No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 7 September 2013

የቀድሞ ደህንነት ሃላፊ ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል እየተገረፈ ነው (ከኢየሩሳሌም አርአያ) የቀድሞ ሹም እየተገረፈ ነው

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ከአዲስ አበባ ፖሊስ ምንጮች አሁን በደረሰኝ መረጃ የአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ የነበረው አረመኔው ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤል በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መገረፉን አስታውቀዋል። የአዜብና መለስ ቀኝ እጅ የነበረው ይህ ጨካኝ የደህንነት ሹም በስልጣን በነበረበት ወቅት እነ ጄኔራል አሳምነውን በመደብደብ፣ አይናቸውን በቦክስ በመምታት ከፍተኛ የጭካኔ ተግባር ይፈፅም እንደነበረ ምንጮች አስታውሰዋል። በ1997-98 ዓ.ም በሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ወገኖች እንዲገደሉ፣ እንዲታሰሩና አሰቃቂ ግፍ እንዲፈፀምባቸው ያደረገው ወ/ስላሴ መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል። በርካታ ሰዎች ከመግረፍና ከማሰቃየት ባለፈ በጥይት ደብድቦ ይገድል እነደነበረ አመልክተዋል። የቤተመንግስት የጥበቃ ሃላፊ አቶ ዘርኡ መለስ አንገታቸውን በስለት በማረድ እንዲሁም የመንገድ ት/ሚኒስትሩን አቶ አየነው ቢተውልኝን በገመድ አንቆ የገደለው ወ/ስላሴ መሆኑን ከዚህ ቀደም መገለፁ ይታወሳል። ወ/ስላሴ በትላንትናው እና በዛሬው እለት ሁለት ጊዜ መገረፉን ምንጮች አረጋግጠዋል

የአብዮቱ የምፅአት ቀን ምልክቶች! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

የአብዮቱ የምፅአት ቀን ምልክቶች! (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)September 3, 2013
Journalist Temasgan Desaleg‹‹በአፍሪካ ትልቁ አምባገነን›› የሚል ተቀፅላ የተሰጣቸው የሊቢያው ኮሎኔል መሀመድ ጋዳፊ እና የግብፁ ሆስኒ ሙባረክ በህዝባዊው እምቢተኝነት ከስልጣን መነሳታቸው በመሰል አገዛዞች ስር ያደሩ ሕዝቦችን ለለውጥ ማነቃቃቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ በተለይም ከራሳቸው መንግስት ተኳርፈው አስተማማኝ የዲሞክራሲ ተቋማትን በገነቡ የምዕራብ ሀገራት በብዛት የሚኖሩ ዜጎች ላሏት ኢትዮጵያ ንቅናቄው የፈጠረው ተመሳሳይ መነሳሳት ቀላል ባለመሆኑ ኢህአዴግን ሊወጣው ከማይችለው ቅርቃር ውስጥ ከቶታል፡፡ የዚህ ተጠየቅም ቀድሞ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ ድርጅቱ ‹እሳት ማጥፊያ› ያደርጋቸው የነበሩ አጀንዳዎቹ ያለፈባቸው (Expired) መሆናቸውን ማሳየት ነው፡፡
ሰባቱ ‹‹ቀኖና››ዎች
ስርዓቱ ከሃያ ሁለት ዓመታት በላይ በስልጣን የመቆየቱ ምስጢር ከሁለት ምንጭ የሚቀዳ ነው፡፡ አንዱ የታዘዘውን ሁሉ ያለ ምንም ማንገራገር የሚፈፅመው ጠመንጃ አንጋቹ (መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ እና የደህንነት መዋቅሩ) ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ከፖለቲካው ፍልስፍና የሚወረሱ አጀንዳዎቹ ናቸው፤ ይሁንና ለጊዜው የታጠቀውን ኃይል ወደ ጎን ብለን ስርዓቱ ‹‹የፖለቲካዬ መገለጫዎች›› ብሎ እንደ ቀኖና ይዟቸው የነበሩትን ሰባት ጉዳዮች በደምሳሳው ብንቃኝ የመቃብር አፋፍ ላይ የቆመ ስርዓት ስለመሆኑ የማመላከት አቅም አላቸው ብዬ አስባለሁ፡፡