መለስ ዜናዊ የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም ከተጠቀሙባቸው ዘዴዎች አንዱና ዋናው “የትግራይ ህዝብ የሥርዓቱ ልዩ
ተጠቃሚ”እንደሆነ አድረገው በካድሬዎቻችው በኩል ያለመሰልቸት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ማካሄድ ነበር። ይህ ዘዴ የትግራይ ህዝብ
ተጠቃሚ፤ የኢትዮጲያ ህዝብ ግን የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲሰማው አድርጎታል። አቶ መለስ “ነፃ ሚድያ” ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻል ሁኔታ ስላጠፉትና የኢትዮጵያ ህዝብም የሳቸው የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ስላደረጉት እሳቸው የሚናገሩት እና የሚያወሩት እውነት ይሁን ውሸት ለማወቅ ይቸገራል። ያ ውሸት ተደጋግሞ ሲነገረው ውሸቱን እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል። አቶ መለስ ኢኮኖሚህ 11 በመቶ አድጓል እያሉ ነጋ ጠባ ሲወተውቱት፣ ከአመት ወደ አመት ኑሮው እየከፋ፣ ጉልበቱ በረሀብ እየደከመ የሄደው ወገን ውሸቱን እውነት አድርጎ ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭ የለCም።
መለስ የትግራይ ህዝብ አጋዥ አጣ እንጂ በምን አይን እንደሚያያቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ። መለስ እና ኢትዮጵያ እሳትና ጭድ
መሆናቸው ጎልቶ የወጣው በተለይ የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት አክሽፈው፣ የኢትዮጵያ መሬቶችን ለኤርትራ አሳልፈው ለመስጠት ባለ አምስት ነጥብ የሰላም እቅድ የሚል የማጭበርበርያ እቅድ ነድፈው እሱን ለመተግበር ደፋ ቀና ሲሉ በነበረበት ወቅት ማለት ነው!
ቀጥሎም ከመተማ እስከ ጋምቤላ ያለውን እጅግ ለም መሬት ያላንዳች ሀፍረት ለሱዳን እጅ መንሻ ሲያደርጉ፣ ሰውየው ኢትዮጵያን
በሁሉ መንገድ ለማዳከም ቆርጠው የተነሱ እንደሆኑ ታወቀ። ባለፈው አመትም ቢሆን የሻቢያ ሰራዊት በተደጋጋሚ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ፣ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አስሮ፣ ያገሬውን የቀንድ ከብቶች፣ በጎችና ፍየሎች እንደልቡ ዘርፎ ሲወስድ፣ መለስ “ሻቢያ ግልጽ ጦርነት እስካልከፈተብን ድረስ፣ በትንንሽ ትንኮሳዎች ተታለን ዋናው ጠላታችን የሆነውን “ድህነትን” ከመዋጋት ወደኋላ አንልም” ሲሉ በኢትዮጵያ ህዝብና ሀገራዊ ሉዓላዊነት ሲያሾፉ ተስተውለዋል።
መለስ ከክልሎች ሁሉ የሚፈሩት እና ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግለት የሚሹ ቢኖር የትግራይን ክልል ነው። የትግራይ ህዝብ አመፅ ማለት በሰራዊቱ ውስጥ ያለው ወታደርም አመፀ ማለት ነው። ያ ደግሞ የመለስ የስልጣን እድሜ ያሳጥረዋል። ያ አደገኛ ሁኔታ እንዳይከሰት ነበር አቶ መለስ ቴዎድሮስ ሐጎስን የክልሉ የበላይ ጠባቂ ያደረጉት። ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሐጎስ ከፊሎቹ ወንድሞቹ የሻብያ ተዋጊዎች ስለነበሩ፣ ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ስትከፈት እና መቀሌ የሚገኘው የአይደር የህፃናት ት/ቤትን በቦምብ ሲደብደብ፣ ቁጣውን በሰልፍ የገለፀው የመቀሌ ነዋሪ ህዝብ ከጠየቃቸው ጥያቄዎች አንዱ “ቴዎድሮስ ሐጎስን” እንዲባረርለት ነበር። አቶ መለስ ደግሞ እራሱ አስጊ ሁኔታ ውስጥ ቢኖርም፣ ፈራ-ተባ ከማለት ውጪ፣ ከኤርትራ ጋር የወገነውን ጠ/ሚኒስቴር ደፍሮ ከስልጣን ሊያባርር የሚችል የህወሓት ኃይል ስላልነበር፣ ቴዎድሮስ ሐጎስን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አውጥቶ ወደ ኃያሉና ታማኙ የፖሊት ቢሮ አባል አድርጎ ሾመው። ያቺን የመቀሌ ህዝብ ክስ ለመበቀል ነበር ቴዎድሮስ ሐጎስም በምርጫ 97 ጊዜ“ትግሬ ወደ መቀሌ፣ ዕቃ ወደ ቀበሌ” የምትል መርዝ በቅንጅት ስም አዲስ አባባ ሆኖ የረጫት። የኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ ድጋፍ የነበረው ቅንጅት ለዘር ግጭት ትንኮሳ የተበተነችውን መርዝ ተጠያቂው ቅንጅት እንዳልሆነ በሚድያ ወጥቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለመግለጽ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ሚዲያውን የተቆጣጠረው በረከት ስምኦን ግን የቅንጅትን ጥያቄ ሊያስተናግድ ቀርቶ አመራሩን እንዳለ በጅምላ ዘብጥያ እንዳወረዳቸው የትናንቱ ትውስታ ነው።
ዛሬ መለስ የሉም። ያሉት የአቶ መለስ ባለሟሎች ናቸው። በረከት ስምኦን፣ ሳሞራ ዮኑስ፣ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ እና ሌሎች የኤርትራ ዝርያ ያላቸው ሰዎች ዋናውን የስልጣን ቁልፍ ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በመሆን አቶ ሀ/ማርያም ደሳለኝን አንደ ጋሪ ፈረስ ከፊት አስቀድመው እየተጓዙ ይገኛሉ። ፍርሃት እና ጭንቀት የሞላበት ጉዞ እንደሆነ ግልጽ ነው። “ያለን አማራጭ መለስ ሲጠቀምበት የነበረውን ስልት መጠቀም አለብን” እንደሚሉ ልዩ ትምህርትን አይጠይቅም። አንደኛና ዋነኛው ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከቀሪው ወገኑ ጋር እንዳያብር አሁንም ተነጥሎ የሚመታበት መንገድ መዘየድ የግድ ይላል። ይህን ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ የተመደበችው ደግሞ አዜብ ሆናለች።
“መለስ ትግራይን በኢንዱስትሪ ለማልማት የ5 አመት እቅድ ነድፎ ነበር” - አዜብ መስፍንአዜብ ኢህአዴግ ወይም ራስዋ በምትቆጣጠረው ቴሌቭዥን ሰሙኑን ታይታ ነበር። ጋዜጠኛዋን ያነጋገረቻች
አዜብ ኢህአዴግ ወይም ራስዋ በምትቆጣጠረው ቴሌቭዥን ሰሙኑን ታይታ ነበር። ጋዜጠኛዋን ያነጋገረቻች ኤፈርት ቢሮ ውስጥ ቢሆንም፣ አዜብ ግን አሁንም ሀዘን ላይ የተቀመጠች እንደሆነች ተመልካች እንዲያውቅላት የምትሻ ትመስላለች። ድምጽዋ በልቅሶ የጎረነነ ታስመስለዋለች። “መለስ ትግራይን በኢንዱስትሪ ለማበልጸግ የአምስት አመት እቅድ ጽፎ ነበር!” አለች አዜብ በጎረነነ ድምጽ። አሃ! ጨዋታ እዚህ ላይ ተጀመረ። መለስ እሱ ራሱ አልፎ አልፎ ሲናገር እንደተደመጠው ወደ ክልል ወርዶ ጣልቃ ልግባ እንኳ ቢል ጊዜ እና አቅሙ እንደሌለው፣ እሱ የተወጠረው፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ጉዳዮች፣ በአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካ (ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ ወዘተ) ከዛም አልፎ በአፍሪቃና በጥቂቶችና በበለፀጉ የዓለም መሪዎች ስብሰባ (G-8 እና G-20) ላይ እየተገኘ በንቃት መሳተፍን እንደሆነ ደጋግሞ ይገልጽ ነበር።
ታድያ ዛሬ ወ/ሮ አዜብ ከነበረከት ስምኦን ጋር ሆነው የጠነሰስዋትን ተንኮል ይዘው ወደ ሚድያ በመቅረብ መለስ ትግራይን የኢንዲስትሪ ማእከል ለማደረግ መጽሀፍ ጽፏል ብለው አረፉት። መለስ ለትግራይ ልዩ የእንዲስትሪ ራእይ ቢኖራቸው ምነው 21 አመት ሙሉ ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ አልተገለፀላቸውም? ይቺ ራእይ የአዜብ እና የበረከት “ትግራይን የማጥመድ ራእይ” እንጂ፣ እንደተባለው የልማት ራእይ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። ደፋርዋ አዜብ አክላም “የኔ ኃላፊነት የመለስን ራእይ እውን ማድረግ ነው” ካለች በኋላ የEFFORT (ትእምት) ኩባንያዎች ዘንድሮ ከ16.5 ቢልዮን ብር በላይ የሚገመት ምርትና አገልግሎት ለገበያ ለማቅረብ እቅድ ተይዟል አለች።
ለሲሚ ጀሮ እንዲጥም ግን አዜብ ከሁሉ አስቀድማ “የህዝብ ንብረት” ስትል የገለጸችውን ኤፈርት ባለፈው አመት ብቻ 376 ሚልዮን ብር በግብር ለመንግስት ገቢ አድርጓል አለች። ዋናው ጥያቄ ደግሞ “የህዝብ ንብረት” ከሚሉ ቃላቶች ጋር ይሆናል። እውነት ኤፈረት የህዝብ
ነውን? ከሆነ ታድያ ለምን በድብቅ በአንድ ቤተሰብ ቁጥጥር ስር ዋለ? የህዝብ ከሆነ ህዝቡ የማኔጅመንት ቦርድ አቋቁሞ በየጊዜው ለምን
የኤፈርት ገቢና ወጪ አንዲያውቅ አልተደረገም?
ከወ/ሮ አዜብ በፊት ኤፈርትን በሥራ-አስኪያጅነት ይዞ የነበረው የመለስ ታማኝ ካድሬ አባዲ ዘሞ (የአሁኑ በሱዳን የወያኔ አምባሳደር)
መሆኑ ይታወሳል። ከአባዲ ዘሞ በፊት ኤፈረትን በመዳፉ አስገብቶ ይቆጣጠረው የነበረው ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ነበር። ታድያ በሱ ጊዜ
በውጭ የሚገኙ የህወሓት ደጋፊዎች መሃል ኤፈረት የህዝብ ነው ከተባለ ለምን ኦዲት አይደረገም የሚል ጭቅጭቅ ተነስቶ ኦዲት መደረግ
አለበት የሚሉ አሽንፈው የውጭ አዲተር ቀጥረው ወደ መቀሌ ይልካሉ። ወደ ኤፈረት ዋና ጽ/ቤት ያመራው የሂሳብ አካውንት መርማሪ
ደግሞ ሽማግሌውን አግኝቶ ለምን እንደመጣ ሲነገረው፣ ስብሃት ነጋ ኃይለ-ቃል በተሞላበት አንደበት “በል ሌላ ችግር ሳይከተልህ
ወደመጣህበት ቶሎ ተመለስ!” ብሎ አሰናበተው።
ወ/ሮ አዜብ ደግሞ ከኤፈርት የሚዘርፉት ገንዘብ አልበቃ ብሏቸው የትግራይን ህዝብ ከተቀረው ወገኑ ጋር ለማጋጨት ድርጅቱን የፖለቲካ
መሳሪያ አድረገው ለመጠቀም እየተንቀሳቀሱ ያሉት። እዚህ ላይ አንዳንድ ተንኮሉ ያልገባቸው ወገኖቻችን የአዜብን ቃል እንዳለ በመውሰድ
ይኸው “እነኚህ ዘረኞች ትግራይን ለማልማት እንጂ” ቀሪው የኢትዮጵያ አካል ምናቸውም እንዳልሆን ነው የሚያሳየው እያሉ በጽሁፍ
ሳይቀር ብሶታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ይኽም ማለት የነ በረከት/አዜብ አደገኛና ከፋፋይ ስትራተጂ ውጤትማ ሁኗል ማለት ነው።
ምክንያቱም እነሱም ያቀዱት ፕላን ቢኖር፣ ተቃዋሚ ከሚባሉት ክፍሎች በኩል የሚሰነዘረውን አስተያየት ቀንጭቦ በመውሰድ፣ መልሰው
ለትግራይ ህዝብ “ይኸው እኛ ትግራይን በኢንዲስትሪ እናበለፅጋለን ስንል፣ ትምክህተኞችና ነፍጠኞች ግን ያንተን እድገት እየተቃወሙት
ይገኛሉ። እነዚህ ኃይሎችን ነው መፍራት ያለብህ። መድረክም ይሆን ሌሎች ተቃውሚዎች ጠላቶችህ መሆናቸውን ላንድ አፍታም ቢሆን
መዘንጋት የለብህም!” እያሉ ህዝቡን ይበልጥ በወገኑ ላይ እንዲጠራጠር፣ ለውጥ ፈላጊ እንኳ ቢሆንም “ከማላውቀው መልአክ የማውቀው
ሰይጣን ይሻለኛል” ወደሚል ድምዳሜ እንዲደርስ ይገደዳል። ስለዚህ ወ/ሮ አዜብ ተናገረች ተብሎ እስዋን አምኖ፣ ነገሮችን በሰከነ አእምሮ
ሳያጤኑ ወደ ድምዳሜ እና ወደ ማውገዝ መጓዝ የተቃዋሚውን ጎራ ትግል እንደሚጎድውና ይባስ ብሎ የገዢውን አካል እንደሚያጠናክር
ከወዲሁ መታወቅ ይኖርበታል።
ኢትዮጵያ በልጆችዋ በልጆችዋ የተባበረ የተባበረ ሃይል ሃይል ታፍራና ታፍራና ተከብራ ተከብራ ትኖራለች ትኖራለች!!!!
ጋሻ ለኢትዮጵያውያን
ህዳር 14 2005
ሲያትል ዋሽንግተን
source ;http://www.abugidainfo.com/amharic/wp-content/uploads/2012/11/Gasha23November2012.pdf
No comments:
Post a Comment