ቀስ በቀስ ደረጃ በደረጃ የሰከነ የሃሳብ እድገት፣ ብስለትና መረዳት ከዘመናት ለውጥ ጋር መሻሻልን መፍጠሩ እውነት ነው። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማኖር፣ ይልቁንም ደግሞ በነፃነት ለመኖር ከወራሪዎች ጋር በተደረገ ትግል ሁሉ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተንቀሳቅሰዋል። ለዚህ ታሪክ ሥሪት የኦሮሞ ልጆች ያልከፈሉት መስዋዕትነት አልነበረም። ኢትዮጵያን ግብርና መራሽ ኢኮኖሚ እስከዛሬ ካቆያት ደግሞ ያለ ኦሮሞ ኢትዮጵያ የለችም። የዚያኑ ያህል ኢትዮጵያ ምሉዕ የምትሆነው ከየትኛውም ዘር ይፈጠር ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ክብር፣ እኩል መብትና ነፃነት ሲኖረው ነው።
No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.
Friday, 1 February 2013
Thursday, 31 January 2013
Indian, Ethiopian activists against land grabbing meet in New Delhi
Lagos, Nigeria – The Indian Social Action Forum (INSAF) and the Oakland Institute in the US will convene a day-long summit on 6 February at the India International Centre, New Delhi, bringing together activists resisting land grabs across India and Ethiopia.
In a press statement, received here Thursday by PANA, organizers said the meeting will be a ground-breaking opportunity for dialogue between Ethiopian small farmers and land rights activists and their Indian counterparts, providing space for those directly affected by land grabs to share their experiences, suffering, and collectively strategise to challenge institutional and corporate land grabbers.
ታደሰ በዛብህ የመርካቶው አይጥ ከበልጅግ ዓሊ
ታደሰ በዛብህ በተወለደ በአስራ አንድ ዓመቱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር – መስከረም 26/1981 ራሱን በማጥፋት ከዚህ ዓለም ተለየ።
ስለ ታደሰ በዛብህ ለመጻፍ ካሰብኩ ብዙ ጊዜ ነው። ቀን ሞልቶልኝ ተሳክቶልኝ አልጻፍኩትም። ሰሞኑን ሁለት ገጠመኞቼ ታደሰን እንደገና እንዳስበው አደረጉኝ። አንደኛው በጀርመን “ራይን ላንድ ፋልዝ” በሚባለው ክፍለ ሃገር ውስጥ ፋልዝ (PHALZ) በመባል በሚታወቅ ጋዜጣ ይታተማል። ይህ ጋዜጣ በ20.01.2013 እትሙ (Gestatten: Neger) በሚል ርዕስ ስለ <<ኒግር>> (“Neger” በእንግሊዘኛ ቋንቋ ደግሞ “Nigger”)በሚመለከት የተጻፈውን ካነበብኩ በኋላ ሲሆን በሁለተኛ ደግሞ እዛው ጀርመን ውስጥ በማደጎነት የተሰጠ አንድ አፍሪካዊ ሕጻን ከተገናኘሁ በኋላ ነው።
Wednesday, 30 January 2013
“የመበስበሱ በሽታ ሁሉም ዘንድ ነው” ሻዕቢያው በረከት ህወሃትን ሊነዱት ይሆን?
የአቶ በረከት ስምዖንና የአቶ ስብሃት ነጋ የደፈጣ ውጊያ ገሃድ መውጣቱን የሚያመላክት መረጃ ይፋ መሆኑን ተከትሎ በህወሃት መንደር ውስጥ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጥሯል። ጉዳዩን የሚከታተሉ እንደሚሉት ልዩነቱን ለማርገብ በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም።
ከፍተኛ ስልጣን የያዙትንና አቶ መለስ ለመተካካት ያዘጋጇቸውን አዳዲስ አመራሮች፣ በቅርቡ ደንብና ህግ በመጣስ ሹመት የሰጡዋቸውን ጨምሮ የሰራዊቱን አዛዦችና ደህንነቱን ከጎናቸው ያሳተፉት ክፍሎች የተፈጠረው ልዩነት እልባት ማግኘት ይገባዋል የሚል አቋም መያዛቸውን የሚጠቁሙ ክፍሎች እነማን ተለይተው እንደሚመቱ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑንን ይገልጻሉ።
“ፓርቲያችን ከእንጥሉ በስብሷል” በማለት ከዛሬ አስራአንድ ዓመት በፊት በአገር ክህደት ሊያስወግዷቸው የተነሱትን ጓዶቻቸውን የረቱት መለስ
Tuesday, 29 January 2013
ሒትለርና አይሁድ፤ መለስ ስብሀትና አማራ ከሉሉ ከበደ
ውድ አንባቢያን “ዘራፊ ሚሊየነሮች” ለሚለው ጽሁፍ ካደረሳችሁኝ መልሶች አጠር ያለውን አንዱን እንመልከትና ወደሚቀጥለው ጉዳይ እናመራለን።
“ወዳጄ ስለነዚህ እርጉም ሰዎች የጻፍከዉን ከማህደሬ አዉጥቼ ዛሬ አነበብኩት። እግዜር ይስጥህ። ምን እላለሁ። አፍዝ አደንግዝ እንደተደረገብን ሁሉ ዝም ብሎ ማየት ሁኗል ።ጉርሻ በሚሸጥበት አገር ሰዉ በቁንጣን አለቀ ሲሉን ለማመን ይዳዳናል። ምን አይነት እርጉም ወራዳ ትዉልድ እንደሆንን ነዉ የሚያሳየዉ። የትግሬ እና የሻቢያ ምሁራን ቀጥፈዉ ዋሽተዉ በድፍረት የሌለ ታሪክ ታሪክ አድርገዉ ተከታዮቻቸዉን እያሳመኑ ነዉ። የእኛ ምሁራን ደግሞ ሲሞዳሞዱ ጥቅም አይቅርብን ብለዉ ሲልከሰከሱ ስለኢትዮጵያ ከሞላ ጎደለ የሚጽፈዉ ያዘነልን ነጭ ሁኗል። ቢያስቡት ቢያስቡት መልስ የሌለዉ ነገር ነዉ። ነገር ግን ትግሬን ምን አደረግነዉ? ትግሬ ከሌሎች ወገኖች በላይ የደረሰበት በደል ምንድነዉ? ኢትዮጵያን ሊያጠፋ የተነሳበት ምክንያት ምንድነዉ? የሚለዉ ነገር ሁልጊዜ ጥያቄ ዉስጥ ይከተኛል።
ሕወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ ከኢየሩሳሌም አርአያ
ዛሬ በመቀሌ ለአባላ ትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩበተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ» ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤
«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤
«ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤
Monday, 28 January 2013
ስልጣንና ንግድ በህውሃት መንደር ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)
አመልና ልማድ የትም ቢሆን አይለቅምና ከሃገርና ከህዝብ መዝረፍ የለመደው የወያኔ ህውሃት ቡድን ድንበር ተሻግሮ በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን አማካኝነት ያልከፈለበትን የ29ኛው የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር ማስተላለፉ ከነሱ አልፎ ቤሄራዊ ክብራችንን የሚነካ የወረደ ተግባር መሆኑ አስረጂ አያስፈልገውም፡፡ ስለሆነም በካፍ መግለጫ መሰረት የኢትዮጲያ ቴሌቪዥን በዚህ ሳይከፍል ሰርቆ ባስተላለፈው ስርጭት ላይ የሃገር ውስጥ እስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶችን እየጠራ ተጨማሪ ገቢ ማግኘቱ ሌላው አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ የኢትዮጲያ እግር ኳስ ቡድን ከ31 ዐመታት በሗላ ለዚህ መድረሱ ህዝቡን ቢያሰደስተውም ጫወታውን በቀጥታ ለማስተላለፍ ግን የወያኔ መንግስት አቅም የለኝም ማለቱ ጫወታውን በጉጉት ለሚጠባበቀው ህዝብ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ 18 ሚሊዮን ብር እንኳን በዘረፋ ለደለበ የወያኔ ቡድን ቀርቶ ስርዓቱ ላፈራቸው ህገወጥ ባለሃብቶች በጣም ቀላል እንደ ሆነ ብዙዎች ይሰማማሉ፡፡ሆኖም ምኑም ባለየለት ምክንያት ህገወጥ ስርጭት በማስተላለፍ ቤሄራዊ ክብርን ማስነካት ይቅር የማይባል በደል መሆኑን ልብ ሊባል የገባዋል፡፡
Sunday, 27 January 2013
ከአሜሪካ የሕወሓት ሰላዮች ዛቻ ከኢየሩሳሌም አርአያ
አሜሪካ የመሸጉ የሕወሐት ሰላዮች ዛቻና ማስፈራሪያ መሰንዘር ጀምረዋል። አልፈው ተርፈው «ክስ» እንመሰርታለን ብለዋል። ለማስፈራሪያቸው የሚበረግግ ባይኖርም – ነገር ግን ነፃነት ባለበት አሜሪካ ያሉ የፍትህ አካላት በብርሃነ፡ስብሃት፡ በረከት፡አዜብ አሊያም ሽመልስ….የሚሽከረከሩ መስሎዋቸው ያለሃፍረት አንደበታቸውን ሞልተው ሲደነፉና ለማሸማቀቅ ሲሞክሩ መታየታቸው …ምን ያክል የሞራል ድቀት እንደተጠናወታቸው ያሳያል። ባለፉት ወራት ከተሰነዘሩ ተራ ስድቦችና ዛቻዎች የትላንቱ ለየት የሚያደርገው ነጥብ ስላለ ነው፥ ይህችን መልክት ለመፃፍ የተገደድኩት። እነዚህ ሰዎች አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የመሸጉ የሕወሐት ሰላዮች እንደሆኑ ላሰምርበት እወዳለሁ። ከጀርባቸው ብርሃነ እንዳለ በግልፅ በአንደበታቸው አረጋግጠውልኛል። ዋናው አላማቸው ደግሞ « ሳንጋለጥ..ቀድመን እናሸማቅ፤ ..» ከሚል ከንቱ አስተሳሰባቸው የመነጨ ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)