በቀደመ ስማቸው ኢያሱ ተፈሪ ተብለው ይጠሩ የነበሩት አባ ገብርኤል በቀድሞው ፓትርያርክ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፈቃድ አባ ገብርኤል በመባል የዽዽስና ማእረግ
ተቀበሉ ከዚያም በተለያዩ የኢትዮዽያ አሕጉረ ስብከቶች በሊቀ ጳጳስነት አገልግለዋል በተለይም የቀደመችው የኢትዮጵያ አካል የነበረችው የኤርትራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ ከተዋሕዶ ትምህርት የወጣ የምስጢረ ሥላሴን ትምሕርት የሚያፋለስ መጽሐፍ በመጻፋቸው ምክንያት ተወግዘውና ተሽረው በቀደመው አለማዊ ሥማቸው አቶ ኢያሱ ተፈሪ ተብለው በቅዱስ ሲኖዶስ ተለይተው እንደነበር ታሪክ መዝግቦት የተቀመጠ መሆኑ የታወቀ ጉዳይ ነው
አባ ገብርኤል በአቋማቸው ወላዋይነት በተናገሩበት የማይጸኑእንደ ገበታ ውኃ የሚዋልሉ ይህን ብየ ነበር ብለው ይሉታና ትዝብት የሌላቸው እና ጠንካራ ነው ብሎ
ያመኑበትን ክፍል በመጠጋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚታወቁት እኚህ ግለሰብ ከአባ ጳውሎስም ጋር በፈጠሩት ጠብ አስመልክተው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ተናግረው ነበር ”አባ ጳውሎስ እንዲመረጡ ለዚህ ፕትርክና እንዲበቁ ባደረግሁት አስተዋጽኦ እጅግ ይጸጽተኛል”በማለት ከሀገር ወጥተው መንግሥትንና ፐትረያርኩን ሲቃወሙ የነበሩ በመንግሥትም የሰላ ሂስ ሲሰነዝሩ የታወቁ ግለሰብ መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው
በምድረ አሜሪካ በነበሩበት ጊዜም ትክክለኛውና ሕጋዊው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ናቸው እያሉ ሲናገሩ የነበሩት እኒህ አባት
የሰላማዊ ሰልፍ መሪ በየቲቪው መስኮትና በየሬዴዎው ጣቢያው የኢትዮጵያን ችግር ተንታኝ የነበሩ ግለሰብ ባልታወቀ ምክንያት እንደ አክሮባቲስት ተገልብጠው አዲስ አበባ በመግባት የሆነውን ያልሆነውን በመዘላበድ እነደገና ተቀይረውና ሌላ ሰው ሆነው ትናትና ደግሞ በአሜሪካ ሬዲዮ ጣቢያ የሰጡትን አስተያየት የሰማ ሰው እጅግ የሚያሳዝን ሆኖ እናገኘዋለን
ታዲያ እነዚህን ከመሰሉ አባቶች የቤተ ክርስቲያን አንድነት ይመጣል ብሎ መጠበቅ ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ያህል ነው አኒህ አባት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ተጣቂ እንደሆኑና ይታጠቁት የነበረው የጦር መሳሪያ እንደጠፋባቸው በዚህ ጦስ ምክንያት አንድ ግለሰብ ተጠርጥሮ ሥራውን እንዲያጣ ምክንያት አንደተደረገ በአንድ ኢንተርኔት ድህረገጽ እንዲህ ይነበባል
የአቡነ ገብርኤል ማካሮፍ ሽጉጥ ጠፋ
- ሰርቀሀል ተብሎ የተጠረጠረው ዲ/ን ፍጹም እንዳለ የተባለ አገልጋያቸው እንዲባረር ተደርጓል፡፡
ሽጉጥ በጓዳ አስቀምጠው የሀይማኖት አባት ነኝ ለማለት መሞከር በእጅግ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ነገሩ አሳፋሪ ስለሆነም ለፖሊስ ለማመልከት አልደፈሩም፡፡ እስራኤልን የሚጠብቅ አያንቀላፋም የሚለውን ቃል ያላነበበቡት አባቶቻችን ራሳቸውን ለመጠበቅ የማያንቀላፋውን ጌታ ትተው ሽጉጥን ተስፋ ማድረጋቸው ይገርማል፡፡ እውነትን ጽድቅን እየሰሩ እግዚአብሔርን ተስፋ ከማድረግ ይልቅ ሁሉን እያደፈረሱ በሽጉጥ መታመን የማይጠቅም ነገር መሆኑን መዘንጋታቸው ገርሞናል፡፡
ብጹዕነታቸው በደርግ ጊዜ አድርገውት በነበረው ንግግር “ሰው ራሱን በሚያስፈልጉ ነገሮች መጠበቅ አለበት፡፡ እግዚአብሔርም እኮ የሚጠብቁት ጠባቂ መላዕክት አሉት” በማለት እግዚአብሔርን በማያውቅ ባህሪያቸው ስለ እግዚአብሔር የስህተት ትምህርትን አስተምረው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ በቅዳሴያችን “መላዕክትን የምትጠብቃቸው አንተ ነህ” የተባለውን ጌታ፤ አቡነ ገብርኤል ግን ብቻውን ምንም እንደማያደርግ አስበው መላዕክቱ ይጠብቁት ነበር ማለታቸው በወቅቱ ትዝብት ላይ ጥሎዋቸው እንደ ነበረ ይታወሳል፡፡ እኚሁ ጳጳስ ታድያ እግዚአብሔርም ይጠበቃል ብለው የሚያምኑ በመሆናቸው ለራሳቸው መጠበቂያ ሽጉጥ ቢይዙ የሚደንቅ አይሆንም፡፡ ብቻውን ሀያል እና አሸናፊ የሆነውን ጌታ በማንነቱ አለማወቅ እና ልጆቹን አክብሮ እንደሚዝ እና አንደሚጠብቅም አለማወቅ ከማካሮፍ ሽጉጥ ጋር ተቃቅፎ ለመተኛት እንደሚዳርግ እሙን ነው፡፡ የሀይማኖት አባቶች የሚጠበቁት በመንፈስ ቅዱሰ እንጂ በሽጉጥ አለመሆኑን ለአባቶቻችን እግረ መንገዳችንን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡
ታዲያ ወገኖቼ ይህን በመሰለና እጅግ ለመስማት በሚዘገንን ድርጊት በሥነምግባርና በሞራል ዝቅጠት በወደቁ አባቶች የቤተ ክርስቲያን አንድነት የምዕመናን ሕብረት እንዴት ይምጣ የሀገር ሰላም የወገን ሰቆቃስ እንዴት ይወገድ ??
እባካችሁ ሁላችንም ለቤተ ክርስቲያን ሰላምንና አንድነቷን የምንናፍቅ ወገኖች በሕብረት የምንነሳበት ጊዜው አሁን ነው
ዘመነ ካሳ ፍራንክፈርት ጀርመን
No comments:
Post a Comment