No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday, 30 March 2013

ታምራት ላይኔና አማረ (ክፍል-2) ከኢየሩሳሌም አ.

አማረ አረጋዊ በማስታወቂያ ሚ/ር የኢቲቪ ስራ አስኪያጅ ሃላፊ እያለ በጣም አፀያፊ ተግባራትን በየእለቱ ይፈፅም ነበር። እሱን ጨምሮ አራት የሕወሐት ሃላፊዎች ተመሳሳይ ወራዳ ተግባር ይፈፅሙ ነበር፤ አንዱ ዋሽንግተን የሚገኝና የፓርቲው ሰላይ ሲሆን አንዱ የሻዕቢያ ተላላኪ ሆኖዋል፤ ሌላው ሹም በርካታ ሴቶችን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ሆን ብሎ በማስያዝ አገር ቤት እንዳለ (እስከ 2000ዓ.ም) አውቃለሁ፤ አሁን ግን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም።…
በወቅቱ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ጉዳዩን ሰምተው አማረን ግምገማ ይጠራሉ፤ ቃል በቃል እገልፀዋለሁ፥ «አማረ ቢሮ ውስጥ (office sex) ትፈፅማለህ፤ ..» በማለት በማስረጃ አስደግፈው ሲነግሩት፣ የሰጠው መልስ ፥ «በረሃ አይደለም ያለሁት፤ ስራዬን እስካልበደልኩ ድረስ የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ፤ መብቴ ነው..» የሚል ነበር። በዚህም ምክንያት በታምራት ትእዛዝ አማረ ከሃላፊነት እንዲነሳ ተደረገ።.. በእርግጥ አማረ ኢቲቪ እያለ ለጋዜጠኞችና ለፕሮግራም አዘጋጆች ሙያዊ ነፃነት በመስጠት በኩል ስሙ በበጎ የመነሳቱን ያክል፣ በአንፃሩ ለዜና አንባቢነት.. ወዘተ ለመቀጠር የምትመጣ ሴት እንደግዴታ የሚቀርብላት ገላዋን ለአማረ <ማቅረብ> ነበር። በሕዝብ የሚታወቁና የተጎበኙ በዝርዝር ማንነታቸውን መግለፅ ቢቻልም ለዛሬው ማለፍን መረጥኩ። በነገራችን ላይ አንድ ሴት በግሩፕ ጭምር ቢሮ ውስጥ ያማግጡ እንደነበር ሳልጠቁም አላልፍም።… በተጨማሪ በወቅቱ የማ/ሚ/ር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ «ዳንዲ» በሚለው መፅሃፍ እንደገለፁት «በስነምግባር ጉድለት የተገመገሙና እርምጃ የተወሰደባቸው እንዳሉ..» ጠቁመው ነበር። ያውም በጨዋ አገላለፅ!! ስም ግን አልጠቀሱም። አንዱ ግን አማረ ነበር።….
አማረ በአቶ ታምራት ውሳኔ በተላለፈበት ሰሞን እንዳጋጣሚ አቶ መለስ ለጉብኝት አውሮፓ ነበሩ። ሲመለሱ የጠየቁት «አማረ የታለ?» ብለው ነበር። የተፈጠረው ሁኔታ ተነገራቸው። አማረን አስጠርተው አነጋገሩት። ከዛም አማረ ጋዜጣ መጀመር እንደሚፈልግ ገለፀ። በሃሳቡ ተስማሙ። ጋዜጣው «እንደ መነፅር ሆኖ መንግስትን፣ፓርቲውን..» ማገልገል እንዳለበት ተስማሙ። በአቶ መለስ ቀጭን ትእዛዝ ለ<ሪፖርተር> ወይም « ኤም.ሲ.ሲ» ማስጀመሪያ አንድ ሚሊዮን ብር (በወቅቱ ምንዛሬ ከሁለት መቶ ሺህ የሚበልጥ ዶላር) እንዲፈቀድለት አደረጉ። ለገንዘቡ መፈቀድ የተሰጠው ሽፋን ወይም ምክንያት < የግልጋሎት ዘመን > የሚል ነበር። በአንፃሩ የእርሱን ሁለት ወንድሞች ጨምሮ 36ሺህ የፓርቲው ታጋዮች በመለስ ዜናዊ « ጓሓፍ » ወይም <ቁሻሻ> ተብለው ጎዳና በጅምላ የተጣሉት አንዳች ሳንቲም ሳይሰጣቸው ነበር። የትና ለማን ነው አማረ ያገለገለው?..ስንት አመት?..ሴቶች እህቶቻችን <ገላ> ላይ እንዳሻው <ስለተገለገለ> ?…የሚሉ አስገራሚ ጥያቄዎች መነሳታቸው ግድ ነው።
ያም ሆነ ይህ አማረ ከመለስ በተበጀለት የህዝብ ገንዘብ ..በግል ፕሬስ ሽፋን የሚነግድበትን <ጋዜጣ> ጀመረ። እንደተባለው <መነፅር> ሆኖ ቀጠለ። የአየር መንገድ ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አህመድ ቀሎ ከሃላፊነት ሲነሱ በ<ጦቢያ> ጋዜጣ ላይ በወቅቱ በሰጡት መግለጫ « እኔን ያባረረኝ መንግስት ሳይሆን.. ለመንግስት መስተዋት ሆኖ በሚያገለግለው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው» ብለው ነበር።…አማረ ሲበዛ ቂመኛ ሰው ነው፤ ታምራት ላይኔን እስኪበቃው በጋዜጣው ተበቅሏቸዋል። ከታሰሩ በኋላ ፥ < ከመኖሪያ ቤታቸው ቁምሳጥን ውስጥ የተገኘ የፍቅር ደብዳቤ…» እያለ በየሳምንቱ ዘምቶባቸዋል።
(ይቀጥላል)
sorce,,http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6787

No comments:

Post a Comment