No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 30 March 2013

ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል! “ከሁሉም ነገር ጽድት ብለን እንታገል”

አቶ መለስ ከሞቱ ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ንግግርና መዕልክት የሚያስተላልፉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን መረጋጋት እንደማይታይባቸው ተገለጠ። አሁንም በባለቤታቸው ስምና መንፈስ ሙግትና ማብራሪያ ከማቅረብ አልተላዘቡም። ይህን የሚያደርጉት ከጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ተመልክቷል።
ሰሞኑንን በተጠናቀቀው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ መለስን አስመልክቶ ወ/ሮዋ የተናገሩት ንግግር በጭንቀት ውስጥ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የተናገሩት አብረዋቸው ባህር ዳር ስብሰባ የተቀመጡ የድርጅታቸው ኢህአዴግ “ባልደረቦቻቸው” ናቸው።
በጉባኤው ወቅት አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ የተዘጋጀው “ዝክረ – መውደስ” ታሪካዊ ሰነድ እንዲሆን ከመጽደቁ በፊት ወ/ሮ አዜብ በሰጡት አስተያየት “በፔሮል የሚከፈለው ብቸኛ መሪ መለስ ብቻ ነው” በማለት ራሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በፔሮል በሚከፈላቸው ገንዘብ ብቻ እንደማይኖሩ የሚያመላክት ንግግር አድርገዋል።

ኢህአዴግን “አድርባይ” አመራሮች አስግተውታል አባላት “አድርባይነት የመመልመያ መስፈርት ነው” አሉ!!

ኢህአዴግ አመራሮቹን “አድርባይነት የተጠናወታቸው” ሲል ፈረጀ። የከፍተኛ አመራሮች የግምገማ ውጤት የሆነውን ፍረጃ የሰሙ “የኢህአዴግ አባል ለመሆን አንዱና ዋናው መስፈርት አድርባይነት ነው” በማለት አድርባይነትን የፈጠረውና ያስፋፋው ራሱ ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት እንደሆነ አመለከቱ።
በባህር ዳሩ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የነበረ ጋዜጠኛ በምሥጢር የላከው ዜና “አድርባይነት” ኢህአዴግን በሚፈታተን ደረጃ መስፋፋቱ መገለጹ አብዛኞችን የድርጅቱን አባላትን አስገርሟል።
ኢህአዴግን የፈጠረውና ከላይ ሆኖ የሚመራው ህወሃት “ነጻ” አመለካከት የማይወድ፣ የነጻ አስተሳሰብ ባህል የሌለው፣ ራሳቸውን የቻሉ ድርጅቶችን፣ ፓርቲዎችንና ማህበራትን አጥብቆ የሚጠላ፣ ሁሉም ለሱ እያጎበደዱ በሚሰፈርላቸው ቀለብ እንዲኖሩ ሌት ከቀን የሚሰራ መሆኑ እየታወቀ ማንን? ለምንና እንዴት አድርባይ በሚል እንደሚፈርጅ አብዛኞች ግራ መጋባታቸውን የደረሰን ዜና ያመለክታል።

“እያንጓለለ” የአዜብ ኮሜዲ ከቴድሮስ ሐይሌ (TADYHA@GMAIL.COM)

“መለስ ወደዚህ ዓለም ጭንቅላቱን ይዞ ለዝህች አገር ለዚህች ምድር የሚጠቅም ሃሰብ አመነጨ ለግሌ ለቤተሰቦቼ ሳይል አንድ ቀን ለራሱ ሳይሆን መንግስት በሚሰጠው ደመወዝ በፔሮል የሚከፈል መሪ በዓለም ላይ መለስ ብቻ ነው።” አዜብ መስፍን
የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ዝናው ገኖ የነበረው የቀድሞው መንግስት ተራ ወታደር የነበረው ታምራት ገለታ የተባለ አባይ ጠንቋይ ሴት ወንዱን መሃይም ምሁሩን ብቻ ከተራው ዜጋ እስከዘመኑ ባለስልጣናት ሲያሰግድ ለቃልቻ ጣዖቱ ግብር ሲያስገባ የበረታ መንፈሳዊ ሃይል የተቀዳጀ እንደሆነ በአንድ ግዜ በተለያየ ቦታ እንደሚገለጽ ለተማጠነው ሃብት ጤና ትዳር እንደሚሰጥ በመስበክ ብዙ የዋሃንን አሳምኖ እስከ መመለክ ደርሶ የእግሩን እጣቢ እነደ ጠበል ሲያስጠጣ የነሆለሉለትን ሃብታሞች መድሃኒት በማጠጣት ገድሎ ሃብታቸውን የወረሰበትን የዩንቨርስቲ ምሩቃንን ሳየቀር ሳር እያስጎዘጎዘ ቡና እያስወቀጠ ይካደም የነበረበትን ሞራል አልባ የእውነት ድራማ በፍርድ መቋጫ እስካገኘበት ድረስ ያለውን የግለሰቡን የአጭበርባሪ ጥንቆላ ተውኔት ያንድ ወቅት መነጋገሪ ሆኖ የድርጊቱ ሰለባዎችና ራሱ ወንጀል ፈጻሚው ጭምር ለፖሊስ ይሰጡ የነበረውን መረጃ በየፌስቡኩና በዩትዩብ ተለቆ ጉድ ሲባል ነበር። ይህ አባይ ጠንቋይ ታዲያ በማጭበርበር ባካበተው ሃብቱ የገነባቸውን የቢዝነስ ተቋማት የላቡ ውጤት መሆኑንና ህብረተሰቡን በመርዳት ያበረከተው በጎ አስተዋጾ የማይገባ ስም እንደተሰጠው ለመከራከር ያቀረበው እፍረት አልባ ሙግት ተገቢ በሆነ ቅጣት መደምደሙን አስተውለናል።
ይህ አባይ ጠንቋይ ቢታሰርም አምሳያዎቹ የፖለቲካ ሟርትና የሙት ራዕይ አስፈጻሚ ተንበርካኪ የወያኔ ሎሌዎች መለስ የተባለ ጣዖት አቁመው ሲበሉም ሲጠጡም ስሙን ካለነሱት የማይሆንላቸው እንደ ሃይለማርያም ደሳለኝ ያለ ነሆለል ወንጌላዊ ነኝ የሚል ወንጀለኛ ከጠንቋዩ ካዳሚዎች በባሰ አገላለጽ መንገድና እውነት መለስ ነው ሲል የሬሳ አምልኮውን የገለጠበት አጋጣሚ የዘርና

ታምራት ላይኔና አማረ (ክፍል-2) ከኢየሩሳሌም አ.

አማረ አረጋዊ በማስታወቂያ ሚ/ር የኢቲቪ ስራ አስኪያጅ ሃላፊ እያለ በጣም አፀያፊ ተግባራትን በየእለቱ ይፈፅም ነበር። እሱን ጨምሮ አራት የሕወሐት ሃላፊዎች ተመሳሳይ ወራዳ ተግባር ይፈፅሙ ነበር፤ አንዱ ዋሽንግተን የሚገኝና የፓርቲው ሰላይ ሲሆን አንዱ የሻዕቢያ ተላላኪ ሆኖዋል፤ ሌላው ሹም በርካታ ሴቶችን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ሆን ብሎ በማስያዝ አገር ቤት እንዳለ (እስከ 2000ዓ.ም) አውቃለሁ፤ አሁን ግን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም።…
በወቅቱ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ጉዳዩን ሰምተው አማረን ግምገማ ይጠራሉ፤ ቃል በቃል እገልፀዋለሁ፥ «አማረ ቢሮ ውስጥ (office sex) ትፈፅማለህ፤ ..» በማለት በማስረጃ አስደግፈው ሲነግሩት፣ የሰጠው መልስ ፥ «በረሃ አይደለም ያለሁት፤ ስራዬን እስካልበደልኩ ድረስ የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ፤ መብቴ ነው..» የሚል ነበር። በዚህም ምክንያት በታምራት ትእዛዝ አማረ ከሃላፊነት እንዲነሳ ተደረገ።.. በእርግጥ አማረ ኢቲቪ እያለ ለጋዜጠኞችና ለፕሮግራም አዘጋጆች ሙያዊ ነፃነት በመስጠት በኩል ስሙ በበጎ የመነሳቱን ያክል፣ በአንፃሩ ለዜና አንባቢነት.. ወዘተ ለመቀጠር የምትመጣ ሴት እንደግዴታ የሚቀርብላት ገላዋን

የአማረ ገመና ሲገለጥ! (ክፍል-1) ከኢየሩሳሌም አ.

አዲስ አበባ አየር ማረፊያ፣ ነሃሴ 13 ቀን 1997ዓ.ም ፣ ምሽት 2 ሰዓት…ለእረፍት መጥቶ የነበረ ጓደኛዬን ለመሸኘት በስፍራው ተገኝቻለሁ። ..እንዳጋጣሚ በቅርብ ርቀት የ<ሪፖርተር> ጋዜጣ ባለቤት አማረ አረጋዊን አየሁት፤ ወደርሱ አምርቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ < ወደ አሜሪካ ለእረፍት የላከውን ልጁን ለመቀበል እንደተገኘ > ገለፀልኝ። …ከዛም ወደ ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት በመግባት ወሬ ቀጥልን፤ በመሃከሉ አማረ ፥ « ..ሲሳይና እስክንድር የጋዜጠኝነት ካባቸውን አውልቀው ለምን በግልፅ ፖለቲከኛ አይሆኑም? » ሲል በሹፈት አይነት ጠየቀኝ። « ምን ማለት ነው?» ስል መልሼ ጠየቅኩት፤ ..« በግልፅ የሚፅፉትን አታይም እንዴ?..የቅንጅት ዋና አቀንቃኞች ሆነዋል እኮ..» ካለ በኋላ አያያዘና « ..ይህችን አገር ልደቱና ሃይሉ ሻውል እንዲመሯት ነው የሚፈልጉት?…ልደቱ ነው አገር ለመምራት የሚቀመጠው?..» ሲል ያቺ የማውቃት የአማረ ፌዝና ሹፈት ፈገግታ በስሱ እያሳየኝ፤ …በዛ ሰሞን አማረ <አቋሙን> ይፋ አውጥቶ በቅንጅትና በጋዜጦች በተለይም በኢትኦጵና ምኒልክ ጋዜጦች ላይ በየሳምንቱ ..ለገዢው ፓርቲ የወገነ የቃላት ጦርነት የገጠመበት ወቅት ነበር።

Friday 29 March 2013

ODF, a democratic alternative for Ethiopia

(OPride) After an intense week of discussions in Minneapolis, Minnesota, the activist group Oromo Dialogue Forum on Thursday announced the formation a new political party, the Oromo Democratic Front.

This came after a year long deliberations on the direction of the Oromo people’s struggle in Ethiopia, a series of media interviews, and meetings across continents.
 
Leenco Lata, an intellectual and founder of the Oromo Liberation Front (OLF), a rebel group formed in 1973 by Oromo nationalists to fight for the self-determination of the Oromo people, was elected the chairman of the new organization.

North Korea orders rockets on standby to hit US bases - state media

Pyongyang has ordered rocket units be put on standby to fire on US bases in the South Pacific. “The time has come to settle accounts with the US imperialists in view of the prevailing situation,” North Korean leader declared, according to state media.
It follows a US B-2 flyover of South Korea that saw dummy ammunition dropped as part of a joint military drill Thursday.
The North Korean leader and army marshal Kim Jong-un declared that “the revolutionary armed forces of the DPRK would react to the US nuclear blackmail with a merciless nuclear attack, and war of aggression with an all-out war of justice,” according to KCNA.
The decree placing the Strategic Rocket Force on standby was signed following an urgent meeting of the military command early Friday morning, according to North Korean media. The plan suggests

ESAT Yesamintu Engida Interview With Photo Journalist Benyam Mengesha Part


! …….. የትእምት ካፒታል ስንት ነው? ……………!

ዛሬ እሁድ መጋቢት 8 የኢህኣዴግ ኣባል ድርጅቶ ች ጉባኤያቸው እንደጀመሩ ኢቲቪ እየነገረን ነው።

በመቐለ ከተማ ‘ቀውጢ’ የተባለ የድጋፍ ሰልፍ ተጠርቶ እየተከናወነ ይገኛል። ሃይለኛ ዝግጅት ነው። በህወሓት ታሪክ ለድርጅታዊ ጉባኤ ስብሰባ ድጋፍ ለማሰባሰብ ህዝባዊ ሰልፍ ሲጠራ የኣሁኑ ለመጀመርያ ግዜ ነው። ደርግም ለሞት ሲቃረብ ሰልፍ መጥራት ኣብዝቶ ነበር ኣሉ።
...

ለፕሮግራሙ የወጣ ወጪ ስንት መሆኑ ለማወቅ ያደረኩት ጥረት ኣልተሳካም። ግን በጣም ብዙ መሆኑና ከትግራይ መንግስት ካዝና እንደሆነ ግን ኣውቄያለሁ። ፓርቲና መንግስት ኣንድ የሆነበት ሀገር፤ የግብር ከፋዮች ገንዘብ ለፓርቲ ሰልፍ ዝግጅት ሲውል ኣይገርምም!!!?

ከሰልፉ በላ ይ ይበልጥ ቀልቤን የሳበው ግን የትእምት (ትካል እግሪ ምትካል ትግራይ) ወይ EFFORT (Endowment Fund For the Rehabilitation of Tigray) ተሽከርካሪዎች በመቐለ ከተማ ያደረጉት ትእይንት (ሰልፍ) ነው። በጣም ገርሞኛል። ብዛታቸው፣ ዓይነታቸው፣ ሁለመናቸው።

ትእምት በጣም ሃብታም መሆኑ ገባኝ። ‘ታድያ ይሄን ይዘን ለምን ኣላደግንም?’ የሚል ጥያቄ ጫረብኝ። የሚገርም ነው።

ገርሞኝ ዝም ኣላልኩም። ኣንድ የትእምት ሰራተኛ የትእምት ኩባኒያዎች ካፒታል ስንት እንደሆነ ጠይቄው የሚከተለውን መረጃ ሰጥቶኛል። (ፅሑፉ የራሱ ነው)።

! …….. ወይ የመናገር ነፃነ …..ት! …….!

እንዲህም ተነስተዋል፣ “ኣብርሃ መቀሌ ዉስጥ ሁኖ የፈለገውን እየተናገረ፡ ‘ ኢትዮዽያ ዉስጥ የመናገር መብት የለም’ ይላል።”

ጥሩ የሚባል ኣስተያየት ነው። ነገር ግን የመናገር መብት ወይ ነፃነት በኣግባቡ ካለመገንዘብ የመነጨ ይመስለኛል።

(1) የመናገር መብት በፌስቡክ ብቻ መፃፍ መቻል ማለት ነው? ስለ መናገር መብት ስናገር፣ መናገር የምችልባቸው መድረኮች እንዲኖሩ እየጠየቅኩ ነው። ለምሳሌ እኔ በነፃ ሚድያ (የግል ቲቪ፣ ሬድዮ፣ ጋዜጣ፣ መፅሄት፣ ጦማርና የተለያዩ ዌብሳይቶች እንደፈለኩ መናገርና መፃፍ እችላለሁ??? እነዚህ ሁሉ የተዘጉ ኣይደሉምን??? በነፃነት እንዳንናገር ኣልታፈንም??? የግል ሚድያ ሲታፈን የመናገር መብትም ኣብሮ እየታፈነ ነው።

ስለዚ በፌስቡክ መፃፍ ስለቻልኩ የመናገር መብቴ ተከብሮልኛል ማለት ኣይቻልም። ፌስቡክ የኢትዮዽያ መንግስት የግል ስጦታ ኣይደለምና።

(2) እንበልና እኔ (በፌስቡክም በሌላም) የፈለኩትን ነገር እንድናገር ተፈቅዶልኛል። እኔ የመናገር መብት ኣለኝ ማለት ሁሉም የኔ ኣምሳያ የመናገር መብት ኣለው ማለት እንችላለን? ብዙ ዜጎች (እንኳን የመናገር መብታቸው ሊጠቀሙና) ለህይወታቸውም ፈርተው ይኖራሉ። ብዙ ጓደኞቼ ህወሓትን ባለመደገፋቸው ከስራ ተባረዋል። የፈለጉትን የተናገሩ ከገዢው ፓርቲ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል።

Wednesday 27 March 2013

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?

የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡

ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት የእስር ተግባር እውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው? አስብሎናል፡፡ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ በተደጋጋሚ ጥፋት ፈፅሟል፡፡

“ዘጠኝ ቦላሌ…” ከይኸነው አንተሁነኝ ከይኸነው አንተሁነኝ

የክህደት ቁልቁለት አሉ ታላቁ ምሁር!!! የክህደት ውርስ የበቀል ዛር እያስጎራ፣ የሚሆነውንም የማይሆነውንም እያስቀባጠረ ሃያ አንድ ዓመት እያንደረደረ ወርውሮ እዚህ ያደረሰው ሕወሃት ስለመድረሱ እንጅ ወደ ፊት ስለሚሆነው ወይም ስለሚያደርገው ከግምት በላይ የሚያውቀው ነገር ያለ አይመስልም። አውቃለሁ ብሎ ያቀዳቸው ተማከርኩ ብሎ ያወራቸው ሁሉም እንዳይሆን እንዳይሆን እየሆኑበት መሆኑ ይሰማል። ብዙ የተነገረለት ስንት የተባለለት ”የሕወሃቱ የእድገት ትራንስፎርሜሽን”ም ብዙም እንዳልጨበጠ የሚወራው ሳይሆን እየሆነ ያለው የምድሩ ላይ እውነት እያሳበቀበት ነው። ወትሮም ያልነበረው የሁለት አሃዝ ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ፉከራም ወደ ሗላ እየባረቀ ”ለነዚህ ያህል ዓመታት ሁለት አሃዝ ተከታታይ እድገት ለምን ድህነትንና ስደትን በመጠኑ እንኳ ሊቀርፍ አልቻለም?” የሚለውን የዓለም ማሕበረሰብ ጥያቄ ባልተሳከረ መልኩ ለመመለስ ለሕወሃት አስቸጋሪ ሆኖበታል። ምክንያቱም የኑሮ ውድነቱ፣ ርሃብ እና ችግር የሚያንገላታው የሕዝባችን ቁጥር፣ የተማረ የሰው ሃይል ስራ አጥነት እንደጉድ መጨመር፣ ሁሉን አቀፍ ስደት ለመናገር ከሚያስቸግር በላይ መሆን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከምንም ጊዜ በላይ ዋጋው ረክሶ የታየባቸው ዘመናት በሙሉ በሕወሃት የአገዛዝ ዘመን በተለይም ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አመጣሁ እያለ በሚለፍባቸው በነዚሁ ዓመታት ነበርና ነው። ለዚህም ይመስላል የዘንድሮው የሕወሃት የኢኮኖሚ እድገት ትንበያ ለዓመታት የሙጥኝ ያላትን ያችን ጉደኛ አስራ አንድ ቁጥር ለቆ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወዳስቀመጡት የእድገት ትንበያ አሃዝ ለመድረስ ወደ ታች የተምዘገዘገው።

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”

የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡

በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ
አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡