ማርስዋን (Mars One) የተባለ የሆላንድ ኩባንያ እ.ኤ.አ በ2023 እንዲካሄድ ላቀደው ወደ ፕላኔት ማርስ ጉዞ የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞችን መመዝገብ እንደሚጀምር ዛሬ ይፋ አደረገ። ጉዞው ለየት የሚያደርገው ሰዎቹ ወደ ምድር ተመልሰው የማይመጡ ሲሆን እስከ ህይወታቸው ፍጻሜ ማርስ ላይ ለመኖር ተስማምተው ጉዞውን ይጀምራሉ።
የመንኮራኩር ጉዞዎችን እጅግ ውድ ከሚያደርጋቸው ነገሮች አንዱ ደርሶ መልስ ጉዞ ሲሆን ይህኛው ግን የመመለሻ ጉዞ ስለሌለው ዋጋው አነስተኛ የሆነ እና በዛ ያሉ ሰዎች ሊከፍሉት የሚችሉት እንደሆነ ተነግሮአል። በርካታ መኩራኩሮችን በአንድ ግዜ በማምጠቅ ብዙ ሰዎችን ወደ ማርስ ለማጓጓዝ እቅድ የተያዘ ሲሆን በማርስ ላይ የሰው ልጅ ኑሮውን እንዲመስርት እና ግዛት እንዲኖረውም ሰፊ እቅድ ይዘዋል። ማንኛውም ለጉዞው ጤናማ የሆነ ሰው ማመልከት የሚችል ሲሆን የማመልከቻ ክፍያ እንዳለው ታውቋል።
ሁለተኛ ጉዞ እ.ኤ.አ በ2025 የታቀደ ሲሆን ከመጀመሪያው ጉዞ በተቀሰሙ ልምዶች በመጠቀም የተሻለ ጉዞ እንደሚሆን ታምኖበታል። ሴቶችም ወንዶችም እንዲጓዙ የሚደረግ ሲሆን በተከታታይ ዙር ጉዞዎች በማርስ ላይ የሰው ልጅ መዋለድ እንዲችል ይደረጋል ብለዋል።
ድርጅቱ ለጉዞ የሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር እና ለገበያ በማቅረብ ከሚያስፈልገው ገቢ የተወሰነውን ለመሸፈን ያቀደ ሲሆን ምርቶቹን ማስተዋወቅ ጀምሮአል። ከዛ በተጨማሪም የሰው ልጅ ማርስ ላይ መኖር ቢጀምር እንዴት እንደሚኖር እዚህ ምርድ ላይ ያለው ሰው በጉጉት ለማየት ስለሚፈልግ ከቴሌቭዥን ስርጭት በርካታ ገንዘብ ሊያገኙ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል።
ብዙዎች አስፈሪ፣ በጣም ከባድ እና ለሰው ልጅ አሁን ባለበት ሁኔታ የማይታሰብ ነው ቢሉም ድርጅቱ እንደሚያሳካው ሙሉ ተስፋ አድርጎ እንቅስቃሴውን ጀምሮአል። [CNN]
source: thearadaonline.com

No comments:
Post a Comment