እስክንድር ነጋ

የሆነ ሆኖ እስክንድር ማክሰኞ ፍርድ ቤት ቀርቦ ‹‹ቤቴን አትውረሱብኝ›› ብሎ ስለማይከራከር ‹‹በዕለቱ ፍርድ ቤት መሄድ አልፈልግም›› ሲል ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ ግን ‹‹የግድ ማቅረብ ስላለብን ይዘንህ እንሄዳለን›› የሚል ምላሽ ሰጥተውታል፡፡
እናም እስክንድር በዕለቱ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ምንም አይነት ምላሽ ላለመስጠት ወስኗል፡፡ ባለቤቱም ‹‹የሚስትነቴን ድርሻ አትውረሱብኝ›› ብላ አትከራከርም፡፡ ፍርድ ቤቱ የፈለገውን ይወስን የሚል አቋም ነው ያላት፡፡ በዛሬው ዕለት ሊጠይቀው ቃሊቲ የመጣውን የሰባት ዓመቱን ህፃን ልጁን ጠባቂ ፖሊሶች እየሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ‹‹ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ፡፡ አይዞህ! ስርዓት ተቀያየሪ ነው፤ ንጉሱ የወረሱት በደርግ ተመልሷል፤ ደርግ የወረሰው በኢህአዴግ ጊዜ ተመልሷል፤ ኢህአዴግ የወረሰው ደግሞ ኢህአዴግ ሲወድቅ መመለሱ አይቀሬ ነው›› ብሎታል፡፡ በ1993 ዓ.ም ግምቱ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የእስክንድር እናት ቤት በግፍ እንደተወረሰ ይታወቃል፡፡
እስቲ አሁ እንኳን ምንአለበት ትንሽ እንደ ሰው አስባችሁ ልጁን የሚያሳድግበትን ንብረት ብትተውለት? …ዛሬም በትላንቱ መንገድ፣ ዛሬም በመለስ ጫማ፣ ዛሬም በመለስ ራዕይ… አቤት! እንዴት ልብ የሚያደማ ነገር ነው! ይህ ምን አይነት ጭካኔ ነው?
No comments:
Post a Comment