No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday, 5 January 2013

በኬንያ ስደተኞች ከተማ ልቀቁ ተባሉ ኢትዮጵያውያኑ እንታፈናለን ብለው ሰግተዋል

dadaab
 
ወቅቱ 2003 አጋማሽ ላይ ነው። ሁለት የኢህአዴግ ሰዎች ድንበር አቋርጠው ናይሮቢወቅቱ 2003 አጋማሽ ላይ ነው። ሁለት የኢህአዴግ ሰዎች ድንበር አቋርጠው ናይሮቢ ይገባሉ። በናይሮቢ አድርገው ወደ ሌላ አገር ለመኮብለል ጊዜያዊ ማረፊያ መጠነኛ ሆቴል ይከራዩና ለሁለት አንድ ላይ ያርፋሉ። አንደኛው ከሰዎች ጋር ቀጠሮ እንዳለው አስታውቆ ወደ ጉዳዩ ይሄዳል። ቀጠሮው ቦታ ቆይቶ ለጓደኛው ስልክ ሲደውል “እንዳትመጣ፣ ጓደኛህን ከተኛበት ገብተው የማይታወቁ ሰዎች ወስደውታል” የሚል መልዕክት ይደርሰዋል። ከዚያን ቀን ጀምሮ ስለጓደኛው ሰምቶ አያውቅም። እሱም አገር ቀይሮ በስደት በመንከራተት ላይ ይገኛል።

TPLF increasingly split in Ethiopia

Indian ocean Newsletter

Despit appearances, the Tigray peoples Liberation Front (TPLF) formerly the hard core of the EPRDF (ruling coalition), does not seem to be getting over the death of
its leader Meles Zenawi. The latters widow, Azeb Mesfin , is increasingly isolated and abandoned by her former friends. Abay Tsehaye, her late husbands advisor on security issues who became the general director of the Ethiopian sugar coorporation in 2010, talk to her on the phone. Two other TPLF leaders, the forien affairs minister Tewodros Adhanom and the deputy prime minister Debretsion Gebremicheal , harbour discreet ambitions to become prime minister instead of Hailemariam Desalegn. In the last week of December , the TPLF held a two-day long excutive comittee meeting
whose discussions were widely broadcast on television. All except for the first half day, when the debates on the delicat matters were held behind close doors, such as internal
division, anease in the army, preparation for the TPLF and

የዳዉሮ ህዝብ አመጽ እንደገና ሊያገረሽ ነው “እውነትና ፍትህ በሌለበት ሀገር ኑር አትበሉኝ!”


ረ/ሳጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ

የዳውሮ ዞን ፖሊስ ባልደረባ
(ዋካ ከስዊድን)
መግቢያ
የዳውሮ ሕዝብ የደረሰበትን የመልካም አስተዳደር እጦት፤ በአቅራቢያው ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት አለመቻል፤ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ሕዝቡ ለሚያቀርበው የመብት የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ያለመስጠት፤  በየወቅቱ በሚፈራረቁ የሥልጣን ተረኛ በሆኑት የህወሐት/ ደኢህዴን ካድሬዎች የግል ፍላጎትና ውሳኔ ብቻ የወረዳ ማዕከል እየተወሰነ ከመንደር ወደ መንደር በመዘዋወሩ የተነሳ ማሕበራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት አለመቻል አበሳጭቶት ወደ አምጽ ማምራቱን በመዘርዘር ከዚህ በፊት በሦስት ክፍሎች ያዘጋጀሁትን ጽሑፍ ማስነበቤ ይታወሳል።
አሁንም በሕወሃት/ ደህዴን ካድሬዎች ተንኳሽነት የተነሳ የሕዝቡ ቁጣ እንደገና እያገረሸ መጥቷል። እስሩ ማንገላታቱ ከሥራ ማባረሩ ተጀምሯል። የሕዝቡ ጥያቄ የሚታወቅና ግልጽ ነው። ከሚዲያና ከካድሬዎች የሚነገረውን የሀገሪቱን  የኢኮኖሚ የልማትና እድገት ፕሮፓጋንዳ ባሻገር ድርሻውን ማግኘት ቀርቶ በአይኑ ለማየት አለመቻል፤ ወጣቶች የሥራ

Thursday, 3 January 2013

የማለዳ ወግ . . . አፋጣኝ ትኩረት የሚሻ የተፈናቃይ የኮንትራት ሰራተኞች ጥሪ . . .

ነቢዩ ሲራክ
አሮጌው የፈረንጆች አመት አልፎ በአዲስ አመት ከመግባቱ አስቀድሞ በዋዜማው ያየን የሰማነው በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩት የኮንትራት ሰራተኞች ውሎ አዳር ደስ አይልም ፡፡ በያዝነው ወርማ በተለያዩ የሳውዲ ጋዜጦች ሳይቀር የተዘመተብን ይመስላል ፡፡ የኮንትራት ሰራተኞች ተከላካይ ጠበቃ አጥተው ፤ በአሰሪዎች ሲባረሩ ፤ ሲደፈሩና አደጋው በርታ ሲል ተፍተው በኢንባሲና በቆንስል መስሪያ ቤቶች ጥገኝነት ይጠይቃሉ፡፡ ግፉአን ፍትህ ተነፍጓቸው ሲንገላቱ፤ ሲያብዱ ሲታመሙና በሃይል እርምጃ ነፍሳቸው ስትጠፋ ለመክረማቸው ምስክሮች ብዙ ነን ! እርግጥ ነው ለነፍስ ግድያ ተይዘውና ተወንጅለው ዘብጥያ የወረዱ እህቶችም አሉን ፡፡
ወንጀሉና ግድያውን በምን ሰበብ አስባብ እንደፈጸሙት ግን ለእኛ የሚነግረን ፤ ለዜጎች ጠበቃ ሆኖ የሚሰማቸውና የሚከራከላቸው ያገኙ አይመስሉም፡፡ በእድሜ ያልበሰሉት እህቶች ነፍስ ለማጥፋት ያደረሳቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ሳይሆን ለመረዳት በመጠለያ ያሉ እህቶች ማነጋገር ይበቃ ይመስለኛል፡፡ እህቶች ተፈጸመብን የሚሉትን ግፍና የመደፈር ጥቃት አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ለመፈጸም የሚሰጥ ምክንያት ሊሆንና ወንጀልን መፈጸም አይገባም፡፡ ያም ሆኖ ሊገል የመጣን ገዳይ ለመከላከል አስበውትም ሆነ ሳያስቡት መግደል ራስን ከጥቃት ለመከላከል የሚደረግ እንቅስቃሴ እርምጃ መሆኑን ከህግ አንጻር የሚያስረዳ የመንግስት ተወካይ ያስፈልገናል፡፡

Tuesday, 1 January 2013

የማፍረስ አባዜ ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም


“መካብ ሲያቅት ማፍረስ ሥራ ይሆናል”
ፕ/ር መስፍን ወልደ-ማርያም
ታኅሣሥ 2005
በአለፉት ሃያ አንድ ዓመታት፣ በተለይም ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ፣ የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ልዩ መታወቂያው ያደረገው እያፈረሱ መገንባትን ነው፤ ማፍረስ ቀላል ሥራ ነው፤ ጭንቅላትም፣ ማሰብም አይጠይቅም፤ ልብም፣ ስሜትም አይጠይቅም፤ የሚጠይቀው የዝሆን አካልና ጉልበት ብቻ ነው፤ አንድ ቤተሰብ ስንት ዓመት በዚያ ቤት ውስጥ ኖረ? ጎረቤቶች ምን ዓይነት ትስስር አላቸው? በማኅበር፣ በእድር፣ በዝምድና በቤተ ክርስቲያን ወይም በቤተ መስጊድ፣ በመቃብር፣ በሥራ፣ በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሰው ኑሮ ከልደት ጀምሮ የተፈተለበትና የተደራበት ውስብስብ የኅብረተሰብ አካል መኖሪያ ነው፤ ይህንን አካል ለማፍረስ ትንሽ ጭንቅላትና ግዙፍ ጡንቻ ያለው አይቸግረውም፡፡
መኖሪያ ቤቶችን ማፍረስ፣ መቃብሮችን ማፍረስ፣ የንግድ ድርጅቶችን ማፍረስ፣ ትምህርት ቤቶችን ማፍረስ፣ … ማፍረስ… ማፍረስ… ማፍረስ! ሳያለቅሱ እያስለቀሱ ማፍረስ፤ መሬቱን ማራቆት፣ ሰዎቹን ማራቆት፤ እያፈረሱ ማራቆት፤ እያራቆቱ ማስለቀስ፤ እያስለቀሱ ማፈናቀል፤ እያፈናቀሉ መጣል፤ የሚፈርሰው ቤት ብቻ አይደለም፤ የሚራቆተው መሬት ብቻ አይደለም፤ የሚፈርሰው ሰው ነው፤

ተስፋ መቁረጥ የወለደው እርምጃ – መስጊድ ነጠቃ!


ድምፃችን ይሰማ
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች መሠረታዊ የእምነት ነፃነት መብታችን ተጥሶ ለተቃውሞ አደባባይ ከወጣን ድፍን አንድ አመት ሞላን፡፡ ይህ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን አንድ ላይ ያስተሳሰረ ተቃውሞ መነሻውም ሆነ መድረሻው የመንግስት በሐይማኖታችን ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና የህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች በይፋ መጣሳቸው ነው፡፡ አሕባሽ የተሰኘውን አንጃ ከሊባኖስ በማስመጣት በሙስሊም ዜጎች ላይ በኃይል ለመጫን የተደረገው ሙከራ ለዚህ የከፋ ድርጊት ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡
አሕባሽ በከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ታጅቦ በመንግስት ጋባዥነት ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ሊፈፅማቸው ያሰባቸው በርካታ ፕሮጀክቶች ነበሩት፡፡ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የአህባሽ የግዳጅ ጠመቃ ላይ በወጣው ባለ 15 ነጥብ የአቋም መግለጫ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በአህባሽ የመጅሊስ አስተዳደር ጥብቅ ቁጥጥር ስር እንዲውል፣ ማንኛውም የመስጂድ ኢማምም ሆነ ዳዒ ይህንን የአሕባሽን ስልጠና እንዲሳተፍ፣ የአሕባሽን ስልጠና ያልወሰደ ማንኛውም ኢማም ማሰገድ እንደማይችልና

Monday, 31 December 2012

ESAT Daliy News-Amsterdam Dec. 31 2012 Ethiopia


Happy New Year My FB Friends!!!!!Press release by Fikrie Zelekew

December 31, 2012

Before a new year is getting in, as a human being, everyone promises for him or herself to achieve successful and remarkable things in life whether it is accomplished as it is planned throughout the year or not. Of course, there are many external (social and political) obstacles which can be the bottle necks for its performance than personal or internal influence. The success is differ person to person commitments if it is not influenced by political and social constraints.

However, peoples’ (nations) like Ethiopia people who are tied under the yoke of dictatorship are completely not able to perform their wishes, dreams and plans freely and confidently. Their lives and securities are even treated in the hands of dictators blessing. Man can lose his life under his dictators’ hands or on the way to search safety or be imprisoned or disturbed by corrupted leaders. That means in such nations annual plans cannot be achieved as its plan. Even if life goes up and down, we need to avoid the external obstacles which are determined by the negative results of our dictator leaders.

Sunday, 30 December 2012

በኢሳት እርዳታ ሳጅን ሽታየ ወርቁ ራሱን ከማጥፋት ተቆጠበ

ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ክልል በዳዉሮ ዞን በሎማ ወረዳ ገሣ ከተማ ላይ ይደረግ በነበረዉና የሎማ ዲሣ ህዝብ የአዲስ ወረዳ አግባብነት ስብሰባ ላይ የግል አስያየቱን የሰጠዉ የፖሊስ ባልደረባ ሳጅን ሽታየ ወርቁ እራሱን ከምግብ እና ከውሀ ለ24 ሰዓታት ከልክሎ በወጣበት ዛፍ ላይ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ከኢሳት ጋር ተገናኝቶ አላማውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመፈለጉ የኢሳት ባልደረቦች በስልክ አግኝተው ራሱን እንዳያጠፋ በመምከራቸው፣ ከድርጊቱ ታቅቦ በፖሊስ ታጅቦ ወደ እስር ቤት ተጉዟል።
ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ ከሁለት ቀናት በፊት “ወረዳ አያስፈልም ካላችሁ ለምን ድሮ ለሲዳማ 9 ለወላይታ 5 እያለችሁ ሸንሽናችሁ ሰጣችሁ በማለት” በስብሰባ ላይ በሰጠዉ አስተያየት ምክንያት በዕለቱ ለስብሳበ የወጡ የወረዳዉ የመንግሥት ሠራተኞች የእርሱን ሀሳብ በመደገፍ ስብሰባዉን አቋርጠዉ በመዉጣታቸዉ ምክንያት ከትላንቱ ስብሰባ የወረዳዉ ፖሊስ አባላት በሙሉ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን መግለጻችን ይታወሳል፡፡