No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Friday 28 June 2013

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው ከኢየሩሳሌም አርአያ

Bereket Simon is the Ethiopian Communications Ministerበዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።
source:-http://ecadforum.com/Amharic/archives/8672/

No comments:

Post a Comment