No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday 17 May 2013

The irony of Meles Zenawi’s Foundation by Robele Ababya, 17 May 2013


USA locking horns with the monster it created?

Meles Zenawi, the tyrant finally died, Meles Zenawi Foundation
The TPLF regime was catapulted to power armed to the teeth with modern weapons of war provided by Gaddafi coupled with supply of intelligence about the military movements of the Derg regime, which the western powers wanted to revenge for its ideological leaning to the left and its anti-USA stance – all due to the political immaturity of Mengistu breaking at a public rally bottles filled with red liquid condemning imperialism. The US and UK governments in revenge to Mengistu’s bluff kept the TPLF warlords in power by direct financial and security

አጀንዳን እያስቀደሙ ማዘናጋት ከተጠያቂነት አያድንም!


አልፎ አልፎ የጉዞን ጎዳና መመርመር ከብዙ ስህተት ያድናል። ግምገማ -እንደሚሉት የ”ለምን አልታዘዝክም” -“ለምን የብዝበዛው አካል/አፋኝ አልሆነክም” ውጠራ ሳይሆን የሕዝቡን የእርምጃ መስመር በተቻለ ለመጠበቅ- ከላስፈላጊ—–ፍጆታም ለመላቀቅ የሚበጅ መሆኑን በማጤን ነው።

በቀደመ መጣጥፍ ስርአቱ አሁን ሞቷል የሚንቀሳቀሰው በበበድኑ ነው የሚል ታማኒ የሆነ ሓሳቦች ተጨብጦ ነበር። ስርአቱ በቁሙ ሙት ነው ግን ዘለቀ ስንል ሊያዘልቁት ያበቁትን ጥቂት ነጥቦች በጥቅሉ ተቀምጠውም ነበር።
አንድ ሀቅ ይፋ መውጣት አለበት ከተባለ መነገር ያለበት አብይ ጉዳይ-የሆነውስ ሆነ- ትላትናና ዛሬ የህዝቡን ትግል የሚመራው ማነ ነበር-ዛሬስ ማነው ብለን መጠየቅ የግድ ነው። እንደ አነጋገርም ስልት “እርሱ አጀንዳ አለው” “የአንተ አጀንዳ ምንድር ነው” “እርሱ የሚያራምደው የራሱን አጀንዳ ነው” ይባላል። በእርግጥም የዚህ ጥቆማ አጀንዳ “አጀንዳ” እንደመሆኑ ሁሉም የራሱ አጀንዳ አለው። የሚያራምደውም አጀንዳውን ነው። የራስን አጀንዳ የሁሉ ማድረግ ደግሞ በክፉም በደጉም አንድ እርምጃ አስቀድሞ ማስተዋልን ያመለክታ።

የሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ዝግጅት እያደረገ ነው



Ethiopian blue party, semayawi party
የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ባስተላለፈው መሰረት አመራሮቹ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑ ገለጹ።
ፓርቲው “በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ ለመፈለግ…” በሚል ባስተላለፈው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ያነሳናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ የሚፈልግ

Wednesday 15 May 2013

ከሙስናው በስተጀርባ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

በሕወሐት የተፈጠረው የቀውስ ማእበል አድማሱን እየለጠጠ መሔዱን ተከትሎ «ታማኝ» ሆነው በሙስና ሲያገለግሉ የቆዩትን ጭምር እየበላ እንደሚገኝ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በቀዳሚነት የሚያነሱት በጉምሩክ ቁልፍ ስልጣን የነበረውን የሕወሐት አባል ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስን ሲሆን እንዴትና በማን ወደስልጣን እንደመጣ እንዲሁም ምን-ምን ተግባራት ይፈፅምና ያስፈፅም እንደነበረ ምንጮቹ ሂደቱን እንደሚከተለው ይገልፁታል።
ገ/ዋህድ በ1993ዓ.ም ፓርቲው ለሁለት መሰንጠቁን ተከትሎ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ተደረገ። ከጉምሩክ ሃላፊነት በተጨማሪ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተርነት ስልጣን እንዲጨብጥ የተደረገው በአቶ መለስ በተለይ በአዜብ ይሁንታ ጭምር እንደነበረ ምንጮቹ ይጠቁማሉ። ገ/ዋህድ ለዚህ ስልጣን የበቃው ለአቶ መለስ ቡድን በከፈለው መስዋእትነት ሲሆን በክፍፍሉ ማግስት የሙስና ዘመቻ ተከፍቶ እነአባተ ኪሾና ሌሎች እስር ቤት እንዲገቡ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከመስጠት አንስቶ ራሱ ክስ አዘጋጅ፣ምስክርና ፈራጅ..በመሆን የላቀ ሚና መጫወቱን ያስታውሳሉ። በዚህ ተግባሩ የበለጠ ታማኝነቱን በማሳየቱ ከአዜብ በሚሰጠው ቀጥታ ትእዛዝ ሙስናውን ማከናወን መቀጠሉን ምንጮቹ አያያዘው ይጠቁማሉ። በ10ሺህ ቶን የሚገመት ቡና ከአዜብ በተቀበለው ትእዛዝ በህገወጥ መንገድ ከአገር ተዘርፎ የተሸጠበትና ጉዳዩም በፓርላማ ተነስቶ በጠ/ሚ/ሩ «የሌቦቹን እጅ እንቆርጣለን» የሚል አስቂኝ ምላሽ መሰጠቱን ያስታውሳሉ። በተጨማሪ በጉምሩክ ለረጅም አመት በመምሪያ ሃላፊነት ሽፋን የተቀመጠውና የቢሮውን

Tuesday 14 May 2013

አምስት:- ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም! የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዢንና ራድዮ፤ ነገረኛነትን እንዴት እንገራዋለን? ፕ/ሮ መስፍን ወልደማርያም


/ሮ መስፍን ወልደማርያም
Prof. Mesfin Woldemariamሳይንሳዊ ውይይትም ወይም ክርክር የሚመራው በሕገ-ኀልዮት ወይም በእንግሊዝኛ ‹‹ሎጂክ›› በሚባለው የአስተሳሰብ መመሪያ ነው፤ ይህንን አዚህ ለመዘርዘር ከባድ ነው፤ ግን ሁለት መሠረታዊ ቁም-ነገሮችን ማንሣት እንችላለን፤ አንደኛው የሕገ-ኀልዮት መንገድ ከዝርዝር ተነሥቶ ወደማጠቃለል የሚሄድ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከአጠቃላይ ወደዝርዝር የሚወርድ ነው፤ (የትና መቼ እንደሆነ አላስታውስም እንጂ ከዚህ በፊት በጻፍሁት ከታች-ወደላይና ከላይ-ወደታች በማለት እነዚሁኑ መንገዶች ለማስረዳት ሞክሬ ነበር፤ከታች ወደላይ ከዝርዝር መነሣቱን ሲሆን፣ ከላይ ወደታች ያልሁት ከአጠቃላይ የሚነሣውን ነው፤) በቀላል ምሳሌ ላስረዳ፤ ከበደ ሁለት ዓይኖች አሉት፤ ወርዶፋ ሁለት ዓይኖች አሉት፤ ዘነበች ሁለት ዓይኖች አሏት፤ …. እንዲህ እያልን በአካባቢያችን ያሉትን ሰዎች ሁሉ አንድ በአንድ (በዝርዝር) ከገለጽን በኋላ ሰዎች ሁሉ ሁለት ዓይኖች አሏቸው ወደሚል ትክክለኛ መደምደሚያ (ማጠቃለያ)

የሙስናው ዘመቻ ነጸብራቅ የሆነው ደብዳቤ ለግንዛቤ ! ኢየሩሳሌም አርአያ


«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤
«ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።
“ዛሬ እነዚህን ደካማ ጐኖች ተጠቅመው ለጠላት አሳልፈው ሊሰጡህ የሚፈልጉ ያውም ደግሞ የእኔ የምትላቸው ጅቦች ተነስተውብህ ይገኛሉ። ይህንን ግልፅ ለማቅድረግ አሁን በቅርብ ጊዜ በመቀሌ የድርጅቱ ማ/ኰሚቴ ስብሰባ አካሄደን ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ነው እንግዲህ ተከታዩ ነገር የተነሳው። ይኽውም፥ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ ከሚስቱ ጋርና ሌሎችም ያሉበት ይህን አሉ፤

Sunday 12 May 2013

“የትናንቱ እስር ከሙስናው ጉዳይ ይልቅ ፖለቲካዊ ድምፀቱ ነው የሚሰማኝ”

ጌታቸው፣ ከኦስሎ
ሰሞኑን ኢትዮጵያ ከነበረው ዜና ውስጥ ሕዝቡን እያነጋገረ የነበረው የዋናው ኦዲተር ሪፖርት ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት፣ የአሰራር ዝርክርክነት እና ለምን እንደተከፈሉ የማይታወቁ ክፍያዎች በመንግስት መስርያቤቶች ላይ መኖራቸውን የ 2004 ዓም የሂሳብ ምርመራ ሲያደርግ እንደደረሰበት ለምክርቤት ባቀረበው ሪፖርት መግለፁ ነበር።
መንግስት እና የመንግስት ደጋፊዎችም ጉዳዩን እንደዋዛ ለማለፍ ሲሞክሩ እና አለፍ ሲል ደግሞ ጉዳዩ ኢህአዲግን አይመለከትም የሚል ፅሁፍ በማህበራዊ ድህረ ገፆች ለማስነበብ ሲዳፈሩ አስገርመውኛል። በመሰረቱ በስልጣን ላይ ያለ ፓርቲ ማለት በእያንድንዱ የስልጣን መዋቅር ውስጥ አለ ማለት ነው። ይህ ማለት ከገንዘብ ጀምሮ ማናቸውንም የሀገሪቱን ሀብት በመሰለው መልክ ውሳኔ እየሰጠ ነው ማለት ነው። ይህ ”የመንግስት ሀ ሁ” ነው። ይህንን ሃቅ ለመግፋት ያልተፈነቀለ ድንጋይ የለም። በመሆኑም ለደረሰው የገንዘብ ብክነት የገዢው ፓርቲ አባላት እና ባለስልጣናት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠያቂ የሚሆኑባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።