No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Tuesday 2 July 2013

!...... ወይ የሀገር ባህል .............! Abraha Desta

'ኦሾ' የተባለው ህንዳዊ ፈላስፋ ግሪክ ሀገር ሂዶ ለማስተማር በሚዘጋጅበት ሰዓት የሀገሪቱ ዋና ዋና የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ተሰብስበው መንግስት ኦሾ የተባለውን ሰው ከሀገራቸው ባስቸኳይ እንዲያስወጣ ወተወቱ። ያቀረቡት ምክንያት "የልጆቻችን አስተሳሰብ ይቀይራል፣ ባህላችን ያበላሽብናል" የሚል ነበር። ኦሾ ከግሪክ ሀገር እንዲወጣ ታዘዘ። ኦሾ አስተያየት ሰጠ። "ግሪካውያውን ከሁለት ሺ ዓመት ቆይታም ለውጥ አላመጡም። ለሶቅራጠስ መርዝ ያጠጡበት ምክንያታቸው እስካሁን ድረስ አለ። ይሄው ለኔ ትምህርትም ተመሳሳይ ምክንያት ሰጡ" አለ።

ከሁሉም በላይ የከፋ ዕንቅፋት የሰው አስተሳሰብ ነው። አይሁዳውያን ኢየሱስ የተለየ ሓሳብ ስላራመደ ሰቀሉት። የኢየሱስ ተከታዮችም በክርስትና ስም የስንት ንፁህ ሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት ሆኑ። ዓረቦች ነብይ መሓመድን ከሀገር አባረሩ (ከባህላቸው ውጭ ስላስተማረ ነበር)። ባህል ዕዳ ነው።

ቤቲ ስለተባለች ልጅ ለመክሰስ ዓቃብያን ሕግ እንቅስቃሴ እንደጀመሩ ሰማሁ። እነዚህ ሰዎች ይህን ያህል ስራ አጥተው ነው? በኢትዮዽያ ክስ ለመመስረት የሚያስችል ብዙ የፍት ሕ ችግር የለም? ብቻ ይገርማል።

ለማንኛውም ሰሚር ዓሊ የፃፈውን ልጋብዛቹ።



ባህላዊ ዎች እንዲያነቡት የማይመከር (By Semir Ali)

ሰዉን ስለቤት ችግር ሳይሆን ስለቤቲ ጉዳይ እጅጉን እያሳሰበው ይመስላል አንድ የተረገመ ቀን ሳውና ባዝ ውስጥ ተከስቼ ሳውናውን እየሞቅን የማይወራ ወሬ የለም እና አንዱ ስለቤት ችግር አንስቶ ቢያላዝን መልስ የሚሰጠው አጥቶ ኩምሽሽ ብሎ ዝም ባለበት አንዱ ጎረምሳ "ቤቲ እኮ መግለጫ ሰጠች " ከማለቱ ስጋ እንዳገኘ ጅብ ሁሉዋም ተጠቃሚ እየተስገበገበ ወሬውን እያደነቀ እርግማኑን ማውረድ ጀመሩ ..."ደግሞ አይገርምም ኢትዮጵያውያን ፌስቡክ መጠቀም አይችሉም አለችን "...እንደዚህ አይነት ዝባዝንኬ ነገር ነው ሀሜቱ

ወይኔ ሀገራችን ..,,,
ወይኔ ባንዲራችን ..,,,,,
ወይኔ ባህላችን......
ብላችሁ አትበሉ
ቤቲ የቀመሰችውን የቀመሳችሁ ሁሉ .....

እንትና ማነሽ እንዴት ነው ግን ባህላዊ ወሲብ ህሃሐ...ከሁሉም የገረመኝ ማክሰኞ የባህል ሚኒስትሩ
ስለቤቲ መግለጫ ይሰጣሉ እያሉ ሲያወሩ ነው እንዴ መንጌም ይቅርታ መንግስታችንም ገባችበት እንዴ ? አያድርገውና የባህል ሚኒስትሩ መላገጫውን ይቅርታ መግለጫውን ከሰጡ ሱፍ ለብሰው መምጣት የለባቸውም እንደዛማ ከሆነ ማላገጫ ነው የሚሆነው ያው የባህል ልብሳችንን አርገው ጭራ ይዘው እያወዛወዙ ከማይኩ አጠገብም ጠጅ በብርሌ ቢቀመጥ አይከፋም ...,,,.,.,.እንደኢትዮጵያዊ ጀግና አባት እየፎከሩ እየሸለሉ
ተተተተ ተከብረሽ የኖርሽ በናቶቻችን ደም
የደፈረሽ የቦልት አይነቱ ይውደም
ዘራፍ ዘራፍ
ቆይ ግን ኢትዮጵያ የምትገኘው የቤቲ ጭን ውስጥ ነው እንዴ አለ አንዱ የመረረው
ሌሊሳ ግርማ ደግሞ ምን አለልኝ አዲስ አበባ ውስጥ ባህል ያለው ውድ ብር ተክፍሎባቸው የምንዝናናባቸው የባህል ምሽቶች ውስጥ ነው።

በነገራችን ላይ ግብፅ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች anti Morsi and anti Muslim brotherhood party የተቃውሞ ስልፍ እያደረጉ ነው ወታደሩም ለፕሬዝዳንቱ በ48 ሰአት ውስጥ ለህዝቡ መልስ ካልሰጡ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎዋል ለነገሩ ምን አስቀናኝ እኛም occupy Betty ብለን መንግስት ውጡልኝ ለዚች ዱርዮ ካለን እንወጣታለን ተዋርደን አንቀርም።
ወይ የኔ ነገር ወደሳውና ባዝ ወሬዮ ስመለስ አቦ አታካብዱ ብዮ ጣልቃ በመግባቴ አንተ ኢትዮጵያዊ አይደለህም እንዴ ፈረንሳዊ መሆን አለብህ ተብዮ ከኢትዮጵያዊው ወሬ በማሽሙዋጠጥ ተገልያለሁ ቆይ ግን ፈረንሳዊ ምን ማለት ነው?
ምን እልባት ከምናምን አመት በሁዋላ "ቤቲ ግልፅ የወሲብ ወሬዎች አብዮት ያስነሳች ጀግና ትባል ይሆናል " እመኑኝ ጊዜ እኮ ባለጌ ነው።

No comments:

Post a Comment