቸዉ። በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ “ጋፋት እንጂኔሪንግ” ስራዉን ሲጀምር የፋብሪካዉ ሀላፊዎች፤ እንጂኔሮች፤ የመምሪያ ሀላፊዎችና ቴክኒሺያኖች የስራ ዕድል የሚያኙት የትምህርት ደረጃቸዉ፤ ችሎታቸዉና የሰራ ልምዳቸዉ ብቻ እየታየ ነበር፤ ወይም ትግርኛ ስለተናገረ ስራ የሚከለከል አማርኛ፤ ኦሮምኛ ወይም ሌላ ቋንቋ ስለተናገረ አድሎ የሚደረግለት ዜጋ አልነበረም። ዛሬ ወያኔ ከደርግ ስርአት ተረክቦ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ብሎ በሰየመዉ እንዱስትሪ ዉስጥ አብዛኛዉን የሀላፊነት ቦታ የያዙ ሰዎች ለቦታዉ የበቁት በስራ ልምዳቸዉና ችሎታቸዉ ሳይሆን የተወለዱበት ዘርና የሚናገሩት ቋንቋ እየታየ ነዉ። ወታራዊዉ አምባገነን ደርግም ሆነ ወያኔ ይህንን እንዱስትሪ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ከባድ እንዱስትሪ ዘርፍ መሰረት ይሆናል የሚል ራዕይ ነበራቸዉ። ልዩነታቸዉ የእንዱስትሪዉ አስፈላጊነት ላይ ሳይሆን እንዱስትሪዉን ማን ይቆጣጠረዋል የሚለዉ ጥያቄ ላይ ነዉ። ደርግ በሱ መሪነት ለማንም ችሎታ ላለዉ ኢትዮጵያዊ የእንዱስትሪዉን በር የከፈተ ሲሆን ወያኔ ግን እንዱስትሪዉ እንዳለ በአንድ ዘር ቁጥጥር ስር እንዲገባ አድርጓል። ደርግም ወያኔም አምባገነኖች ስለሆኑ አንዱስትሪዉን ከህዝብ ቁጥጥር ዉጭ አድርገዉታል፤ ወያኔ ግን ከአምባገነንም የጎሳ አምባገነን ስለሆነ ይህንን ትልቅ እንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ በትግርኛ ተናጋሪዎች ቁጥጥር ስር አድርጎታል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባለለፉት ሦስት አመታት ይህንን ወያኔ ገነባሁ የሚለዉን የፌዴራል ስርአትና በስርአቱ ዉስጥ የተለያዪ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚጫወቱትን ሚና በመረጃ አስደግፎ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ አቅርቧል። የዛሬ ሁለት አመት ግንቦት ሰባት በኢትዮጵያ መላከያ ሰራዊት ዉስጥ የተዘረጋዉን የወያኔ የዘረኝነት መረብ ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮቴሌኮምን የዘረኝነት አደረጃጀት በመረጃ በማስደገፍ ለህዝብ ማቅረቡ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮረፓሬሺንን የዘረኝነት አደረጃጀትና በዚህ አደረጃጀት ዉስጥ ማን ምን እንደሆነ ያጣናዉን የጥናት ዉጤት በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል። ግንቦት ሰባት ሃያ አራት ሰአት ሙሉ የሚከታተሉትን የወያኔ የደህንነት ሰራተኞች ከበባ ጥሶ የወያኔን ዘረኝነት የሚያጋልጡ መረጃዎችን ከራሱ ከወያኔ ጓዳ እየጎተተ አዉጥቶ ለህዝብ የሚያቀርበዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔን ዘረኝነት አያውቀዉም በሚል አስተሳሰብ አይደለም። ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወያኔ የፈጠረዉ ከፍተኛ የመረጃ ጉድለት አለ ብሎ ያምናል፤ስለሆነም ህዝቡ የወያኔን ዘረኝነት ቢረዳም መጠኑን፤ስፋቱንና ጥልቀቱን በሚገባ ላያዉቅ ይችላል ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቀኑ ደሙን እንደ መዥገር የሚመጠዉን ወያኔን የመሰለ የጀርባ ላይ አጥንት ተሸክሞ መኖር የለበትም ብለን ስለምናምን ህዝብን ለትግል ከምናዘጋጅበትና ከምናነሳሳባቸዉ መንዶች ዉስጥ አንዱ እንደዚህ ህዝብ በገዛ አገሩ “እኩል አደረግንህ” ብለዉ በሚነግሩት ከሀዲዎች ቅኝ አገዛዝ እየተገዛ መሆኑን በማሳወቅ ነዉ።
ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዋና ዳይረክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ ፓርላማ ዉስጥ ተገኝቶ የኮርፓሬሺኑን የሁለት አመት የስራ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ኮርፓሬሺኑ የግል ባለኃብቶችን አያሳትፍም እንዳዉም እያቀጨጫቸዉ ነዉ፤ ለሙስና የተጋለጠ ነዉ፤ ደግሞም አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባል ነዉና ይህ አሰራር ሠራተኞችን ለማስተዳደር አስቸጋሪ አይሆንም ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዉለት ነበር። የግሉን ዘርፍ መቅጨጭ በተመለከተ ኢትዮጵያ ዉስጥ ቀድሞዉንም ቢሆን “የወያኔ ዘርፍ” እንጂ የግል ዘርፍ የሚባል ነገር የለምና ጥያቄዉ መቅረብም አልነበረበትም። ሙስናም ቢሆን የወያኔ ስርዐት ዋናዉ መገለጫ ባህሪይ ስለሆነ ወያኔ እስካልተወገደ ድረስ ሙስና “ሙስናን እናጠፋለን” ስለተባለ ብቻ የሚጠፋ ነገር አይደለም። ግንቦት ሰባትን እጅግ በጣም ያሳዘነዉና ያስገረመዉ ነገር ያንን ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት ነዉ ብሎ የሚናገርለትን ፓርላማ ያስጨነቀዉ (ተጨንቆ ከሆነ) የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር መዉደቁ ሳይሆን አብዛኛዉ የኮርፖሬሺኑ ሰራተኞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት መሆናቸዉ ነዉ። በእርግጥ የአንድ ትልቅ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች በአብዛኛዉ የጦር ሠራዊት አባላት ሲሆኑ የአሰራርና የአስተዳደር ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤ ሆኖም የሠራዊቱ ታማኝነት ለህዝብ ታዛዥነቱ ደግሞ ለህገ መንግሰስቱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህ ችግር በቀላሉ የሚወገድ ችግር ይሆን ነበር።
ginbot 7 exposing woyane 1
የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን በአምሰት አመቱ የእድገትና የትራንስፎርሜሺን ፕላን ዉስጥ የሚጫወተዉን ቁልፍ ሚና ፓርላማዉ በሚገባ የሚገነዘበዉ ይመስለናል፤ ታዲያ ይህ በአገር እድገት ዉስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወተዉ ኮርፖሬሺን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር ሲወድቅ ምነዉ የብሔረሰቦች እኩልነት ምልክት የሆነዉ ፓርላማ አፉን ዘግቶ ተመለከተ? ፓርላማዉን ይበልጥ የሚገድደዉ የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በአንድ አናሳ ብሔረሰብ ሙሉ ቁጥጥር ስር ሆኖ ሌሎቹ ብሔረሰቦች ተመልካች ሲሆኑ ነዉ ወይስ የአንድ ኮርፖሬሺን ሰራተኞች በአብዛኛዉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሲሆኑ ነዉ? ለመሆኑ የወያኔ ዘረኝነት በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን ዉስጥ ምን ያህል ዘልቆ ገብቷል? የኦሮሞ፤ የአማራ፤ የሶማሌ፤ የሲዳማና ሌሎቹም ብሔር ብሔረሰቦች በዚህ ለአገር እድገት ቁልፍ በሆነ ኮርፖሬሺን ዉስጥ የሚጫወትቱት ሚና ምን ይመስላል?
ginbot 7 exposing woyane 2
የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በአስራ አንድ መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን ያስተዳድራል፤ ይህ ሪፖርት እስከተጠናቀቀበት ቀን ድረስ ቁጥራቸዉ በዉል ተለይቶ ባይታወቅም አስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎችም እያንዳንዳቸዉ በስራቸዉ ብዙ ፋብሪካዎችንና የማምረቻ ተቋሞችን ያቀፉ ናቸዉ። የኮርፖሬሺኑን አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይረክተርነተና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ 29 የከፍተኛ አመራር አባላት አሉ። ከእነዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉስጥ 69 በመቶዉ ወይም ሃያዉ ህወሀት ሆን ብሎ ያስቀመጣቸዉ ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸዉ።በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ያላቸዉ ቦታ 31 በመቶ ወይም ከእያንዳንዳቸዉ በቅደም ተከተል ሦስትና ስድስት ሰዎች ብቻ ሲሆን ከተቀሩት አምስት ክልሎች በዚህ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የተመደበ አንድም ሰዉ የለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ እንዱስትሪ ለመገንባት በሚደረገዉ ጥረት ዉስጥ ከፍተኛዉን ሚና ይጫወታል የሚባለዉ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን በሲቪልና ወታራዊ መምሪያዎች ተከፋፍሎ የተዳራጀ ሲሆን በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎች ይገኛሉ። እነዚህን እንዱስትሪዎች በማስተዳደሩ በኩል የብሔር ብሔረሰቦችን ድርሻ ወይም ኮታ ስንመለከት ከአስራ ሦስቱ እንዱስትሪዎች ዘጠኙን የሚያስተዳድሩት የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በኮርፖሬሺኑ ዉስጥ ከፍተኛ ስልጣን ከተሰጣቸዉ የትግራይ ተወላጆች ዉስጥ እነ ብረጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘዉ የብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፖሬሺን ዋና ዳይረክተር ፤ ኮ/ል ተከስተ ኃ/ማሪያም በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮዳክሺን ግንባታ ሀላፊ ፤ ኮ/ል ፀጋሉ ኪሮስ በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ወታደራዊ ምርቶች ሀላፊ ፤ ኮ/ል ሙሉ ወ/ሰንበት በምክትል ዋና ዳይረክተር ማዕረግ የኮርፖሬት ፕሮጀክቶች አስተደዳደር ሀላፊ፤ሻምበል ካህሳይ ክሽን የምርመራና ልማት ዳይረክተርና ሻምበል ገ/ስላሴ ገ/ጊዮርጊስ የአቅም ግንባታና ስልጠና ማዕከል ዳይረክተርን የመሳሰሉ የህወሀት ታጋይ መኮንኖች ይገኙበታል።
ginbot 7 exposing woyane 3
ከትግራይ ዉጭ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች በብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን እንዱስትሪዎች ዉስጥ ከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ ባለዉ የአመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ ዕድል ያገኙ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር አራት ብቻ ነዉ። ይህ ጥናት የተጠናዉ ከ2004 እስከ 2005 ዓም ባለዉ የአንድ አመት ግዜ ዉስጥ ነዉ። በ2004 ዓም የኢትዮጵያ ህዝብ 90 ሚሊዮን አንደሚሆን የተገመተ ሲሆን ከዚህ ቁጥር ዉስጥ በትግራይ ክልል 5.4 ሚሊዮን ህዝብ በተቀሩት ስምንት ክልሎች ደጎሞ 84.6 ሚሊዮን ሀዝብ ይኖራል ተብሎ ተገምቷል። ይህ ጥናት በዋናነት የሚያመለክተዉ በዋና ዋና የሀላፊነት ቦታ የተቀመጡትን ግለሰቦችና ግለሰቦቹ የመጡበትን ብሔር ስለሆነ ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺንን የሰዉ ኃይል ምደባና የደረጃ እድገትን ጠለቅ ብለን ስንመለከት አብዛኛዎቹ እንጂኔሮችና ቴክኒሻኖች የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ፤ የደረጃ እድገትን በተመለከተም ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ሲነፃፃር በፍጥነት የደረጃ እድገት የሚያገኙት እነዚሁ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። ይህ ደግሞ በአጋጣሚ የሆነ ነገር ሳይሆን ወያኔ በረሀ ዉስጥ እያለ አቅዶት ባለፉት ሃያ አመታት በስራ ላይ ያዋለዉ የረጂም ግዜ እቅድና ዝግጅት ዉጤት ነዉ። ለምሳሌ ወያኔ ትግራይ ዉስጥ ኤም አይ ቲ ወይም የመቀሌ ቴክኖሎጂ እንስቲቲዩት ብሎ የሚጠራዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ተቀብሎ የሚያስተምረዉ የትግራይ ተወላጆችን ሲሆን ከዚህ ተቋም የሚመረቁ እንጂኔሮችና ተክኒሺያኖች ናቸዉ በኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን የሚሊታሪ ክንፍና በኢትዮቴሌኮም የስለላ ተቋሞች ዉስጥ ተመድበዉ ከፍተኛ የስለላ ስራ የሚሰሩት።
ginbot 7 movement exposing woyane 4
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝና አገር ዉስጥና በዉጭ አገር የሚገኙ ቡችሎቹ የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ድርጅቶች በተለይ በዳያስፖራ ዉስጥ የሚገኘዉን ለእናት አገሩ ተቆርቋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጅምላ “የጥላቻ ፖለቲካ አራማጆች” እያሉ ለአመታት ሲዘልፉን ኖረዋል። የፖለተካ ትግላችን አላማና ግብ ከጥላቻ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለዉ ቢሆንም – ለመሆኑ ይህንን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተና አንዱን አለቃ ሌላዉን ተላላኪ፤ አንዱን የሚሾም ሌላዉን የሚሽር፤ አንዱን አብልቶ የሚያጠግብ ሌላዉን የበይ ተመልካች የሚያደርግ፤አንዱን የአገር መሪነት ቦታ ተረካቢ ሌላዉን ኮብልስቶን ድንጋይ ጠራቢ የሚያደርግ ስርዐት የሚወድ ማን አለ? ይህንን በንጹህ ዜጎች ደም እጁ የቆሸሰና ያደፈ ዘረኛ ስርአት ዉደዱ የሚለንስ ማነዉ? በምድርም በሰማይም የከሰሩ እነ ሚሚ ስብሀቱን የመሳሰሉ የፖለቲካ ሴሰኞች ሊነግሩን እንደሚፈልጉት ትግላችን የትግራይ ወንድሞቻችንንና እቶቻችንን በመጥላት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የትግላችን ብቸኛ አላማ ከትግራይ ወንድሞቻችን ጋር ሊያጋጩን የሚሞክሩትን የህወሀት ወንጀለኞች አስወግደን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር ማድረግ ነዉ።
የግንቦት 7 ንቅናቄ

ማፈራረስ ማተራመስ ማሸበር- የወያኔ ታላቁ ራዕይ ከይኸነው አንተሁነኝ

ጥር 19 2013

“መካብ ሲያቅት ማፍረስ ሥራ ይሆናል” ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም

ወያኔ ላለፉት 21 ዓመታት የሀገራችንን ታሪክ ለማፈራረስና ለመቀየር የቻለውን ሁሉ ሞክሯል። የሕዝባችንን የአልደፈርም ባይነት ወኔ ለመስለብና ለማኮላሸት ያልቆፈረው ጉድጋድ አልነበረም። ሃይማኖታዊ ስርአታችንንና ወጋችንን ለመናድ ብዙ መንገድ በመጓዝ ደክሟል። አብሮ በመቻቻል የመኖር ወጥ ባህላችንን ለመጨፈላለቅና ለማጥፋት ሞክሯል። በኢኮኖሚ የወያኔ ጥገኛ እንድንሆንና የመብት ጥያቄ እንዳናነሳ ፀጥ ብለን እንድንገዛ ለማድረግ ሲጥር ከርሟል። ለወገናችን ጠብ ባላለው ልማት ስም ስንቶችን ከመኖሪያ ቤታቸው ከእርሻ ማሳቸው አፈናቅሏል። አሻፈረኝ ያሉትንም አስሯል ገድሏል። ራሱ የማያከብረውን የይስሙላ ህግም አስከብራለሁ እያለ የስንቶችን መብት ረግጧል። ወያኔ ከሳምንት እስከ ሳምንት ስገቴ ናቸው የሚላቸውንና ያላማሩትን ሁሉ አቅሙ እስከ ቻለ

Sunday 20 January 2013

The original Ethiopian flag arrived in Johannesburg: Excitement and jubilation…

The Horn Times News, 17 January 2013
by Getahune Bekele, Pretoria-South Africa

Excitement and jubilation as Ethiopian refugees received delivery of the original national flag.

Shock, anxiety and bewilderment griped TPLF officials at the Ethiopian embassy in Pretoria as refugees totally rejected the satanic flag of the minority junta; a symbol of the brutal internal colonization of Ethiopia.On Thursday morning the original Ethiopian flag arrived in Johannesburg directly from China, ahead of the black lions opening match against the copper