No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Thursday, 4 April 2013

ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲዎች ክስ ቀረበባት! አቤ ቶኪቻው


መምህርት እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን የአስተዳደር እና የጥበቃ ሰራተኞች ትንቂያለሽ፣ትሰደቢያለሽ እንዲሁም “የምትሰሩትን በሚዲያ እና ድረ ገፆች አጋልጣለሁ” ብለሽ ትዝቺያለሽ በሚል ክስ ቀርቦባት መጋቢት 25 /2005 ዓ.ም ቃሏን መስጠቷ ተሰማ፡፡
ጋዜጠኛይቱ ክሱን አስመልክቶ ቃሏን እንድተሰጥ የተጠየቀቸችው መጋቢት 19 /2005 ዓ.ም ምሽት ከመኝታዋ ተቀስቅሳ የነበረ ቢሆንም ከጠበቃዬ ጋር ሳልነጋገር ምንም የምሰጠው ቃል የለኝም በማለቷ እስከ መጋቢት 25 ሊዘገይላት ችሏል፡፡
ርዮት የተከሰሰችው በፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀፅ 36 መ እና ሠ ላይ በተቀመጠው መሰረት ሲሆን ይህ አንቀፅ “ከባድ የዲሲፒሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ድርጊቶች” ተብሎ የተዘረዘረ ነው፡፡
ርዮት ቅጣቱ ተግባራዊ ከተደረገባት፤

ከአንድ ወር እስከ አራት ወር ለሚደርስ ጊዜ በወዳጅ ዘመዶቿ እንዳትጎበኝ፤ ደብዳቤ እንዳትልክ እና እንዳትቀበል (ይሄ እንኳ አሁንም ተግባራዊ ተደርጎባታል) የእስር ቤቱን ቤተ መጻህፍት እንዳትጠቀም፣ በእስር ቤቱ በሚደረግ የጋራ ዝግጅት እና መዝናኛ ላይ እንዳትሳተፍ እንዲሁም ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር ለሚደርስ ጊዜ ለብቻ እስር ትዳረጋለች፡፡
እንዲህ ከሆነ ደግሞ ያቺ በቃሊቲዊቹ ውቃቢ ትፈቀድ የነበረች አመክሮም ልትከለከል ነው ማለት ነው፡፡
በነገራችን ላይ ወጣቱ ፖለቲከኛ ናትናኤልም በእስር ቤቱ እየደረሰበት ያለውን አበሳ በመቃወም የርሃብ አድማ ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላትም ቅጥ ያጣውን የእስር ስርዓት ሃይ ለማለት የርሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡
ወይ ጣጣ… ብዬ የራሴን አስተያየት በአዲስ መስመር አቀርባለሁ…
እኔ የምለው ግን ኢህአዴግ ምነው እንዲህ መካሪ አጣ…? እርሱ እኛን በስንቱ መከራ እንዳልመከረን እርሱን የሚመክረው ማጣቱ የሚገርም ነው፡፡
እስቲ አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን እስሩ አንሶ አሳር የሚያበላው ምን ይሁነኝ ብሎ ነው? እንደሰማነው በርካታ የህሊና እስረኞች በታመሙ ጊዜ የሚያክሟቸው የእስር ቤቱ ሀኪሞች “መግደል ነበር አንተን” “መጨረስ ነበር አንቺን” እያሉ ያስፈራራሉ፡፡ እውነቱን ለመናገር ይሄ የመጨረሻው ዘመን ምልክት ነውና ነቅታችሁ ጠብቁ፡፡ መንግስታችን “ባትሪ ሎው” እያለ ይመስለኛል!

No comments:

Post a Comment