No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 6 April 2013

Hailemariam Desalegn and Shiferaw Shigute the TPLF collaborators are accountable for Ethnic Cleansing by Tedla Asfaw


On Monday April 8, 2013 Ethiopians are gathering in front of the White House like we have been doing for more than two decades. Our Voice is the Voice of the Voiceless Ethiopian people who are living in a giant jail with no freedom at all. Freedom to live shutting ones own mouth is not even allowed at present. The Ethnic Cleansing underway in Beni Shanguel Gumez in Western part of Ethiopia targeted Amharas as enemy to be removed from their farmland in thousands.
Amharas in the Southern Fiefdom are not new for such Ethnic Cleansing. Last year Amharas were kicked out of their livelihood from Gura Ferda in thousands. Their crime is looking and sounding different from Ethiopians over there.The people have been living along with their

“የሲፒጄውን ተሸላሚ” ዳዊት ከበደን መጨረሻ ማየት ናፈቀኝ ክፈሌ ስንሻው አኔሳ


ዳዊት ከበደ ያለተቀናቃኝ አውራምባ ታይምስ የተባለ ጋዜጣን ሲያስትም ቆየ። እንደ ዳዊት ለ2 አመታት ታስረው የተፈቱት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እና እስክንድር ነጋ የጋዜጣ
ህትመት ፈቃድ ተከልክለው ለእሱ  ተፈቀደ። ለምን ለእሱ ተፈቀደ ብሎ የጠየቀ አልነበረም፤ በእስር ቤት ተፈትኖ የወጣ በመሆኑ ለወያኔ ያድራል ብሎ የሚጠረጥር  ሰው አልነበረምና። ዳዊት  አውራምባን ማሳተም ቀጠለ። ጋዜጣው ጥሩ ስራ እየሰራ ባለበት ጊዜ ዋና አዘጋጁ “ልጁን አላምነውም ብሎ” ጥሎት ጠፋ። ዋና አዘጋጁ በወቅቱ ይናገር የነበረውን ማንም አላመነውም ነበር፤ ቀጥሎም ተረበኛው አቤ ቶክቾው ድርጅቱን ለቀቀ።
አውራምባም፣  ሄደች ሄደችና  ገበያዋ ሲደራ፣ መሀል መንገድ  ቀረች ቆማ ተገትራ ተባለች፤ “ጠንካራ ዘገባዎችን” ማውጣት አቆመች፣ ዜናዎቿ ሁሉ ” ጁነዲን ምሳ በላ፣ አባዱላ ውቅሮን ጎበኘ” ወዘተ ሆነ ። “ዳዊት ከበደ መፍራት ጀምሯል” ተብሎ በአዲስ አበባ መወራት ጀመረ፤ በመሀሉ ሲፒጄ የሚባል ድርጅት የአመቱ ምርጥ ሰው አድርጎ ሸለመው፤ የዳዊትም ስም እንደገና  ከፍ ከፍ አለ። ሁላችንም ዳዊት በመሸለሙ (የመጀመሪያው የሲፒጄ ኢትዮጵያዊ ተሸላሚ በመሆኑም) ደስ አለን፤ እኔ በግሌ በጣም ተደሰትኩ። ዳዊት ግን አንድ ፈተና ገጠመው- በአገር ቤት። ዳዊት ሽልማቱን ለመውሰድ እዚህ አሜሪካ ሲመጣ መቀናጣት አበዛና ስራውን ዘነጋው። በአሜሪካ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የሰጠውን ድጋፍ ሲመለከት 

Friday 5 April 2013

ኢሕአዴግና አፈና በኢትዮጵያ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም


ዳምጠው ወያኔ/ኢሕአዴግና አፈና በኢትዮጵያ

በቀልድ ልጀምር፤ አንድ ጮሌ የአስመራ ልጅ የእኔ ተማሪ ነበር፤ አንድ ጊዜ የጂኦግራፊ ክፍል ተማሪዎች አንድ ጃፓናዊ አስተማሪ ለመሸኘት ግብዣ አድርገው ነበር፤ በግብዣው ላይ የጠቀስሁት ነገረኛ የአስመራ ልጅ (የአስመራ ልጅ የምለው ላርቀው ፈልጌ እንዳይመስላችሁ፤) በአስተማሪዎች ላይ ቀልድ ያሰማ ነበረ፤ ስለኔ ሲናገር፤– መስፍን ወልደ ማርያም የቢሮውን በር ሁልጊዜ ክፍት አድርጎ የሚቀመጠው ለምንድን ነው? ይልና እሱው ሲመልስ፣ በሩን የመዝጋት ሌሎች ዘዴዎች ስላሉ ነዋ! ቀልዱ ለእኔ እንደገባኝ ፊቱን ስለሚያኮሳትር ሰዎች በሩን አልፈው እንዲገቡ አይጋብዝም ማለት ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔም እየሳቅሁ እንደተናገርሁት የሱን ፈሪነት በእኔ መልከ-ክፉነት መደበቁ ነው፤ ቀልዱን ያመጣሁበት ምክንያት ወያኔ ለነጻነት የቆመ መስሎ ለመታየት ሳንሱር የሚባለውን የሚታተሙ ጽሑፎችን በቅድሚያ የማስፈተሽ ቀንበር በሕግ አነሣ፤ ሰዎች እውነት መስሎአቸው ቅሪታቸውን እያነጠፉ ጋዜጦችና መጽሔቶችን ማሳተም ጀመሩ፤ ጋዜጦች እንደአሸን ፈሉ፤ መጻሕፍት ታተሙ፤ ጥቂት ቲያትሮችም ታዩ፤ ዘፈኖች ተመረቱ! ነገር ግን የግል ራድዮና ቴሌቪዥን እንዲሁ የብዙ ሰዎች ሕልም ሆኖ ቀረ፤ ብዙ ሰዎች ብዙ ገንዘብ ከሰሩ፡፡

ድሀ ከሆኑ አይቀርስ – ልክ እንደ አቶ መለስ

(ኤፍሬም እሸቴ – www.adebabay.com)፦ ሰሞኑን በተካሔደው የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አ በኢቲቪ የዜና ዕወጃ ላይ የቀረበው ንግግራቸው የማኅበራዊ ድረ ገጾች የመወያያም የመሳሳቂያም የመሳለቂያም ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ነበር። “#SomeoneTellAzebMesfin” በሚል “ሐሽ ታግ/ #Hashtag” (ቅምር-ቃል ልበለው?) በትዊተር ላይ ኢትዮጵያውያን የግል ሐሳባቸውን ሲሰጡበት የቆዩት የወይዘሮዋ ንግግር ያተኮረው በአቶ መለስ ደሞዝና ድህነት ላይ ነበር።
ዜብ መስፍን ያደረጉትና ያልሰማ ካለ ንግግራቸውን ቀልበጭ አድርጎ ለማቅረብ፦ “ለቤተሰቤ፣ ለግሌ ሳይል የሞተ፣ አራት ሺህ ይሁን ስድስት ሺህ ብር የወር ደሞዝ በፔይሮል የሚከፈል ብቸኛ የአገር መሪ መለስ ብቻ ነበር። የኢሕአዴግ መዋጮ ተቆርጦ በሚተርፈው ገንዘብ እንተዳደርበታለን” ወይም ተዳድረናል የሚል ነው። ወይዘሮዋ ስለ ድህነታቸው ሲናገሩ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው አይደለም። ከዚህ ቀድሞም ተመሳሳይ ሐሳብ ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በየኢንተርኔቱ ላይ ተለጥፎ ተመልክቻለኹ። ለኢትዮጵያውያን ሐሳብ መነሻ የሆነው እንግዲህ በእኔ አባባል “እኛ ድሆች ነን” የሚለው አነጋገራቸው ነው።

Land and Ethiopia’s Corruptocracy By ALEMAYEHU G MARIAM:

Professor A. P. J. Abdul Kalam, the renowned Indian scientist (“Missile Man of India”) and Eleventh President of India (2002-2007) said, “If a country is to be corruption free and become a nation of beautiful minds, I strongly feel there are three key societal members who can make a difference. They are the father, the mother and the teacher.”


Recently, the World Bank released its 448-page World Bank (WB) report, “Diagnosing Corruption in Ethiopia” with evidence galore showing that Ethiopia under the absolute dictatorship of the Meles Zenawi regime has become a full-fledged corruptocracy (a regime controlled and operated by a small clique of corrupt-to-the-core vampiric kleptocrats who cling to power to enrich themselves at public expense). Perhaps the report’s findings should not come as surprise to anyone since “power corrupts and absolute power corrupts absolutely”.

Thursday 4 April 2013

“የ መለስ ዜናዊ ሚስጥሮች …..በተስፋዬ ገ/አብ”

በየእለቱ አዳዲስ ዜናዎች እንሰማለን። ለአብነት “ስዩም መስፍን በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነ” የሚለው ተራ ዜና ነበር። “ስዩም ተወረወረ” ብለን ያመንንም ነበርን። ስዩም ሌላ ተልእኮ እንደተሰጠው ለመረዳት፣ የቻይናና የወያኔን የንግድ ስምምነቶች ማስላትና አንዳንድ አንጓዎች ብቅ እስኪሉ መጠበቅ ያስፈልግ ነበር። አባይ ፀሃዬ የስኳርና የጨው ሚኒስትር ሆኖ ሲሾም ብዙ ስላቆች አንብቤ ነበር። የአባይ ፀሃዬን አንገት የስኳር ጆንያ ውስጥ በመክተት ያላገጡ ሜዲያዎችም ነበሩ። ሆኖም የስዩምም ሆነ የአባይ ምደባዎች ቀጣዩን የወያኔ ዋና ዋና እቅዶች ጠቋሚ ነበሩ። የስዩምን ሹመት ተከትሎ፣ የወያኔ ባለስልጣናት ልጆች ለትምህርት ወደ ቻይና ተላኩ። እነዚህን ልጆች በኮሚኒስታዊ አስተሳሰብ አደራጅቶ ማዘጋጀት የሽማግሌው የትርፍ ጊዜ ተልእኮ መሆኑ እየተሰማ ነው።
ወያኔ የጦር መሳሪያ በብዛት እየገዛና እያመረተ ነው።
ጦር መሳሪያ የማከማቸቱ እውነተኛ አላማ ምን ይሆን? በአባይ ጉዳይ የግብፅን ጦር ለመመከት? ይሄ የተበላ እቁብ ሆኖአል። ትግራይን ለመገንጠል ቆርጠው ወስነው፣ በሹክሹክታ እንደሚሰማው TDF (Tigray Defense Force) የተባለውን ይፋ ያልሆነ መስሪያ ቤት በምስጢር እያደራጁ ይሆን?

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት! አቤ ቶኪቻው


መምህርት እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የአስተዳደር እና የጥበቃ ሰራተኞች ትንቂያለሽ፣ትሰደቢያለሽ እንዲሁም “የምትሰሩትን በሚዲያ እና ድረ ገፆች አጋልጣለሁ” ብለሽ ትዝቺያለሽ በሚል ክስ ቀርቦባት መጋቢት 25 /2005 ዓ.ም ቃሏን መስጠቷ ተሰማ፡፡
ጋዜጠኛይቱ ክሱን አስመልክቶ ቃሏን እንድተሰጥ የተጠየቀቸችው መጋቢት 19 /2005 ዓ.ም ምሽት ከመኝታዋ ተቀስቅሳ የነበረ ቢሆንም ከጠበቃዬ ጋር ሳልነጋገር ምንም የምሰጠው ቃል የለኝም በማለቷ እስከ መጋቢት 25 ሊዘገይላት ችሏል፡፡
ርዮት የተከሰሰችው በፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀፅ 36 መ እና ሠ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ይህ አንቀፅ “ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶች” ተብሎ የተዘረዘረ ነው፡፡
ርዮት ቅጣቱ ተግባራዊ ከተደረገባት፤

የእስክንድር ወንጀሉ መምከሩና ኣቅጣጫ ማሳየቱ ብቻ ነው ከገለታው ዘለቀ



ኣንድ ጊዜ ኣባባ ተስፋየ ከዚያ ከሚያምርባቸው የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅታቸው ጠፉብኝና ኸረ የት ገቡ? ብየ ኣንዱን ጠየኩ።
“ኣልሰማህም እንዴ ?”
በፍጹም ምን ሆኑ? ደንገጥ ብየ እንደገና ጠየኩ።
ያ ሰው እየሳቀ “ባለፈው ጊዜ ኣዲሱ ኣመት የሰላምና የእርቅ ያድርግልን ብለው በመናገራቸው የመንግስት ሰዎች ማን ሲጣላ ኣዩ? ብለው ኣባረሩዋቸው እኮ!” ሲለኝ ለደቂቃዎች እንደዚያ
በዚህ ስደነቅ ስደመም ደሞ ኣንዴ እንዲህ ሆነላችሁ። እንዲሁ ኣንድ ሻይ ቤት ተቀምጨ ወጪ ወራጁን እማትራለሁ። በመሃል ኣንድ ሰው ሳምሶናይት የሚባለውን ቦርሳ ጠልጠል ኣርጎ ገባና ወዲያ ወዲህ ካየ በሁዋላ የኔን ጠረንጴዛ ተጋርቶ ለመቀመጥ በትህትና ጠየቀኝ። ወንበሩን ሳብኩለት። እንደኔው ሻይ በሎሚ ኣዞ ቁጭ ኣለ። ጥቂት ቆየት ካለ በሁዋላ ያቺን ቦርሳውን ከፈተና ኣንዲት ጋዜጣ ኣውጥቶ ዘረጋጋና ማንበብ ጀመረ። ብዙም ሳይቆይ ሁለት ሰዎች ወደ ሻይ ቤቱ ገቡና ከኛ መቀመጫ ትይዩ ተሰየሙ። ኣንዱ የቀኝ እግሩን ቀጥ ኣርጎ ዘርግቶ ነበር የተቀመጠው። በሁዋላ ኬክ ሊመርጡ ሲነሱ

Wednesday 3 April 2013

! …. የኢህኣዴግ ኣጀንዳና የኣማራ ተወላጆች መፈናቀል …..!

 ህወሓት/ኢህኣዴግ ከሚከተለው ‘ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ’ የተሰኘ የፖለቲካ ኣቅጣጫ (እነሱ ‘ርእዮተ ዓለም’ ይሉታል) ኣንፃር ‘የቡድን መብት’ ከ’ግል መብት’ ይቀድማል። በብዱን መብት እሳቤ መሰረት (በኣንቀፅ 39 የ’እስከመገንጠል መብት’ ታግዞ) ብሄሮች በየክልላቸው ያለ ሃብት (ለምሳሌ መሬት) በዋናነት እንዲቆጣጠሩ ያስችላል።

በዚ መሰረትም ‘የሌላ’ ክልል ተወላጆች በ’ሌላ ክልል’ ... መሬት የማግኘት መብታቸው ሲነፈጉ ይታያል። የኣማራ ተወላጆች ብዙ ግዜ ኑሮኣቸው ከመሰረቱበት ቀያቸው በኃልና በግፍ ሲፈናቀሉ እያየን ነው። በቡድን መብት መሰረት የኢትዮዽያ ሕጋዊ ዜጎች በገዛ ሀገራቸው መኖርያ መሬት ሲከለከሉ ማየት እጅግ ያሳዝናል። በሌላ በኩል በስልጣን ያለ ድርጅት (የራሱን ዜጎች እያፈናቀለ) መሬ ታችን ተቀባይነት በሌለው መንገድ ለዉጭ ዜጎች ሲቸረችር ይታያል። ዜጎቻችን በገዛ መሬታቸው ባዕድ ሁነዋል ።

Tuesday 2 April 2013

የኢትዩፕያ ሙስሊም ወጣቶች ንቅናቄ ሂውማን ራይትስ ዎች ዛሬ በድጋሚ መግለጫ አወጣ

 የሙስሊሙ ማህበረሰብ አመራሮች ነጻነትን በሚነፍግ ችሎት...
እየቀረቡ ነው
‹‹መንግስት ሙስሊም መሪዎችን ከማሰርና ተቃውሞአቸውን  ከማፈን ይልቅ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር
በቀጥታ በመገናኘት ስለችግራቸው ውይይት ማድረግ ይኖርበታል››
የሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ አሕጉር ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ
ሌፍኮው ታዋቂው የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅቱ ሂውማን
ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው መግለጫ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አመራሮች ነጻነትን በሚነፍግ ችሎት እየቀረቡ
ነው አለ፡፡ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ያወጣውን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ዛሬ
ከናይሮቢ ቢሮው ባወጣው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የመረጣቸው አመራር አባላት፣ የሃይማኖት
አባቶች እና አክቲቪስቶች (አራማጆች) ከቀዳሚው የእስራቸው ጊዜ ጀምሮ ተገቢ ባልሆነ የእስረኞች አያያዝ ሲሰቃዩ

በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ አካል ነዉ! (ግንቦት 7)

መግለጫ
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
የወያኔ መሪዎች እነ መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በ1967 ዓም ለትግል ደደቢት በረሀ እንዲገቡ ያነሳሳቸዉና ያሰባሰባቸዉ በአማራዉ ህዝብ ላይ ያላቸው  ጥላቻና የበቀል ስሜት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በደልና እሮሮ አንገፍግፏቸዉ እንዳልሆነ በተለያዩ ግዜዎች ለህዝብ ይፋ የሆኑት የወያኔ  መግለጫዎችና ለረጂም ግዜ ወያኔን የመሩት መለስ ዜናዊና ስብሐት ነጋ በየአደባባዩ ላይ ያደረጓቸዉ ንግግሮች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ከወጣትነት ግዜያቸዉ ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ ጥርሳቸዉን የነከሱ የወያኔ  መስራቾች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለአማራ ህዝብ፤ ባህልና ታሪክ ያለቻዉ ጥላቻ ከተራ ጥላቻ አልፎ በተግባር አማራዉን ወደ ማጥቃት ዘመቻ አደገ እንጂ ለአንድም ቀን ቀንሶ አያውቅም።
የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ ያከበረዉ ወይም የኤኮኖሚና የፖለቲካ ጥቅሙን ያስጠበቀለት ብሔረሰብ ባይኖርም በግለሰብ ደረጃም ሆነ በቡድን የወያኔ ዘረኞች የአማራን ህዝብ ከተቀሩት ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ  ነጥለዉ ለማጥቃትና የስነ ልቦና ዘይቤውን ለመስበር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። በአጠቃላይ የወያኔ ዘረኛ ባለስልጣኖች አማራውን በተከታታይ ሲዘልፉ ቆይተዋል፤አዋርደው  አስረዋል፤ ከአገር እንዲሰደድ አድረገዋል፤ አፈናቅለዋል ገድለዋል።  ለምሳሌ ወያኔ ስልጣን በያዘባቸዉ በመጀመሪያዎቹ አምስት አመታት ዉስጥ ብቻ አሶሳ፤ በደኖና አርባጉጉ ውስጥ አማራ በመሆናቸዉ ብቻ ህጻናት፤ሴቶችና አረጋዉያን በግፍ ተገድለዋል።

Sunday 31 March 2013

የህወአት ታላላቅ የታሪክ ክህደቶች ከ“ፍኖተ ገድል” (ገብረመድህን አርአያ )

ለአነባበብ ይረዳ ዘንድ ጽሁፌን ከመጽሃፉ እያጣቀስኩ ለመልሱ ከራሴ እና አስረጅ ይሆናሉ ካልኳቸው ዋቢ ማስረጃዎች ጋር አድርጌ የራሴን እነሆ እላለሁኝ።
የታሪክ ክህደት ቁጥር 1:
ይህ ጉዳይ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የትግሪኛ ፕሮግራም ላይ አረጋዊ በርሄ እና ስብሃት ነጋ ቀርበው የተወያዩበት/የተከራከሩበት እና እና ስለ መጽሃፉ በተለይ እኛ ከአገር ውጪ ያለን ኢትዮጵያውያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማንበት ጭብጥ ነው -የአክሱም ስልጣኔ ጉዳይ።
ከመጽሃፉ እጠቅሳለሁ:-
<< በርካታ ተመራማሪዎችና ጸሃፊዎች “አክሱም አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ የአማራ ነዋሪዎች ወዳሉበት ደቡባዊ ክፍል ስለመስፋፋቷ የጽሁፍ ማስረጃዎች የሉም። እንደኢትዮጵያ(አማራ) አባባል ሳይሆን የአክሱም ታሪክ ከሁሉ በላይ የደቡብ ኤርትራና የሰሜን ትግራይ ታሪክ ስለ መሆኑን(sic) ማስረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ በተጨማሪ አማራ የአክሱም አፄአዊ ግዛት አካል የነበረ ስለመሆኑ ምንም አይነት ታሪካዊ ጥቁምታ የለም: :>>[1]
የህወሃት መሪዎች የተጠናወታቸው የዘረኝነት በሽታ እንዲሁ በመድሃኒት ወይም በጸበል የሚለቅም አይነት አይደለም። መቼም ዘረኝነት አንዴ ከጀመረ እንደካንሰር ከጀመረበት ቦታ ተወስኖ አይቀርም። እየመዘመዘ ፣ ውስጡን እየበላ መጨረሻ ላይ ታማሚውን ላይመለስ እስከ ወዲያኛው አለም ይወስደዋል። ይኸው ዘረኝነት ዛሬ በአውራጃ ደረጃ ወርዶ የአክሱማዊት መንግስት በሙሉ ትግራይም ቦታ የለውም የሚል መከራከሪያ ከነባሩ የህወሃት

wer

ayrreecgh

አዜብ መስፍንና የቼኮሌቱ ታሪከ ሰለሞን ታረቀኝ


ድሮ ነው አሉ፤ አንዲት በናዝሬት ትምህርት ቤት ትማር የነበረች ተማሪ ጥርሷን ጣፋጭ ጨርሶት ነበርና ወላጆቿ በፍጹም ቼኮላት እንዳትበላ ያስጠነቅቋታል፤ ከዚያም አንድ ቀን አንዲት ጓደኛዋ ቼኮሌት አምጥታ ኖሮ በእረፍት ሰዓታቸው ጓደኛዋ የሰጠቻትን ጥቂት ቼኮሌት ታናሽ ወንድሟ እንዳያሳብቅባት ተደብቃ ስትበላ ያ ከውካዋ ወንድሟ ድንገት ቢደርስባት እጅዋ ላይ የቀረውን በድንጋጤ ወደ አፍዋ አስግብታ ቁልቁል መስደድ፤ ወንድምየውም ቼኮሌት እንድትሰጠው ቢጠይቃት እንዳለቀባት ትነግረዋለች። እሱም ይናደድና አሳብቃለሁ ብሎ ያስፈራራታል። ከዚያም ከትምህርት ቤት ወጥተው ቤታቸው እንደደርሱ ወንድሟን ለመቅደም ብላ ማንም ሳይጠይቃት፥ እማዬ፥ እማዬ እኔ እኮ ዛሬ ቼኮሌት አልበላሁም አለች ይባላል።
የቀድሞዋ ቀዳማዊትም እንዲሁ ቀደም ቀደም ብላ ሳትጠየቅ ተክለፍልፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባሌ የ፮ ሺህ ብር የወር ደመወዝተኛ፥ ከዚህም ተቆራርጦ ፬ ሺህ ብር ያገኝ ነበር ስትል አበሰረችን። የቼኮሌቱ አይነት መሆኑ ነው።

“የኢህአዴግ እብሪትና ትዕቢት አገርንና ህዝብን የሚያጠፋ ነው”

አቶ ግርማ በቀለ 33ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ

የዛሬው እንግዳችን አቶ ግርማ በቀለ ይባላሉ ፡፡ አቶ ግርማ በቀለ በቅርቡ የትብብር ሠነድ የተፈራረሙት 33ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ እና የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት /ኦህዴህ/የተባለ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡-  ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች አሁን በምን እንቅስቃሴ ላይ ናቸው?
አቶ ግርማ፡- የፔቲሽን ፊርማው ወደ ትብብር ሠነድ ከተሸጋገረ በኃላ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ የቀጣይ 6 ወራት ተግባር እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ ትብብሩን ለሚቀጥለው 6 ወራት የሚመራ ቋሚ አስተባባሪ ኮሚቴ ለማስመረጥ በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ እስከ አሁን ድረስ ስንቀሳቀስ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡ ከውስጥም ከውጪም የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቋቋም እዚህ ደርሰናል፡፡ አሁን የደረስንበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ትብብሩ ስስ ነው፤ ትንሽ ቆይተው አለመግባብት ይፈጥራሉ፤ሁሉም አብረው አይዘልቁም የሚሉ ወገኖች አሉና እርስዎ ምን ይላሉ?
አቶ ግርማ፡- የማራቶን ውድድር አብረው የጀመሩ ሁሉ አይጨርሱም፡፡ እጅግ ውስብስብና ፈታኝ በሆነ ሠላማዊ ትግል አብሮ የጀመረ ሁሉ አብሮ ይጨርሰሳል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ትግሉ እየጠራና እየገፋ በሄደ ቁጥር እየተራገፈና እየተንጠባጠበ ሊቀር ይችላል፡፡ እስከ አሁን በይፋ ለቅቄአለሁ ብሎ በይፋ መግለጫ የሰጠ ፓርቲ ባይኖርም በተግባር ግን እስአሁን አምስት ድርጅቶች ግንኙነታቸውን አቋርጠዋል፡፡ ነገ ሌላ ሊቀጥል ይችላል፡፡ 15 ወይም 20 ፓርቲ ነጥሮ ቢወጣ አያስገርምም ቁምነገሩ ቁጥሩ ላይ አይደለም ዋናው ቁም ነገር ፓርቲዎቹ ሕዝብና አገር የሚፈልገውን ተግባር እያከናወኑ ናቸው ወይ? የሚለው ነው፡፡