ቬንዙዌላዊያን የመሪያችውን መሞት እንድሰሙ ሲላቀሱ |
ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የዜና እረፍታቸው ለህዝባቸው እና ለመላው አለም ይፋ የተደረገው የቬንዙዌላው ፕሬዜዳንት ሁጎ ቻቬዝ በብዙዎች ዘንድ አስገራሚ እና አወዛጋቢ ባህሪ የተላበሱ መሪ ነበሩ፡፡ያቺ በላቲን አሜሪካ ውስጥ በተፈጥሮ ጋዝ ሃብቷ ቀዳሚ ስፍራ ያላት ቬንቩዌላን ላለፉት 14 አመታት በሶሻሊስታዊ ርእዮት አለም አካሄድ የመሯት ቻቬዝ ላለፉት ሁለት አመታት ከካንሰር ህመም ጋር ውጊያ ቢያደርጉም በተወለዱ በ58 አመታቸው የሚወዱት ህዝባቸውን እና ከበዙዎች አይምሮ የማይጠፉ አሰገራሚ ትዝታዎቻቸውን ጥለው ወደ ማይቀረው አለም ሄደዋል፡፡
ቻቬዝ በህይወት ዘመናቸው ኑሯቸውን የቀየሩላቸው በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቬንዙዊላዊያን ባለፈው አርብ እለት በተካሄደው የአስክሬን ስንብት ስነ ስርአት ላይ በመገኘት ለታላቁ መሪያቸው ያላቸውን ዘለአለማዊ ክብር እና ፍቅር ለመገለጽ አብዛኞቹ ከ26 ሰአታት በላይ ተሰልፈው ተራቸው እስኪደርስ መጠባበቅ ነበረባቸው፡፡ አነዚያ