No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 12 January 2013

የአበበ ገላው ጉዳይ – ክንፉ አሰፋ

የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት በተሰማ ማግስት አንድ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵአዊ ከአውሮፓ ለአበበ ገላው ስልክ ይደውልለታል። ግለሰቡ ደጋግሞ ሲደውል የአበበ የእጅ ስልክ ጠፍቶ ስለነበር ሶስት ተከታታይ የድምጽ መልእክቶችን ትቶ ነበር።
“አበበ እባክህን ባስቸኳይ መልሰህ ደውልልኝ። አንተን በተመለከት ከአገርቤት የመጣ መረጃ አለ።እባክህን መልሰህ በዚህ ቁጥር አስቸኳይ ደውልልኝ።” ይላል መልእክቱ። ደዋዩ ከልብ እንደተጨነቀ ከድምጹ መረዳት ይቻላል።
አበበም በተባለው ስልክ መልሶ ደወለ።
“ሄሎ! አበበ ገላው ነኝ::”
“ሃሎ! አበበ ገላው ነህ?”
“አዎ አበበ ነኝ፣ ማን ልበል?”
“እኔን እንኳን አታውቀኝም፣ ***** እባላለሁ። የምደውልልህ በጣም ጠቃሚ መረጃ ልነግርህ ነው። ግዜ ካለህ አሁን ማውራት እንችላለን?”
“ችግር የለም ቀጥል።”
“በረከት ስምዖን አዜብ መስፍን፣ እና ብረሃነ ገ/ክርስቶስ አንተን ለማስገደል ማቀዳቸውን ከውስጥ ሰው ተነግሮኛል። እጅግ በጣም የማምነው ከፍተኛ ስልጣን ያለው የደህንነት ሰው ነው የነገረኝ። አደራ ባስቸኳይ ንገረው ስላለኝ ነው ደጋግሜ የደወልኩት። አንተን ለማስገደል ነብሰ-ገዳዮችን ወደ አሜሪካ ልከዋልና ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርግ….”

Thursday 10 January 2013

“በህወሓት ተወርረናል!” ደቡብ ሱዳኖች ኃያልነታችን ብሔራዊ ይሁን

አዲሷ አገር ደቡብ ሱዳን እንደ መንግሥት ተመቻችታ አልቆመችም። የፋይናንስ ስርዓቱም የተረጋጋ አይደለም። የገቢና ወጪ ቁጥጥሩ ክፍተት ያለበት በመሆኑ ለሙስና የተጋለጠ ነው። የጁባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ የአገሪቱ ሃብት በግለሰቦች እጅ ነው። በተለያዩ መስኮችም የባለሙያና የአቅም ችግር አገሪቱ ምስጢርና የኔ የምትለው አስተዳደር እንዳይኖራት አድርጓታል የሚሉ በርከቶች ናቸው።
ይህንኑ ክፍተት ለመሙላት በሚል ኢህአዴግ ደቡብ ሱዳንን ከተወዳጀ ጀምሮ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። የመከላከያ መኮንኖችን አሰልጥኗል፤ የፖሊስ ኃይሉን አደራጅቷል። በአማካሪነት በተለያዩ ዘርፎች የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆ አሁንም ይህንኑ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል። የተመሰረተው ግንኙነት ወደፊትም እንዲሁ በቀላሉ ንፋስ የሚገባው አይመስልም። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ኢህአዴግ በህወሃት አማካይነት ደቡብ ሱዳንን ጠፍንጎ የያዘበት ሰንሰለት በቀላሉ ሊበጠስና ሊሸረሸር የሚችል እንዳልሆነ ይናገራሉ።

ESAT Daily News Amsterdam 09 January 2013 Ethiopia


የተቃዋሚዎቻችን አበሳ (ከፋሲል አያሌው)

ከፋሲል አያሌው
የአንድ ሃገር ህዝብ በራሱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ፣ተፈጥሮዋዊም ሆነ በሌሎች አዊዎቹ ላይ የተሰማውን፣ የታየውን፣ ቅር ያለውን፣ እንዲሁም ያደነቀውን ነገር ያለምንም ተጽዕኖና ፍራቻ መግለጽ ካልቻለ ሰው በመሆኑ ብቻ የተፈቀደለትን በነጻነት የማሰብ፣ የመጻፍና የመናገር ተፈጥሮዋዊ መብቶቹ የተነፈጉት ብቻ ሳይሆን በተለይም በዚህ በሃያ አንደኛው ክ/ዘመን የሰው ልጆች ከደረሱበት ዲሞክራሲያዊ መብቶች አንጻር ሲምዘን በከፍተኛ የነጻነት እጦት ከሚሰቃዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ እንዲመደብ ያደርገዋል:: ኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች መከበር ዙርያ (ደረጃው በተለያየ መልኩ ይገለጽ ይሆናል) ለረጅም ጊዜ ያደረገችው ሙከራና አሁን ያለችበትን የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ነጻነት ላስተዋለ ሲደረጉ የነበሩ ሙከራዎች ሁሉ በተለይም ሲፈራረቁባት የኖሩት ገዢዎቿ ሲተገብሩት የኖሩት ድንጋጌዎችና መመሪያዎች  በርግጥም ለህዝቦቿ

Tuesday 8 January 2013

ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል-የወያኔዎች ስጋት


ከይኸነው አንተሁነኝ

ጥር 8 2013
ዘመናት ይቀያየራሉ፣ ወቅቶች ይለዋወጣሉ፣ የመሸው ይነጋል የጨለመው ይበራል፣ ገናና የነበሩት ነገስታት ዛሬ የሉም የሚተማመኑበት ሃይል ጭምር ተንኮታኩቷል፣ የነበሩት እያረጁ አዲሶቹ እየተወለዱ ብርቱዎች እየደከሙ ደካማ የሚባሉትም እየጠነከሩ ቀጥለዋል። ሁሌም የለውጥ ንፋስ ባካባቢያችን ይነፍሳል። ከለውጡ ጋር ያሉ ይዘምራሉ ነፋሱ የሚገፋቸውም ያማርራሉ። ይህ የነበረ ያለና የሚኖር እውነት ነው። በፍቅር ስም የሚያጠፉ እንዳሉ ሁሉ ስለ ፍቅር ለሌሎች እራሳቸውን ቤዛ የሚያደርጉ ሽዎች ናቸው። ስለ ሀገር እያሉ ድንበርን የሚያያስደፍሩ  ሀገርን የሚቆርሱና ተስማምተው የሚያስቆርሱ የመኖራቸውን ያህል የወገን ቁስል አሟቸው መሰደብ