No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday, 2 April 2013

የኢትዩፕያ ሙስሊም ወጣቶች ንቅናቄ ሂውማን ራይትስ ዎች ዛሬ በድጋሚ መግለጫ አወጣ

 የሙስሊሙ ማህበረሰብ አመራሮች ነጻነትን በሚነፍግ ችሎት...
እየቀረቡ ነው
‹‹መንግስት ሙስሊም መሪዎችን ከማሰርና ተቃውሞአቸውን  ከማፈን ይልቅ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር
በቀጥታ በመገናኘት ስለችግራቸው ውይይት ማድረግ ይኖርበታል››
የሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ አሕጉር ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ
ሌፍኮው ታዋቂው የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅቱ ሂውማን
ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው መግለጫ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አመራሮች ነጻነትን በሚነፍግ ችሎት እየቀረቡ
ነው አለ፡፡ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ያወጣውን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ዛሬ
ከናይሮቢ ቢሮው ባወጣው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የመረጣቸው አመራር አባላት፣ የሃይማኖት
አባቶች እና አክቲቪስቶች (አራማጆች) ከቀዳሚው የእስራቸው ጊዜ ጀምሮ ተገቢ ባልሆነ የእስረኞች አያያዝ ሲሰቃዩ

እንደቆዩና የእስረኞች ግርፋትና ቶርች በስፋት እንደሚፈጸምበት በሚታመነው ማእከላዊ እስረ ቤት ያለ ምንም ክስ ለአራት
ወራት መቆየታቸውን ገልቷል፡፡ እስረኞችም በወህኒ ቤት ስቃይ ይደርስባቸው እንደነበርና ይህን ለፍርድ ቤት
ቢያሳውቁም መፍትሄ እንዳልተሰጣቸው አትቷል፡፡ በተጨማሪም ሪፖርቱ ታሳሪዎች ከጠበቆቻቸው
እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ መነፈጉንና ከውሳኔ በፊትም ነጻ የመባል መብታቸው እንደተገፈፈባቸው
በማንሳት በተለይም መንግስት ‹‹ጂሀዳዊ ሀረካት›› የተሰኘውን ጸብ አጫሪ ፊልም
ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ ለእይታ በማቅረብና የሙስሊሙን ማህበረሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባlaትን
ከታጣቂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አድርጎ በማቅረብ ወንጅሏቸዋል ብሏል፡፡ በፊልሙ የኮሚቴ አባላት
አቡበከር አህመድ፣ ካሚል ሸምሱ፣ አህመድ ሙስጠፋ እና ያሲን ኑሩ እንዲሁም አክቲቪስት ኑሩ ቱርኪ ከችሎት በፊት
በተቀረጹት ቪዲዮ ለእይታ መቅረባቸውን አስታውሷል፡፡ እስረኞችን በዚህ መልኩ ክፍርድ በፊት ወንጀለኛ ማስባልና
ታሳሪዎችን ማሸማቀቅ መንግስት በሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተደጋግሞ የሚስተዋልም ነው ብሏል፡፡ የችሎት
ሂደቱ ከተጀመረ በኋላም ፍ.ቤቱ የችሎት እድምተኞች በተለይም ዲፕሎማቶች፣ ጋዜጠኞችና ቤተሰቦች በፍ/ቤት
እንዳይገኙ በመከልከል ችሎቱ በዝግ እንዲደረግ መወሰኑንም አስታውሷል፡፡ የሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ
አሕጉር ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው እንደሚሉት መንግስት የሙስሊም መሪዎችን ጉዳይ እየያዘ ያለበት
መንገድ ክሱ ፖለቲካዊ መነሻ እንዳለው ፍንጭ ሰጪ ይላሉ፡፡ በሀምሌ 2004 የተነሳውን ግርግር ተከትሎ
የታሰሩት የሙስሊሙ አመራሮችን ጨምሮ በወቅቱ ወደ አንድ ሺ የሚሆኑ ንጹሀን ሙስሊሞች ተይዘው እንደነበር
የገለጸው ይኸው ሪፖርት በእስሩ እና በእርምጃው የሚዲያ ባለሞያዎች እንዲሁም ጉዳዩን ለመዘገብ ጥረት ያደረጉ
ጋዜጠኞችም ሰለባዎች መሆናቸውን አስገንዝቧል፡፡ ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸውና ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ ለዚህ ተጠቃሽ ተደርገው
የተቀመጡ ሲሆን ሁለት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም የክሱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ የሙስሊሙን ማህበረሰብ መነሻ
የመብት ጥያቄዎች ተንተርሶ የተጀመሩ የአርብ አርብ ተቃውሞዎች በመላ አገሪቱ መቀጠላቸውንና በዚህም ሰበብ የሚታሰሩ ዜጎች
ቁጥር ማሻቀቡ በሪፖርቱ ተዳሷል፡፡ የሙስሊሙ አመራር አባላት የተከሰሱት በአዲሱ የጸረ ሽብር
አዋጅ መሆኑና ይህ አዋጅ የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖችን ሁሉ ለመወንጀያነት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን
ያስታወሰው ሪፖርቱ መብት የሚጠይቁ ድምጾችን በሁሉም አቅጣጫ ዝም ለማስባል ህጉ በስፋት ጥቅም ላይ እንደሚውል
በብዙ ምሳሌዎች አስረድቷል፡፡ ሚዲያዎችም በዚህ ክስ ሰለባ እየሆኑ ነው፡፡ ሌስሊ ሌፍኮው ‹‹መንግስት የእምነት እና
የመናገር ነጻነታቸውን ለመጠበቅ ጥረት እያደረጉ ያሉ ሰዎችን ነው እየከሰሰ ያለው›› ይላሉ፡፡ በእኛ ኮሚቴ ጠበቆች
ሕገ መንግስቱን ይጻረራል ተብሎ መቃወሚያ የቀረበበት የጸረ ሽብር ሕጉ በዚህ ሪፖርት እንደተገለጸውም የተለያዩ የሰብአዊ
መብት ድርጅቶችና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ቢሮ አዋጁን አስመልክቶ ጥያቄ ሲያነሱ
መቆየታቸውን አስታውሷል፡፡ ታሳሪዎች ያለ ክስ ለአራት ወራት እነዲታሰሩ የሚያስገድደውን የአዋጁ አንቀጽ ምሳሌ
በማድረግም በአለም ላይ ካሉ የጸረ ሽብር አዋጆች ረጅሙ ይለዋል፡፡ በሪፖርቱ መደምደሚያ ሌስሊ ሌፍኮው መንግስት በሰላም
ድምጻቸውን የሚያሰሙ ዜጎችን እንዲሁም ተቺ ጋዜጠኞችን ከማሰር ይልቅ ይህን የጸረ ሽብር ህግ እንደአዲስ ማሻሻልና
ፖለቲካዊ መነሻ ያላቸውን ችሎቶች ማስስቆም ይገባል ብለዋል፡፡ ‹‹መንግስት ሙስሊም መሪዎችን ከማሰርና
ተቃውሞአቸውን ከማፈን ይልቅ ከሙስሊሙ ህብረተሰብ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ስለችግራቸው ውይይት ማድረግ ይኖርበታል››
በሚልም ሀሳባቸውን ደምድመዋል፡፡ እኛም እንላለን የመብት ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰር፣ መደብደብ፣
መወንጀልና በመንግስት ፍ/ቤት ማቅረብ መፍትሄ አይሆንም፤ መፍትሄው ለዜጎች ጥያቄ
ተገቢውን ምላሽ መስጠት ብቻ ነው፡፡
አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment