No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Thursday, 29 November 2012

አይ.ኤል.ኦ ኢትዮጵያን ለሠራተኞች መብቶች “ክፉ” ሃገር ሲል ፈረጀ



የአይኤልኦ የመደራጀት ነፃነት ኮሚቴው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ፖል ፋን ደር ሃይደን
ከእነዚህ ዋና ዋና እና ቁልፍ ከሚባሉ ስምምነቶች መካከል በማኅበር የመደራጀት ነፃነት ስምምነት፣ ለመደራጀት መብት የሚሰጥ ጥበቃ ስምምነት፣ የወል ድርድር መብት ስምምነት የሚጠቀሱ ሲሆን ኢትዮጵያም እነዚህንና ሌሎቹንም ስምምነቶች ተቀብላ ፈርማቸዋለች፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ ስምምነቶቹን የማክበር ግዴታ እንደሚጠበቅባት የአይኤልኦ የመደራጀት ነፃነት ኮሚቴው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ፖል ፋን ደር ሃይደን ገልፀዋል፡፡የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የሥራ ድርጅት – አይኤልኦ ኢትዮጵያን የሠራተኞችን መብቶች በማክበር በኩል የከፋች ሃገር ናት ሲል
በቅርቡ ሪፖርት አውጥቷል፡፡የአይኤልኦ አካል የሆነው የደራጀት ነፃነት ኮሚቴ ወደ 55 ዓመታት ለሚሆን ጊዜ በሥራ ላይ ያለ ተቋም ነው፡፡ ዛሬ 186 ሃገሮች የሥራ ድርጅቱ አባላት ሲሆኑ ዋና ዋና የሚባሉ ስምምነቶቹንና ሠነዶቹን በየሃገሮቻቸው የሕግ አውጭ አካላት አስፀድቀው ፈርመዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሥራ ድርጅት – አይኤልኦ ኢትዮጵያን የሠራተኛ መብት የማያከብሩ ክፉ ሃገሮች ዝርዝር ውስጥ ያሠፈረበት ድምዳሜ ላይ የደረሱት ኮሚቴአቸው የእነዚያን ስምምነቶች መጣስን የሚመለከቱ ስሞታዎችን የሚመረምር በመሆኑና እንዲህ ዓይነት አቤቱታዎችም ከኢትዮጵያ የደረሱት በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
 source VOA ሐሙስ, ኖቬምበር 29, 2012

No comments:

Post a Comment