No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Thursday, 15 November 2012

ከአዲስ አበባ ውጪ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ መኢአድ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ

ህዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከአዲስ አበባ ውጪ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በኢህአዴግ ካድሬዎችና በመንግሥት ባለሥልጣናት ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ፡፡
የክልል ምክር ቤቶችና የወረዳዎች የምርጫ እንቅስቃሴ በመጀመሩ የኢህአዴግ ካድሬዎች እንደተለመደው አውሬ ባህሪያቸው ጎልቶ ወጥቷል ያሉት የመኢአድ የአሶሳ የአመራር አባል የመንግሥት ደህነቶች የተቃዋሚ ፓርቲ በተለይም የመኢአድ ፓርቲ አባላትንና ደጋፊዎችን እየለቀሙ መሬታችሁን ለቃችሁ ውጡ በማለት እያስፈራሩን ነው ብለዋል
በቅርቡ ሚጀመረውን የ2005 ዓ.ም አካባቢያዊ የቅድመ ምርጫ የእንቅስቃሴ መርሃ- ግብር ተከትሎ በቤንሻንጉል፣ በደቡብ ብሄርና ብሄረሰቦች ክልል ቀበሌ ገበሬ ማህበር በሚገኙ የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ድብደባ፣ ከአካባቢ እና ከሥራ ማባረር እና እሥራት የመሳሰሉ ከፍተኛ ጫና ነው ብለዋል፡፡
በአሶሳ እና በቤንቺ ማጂ ዞኖች የሚኖሩ 150 የመኢአድ አባላቶች እና ደጋፊዎች ከጥቅምት ወር ጀምሮ መሬታቸውን መነጠቃቸውን ታውቋል፡፡
መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በ2002 ዓ.ም ምርጫ ዋዜማ ከኢህአዴግ ጋር የምርጫ የስነ-ምግባር ደንብ መፈረሙ ይታወሳል፡፡

No comments:

Post a Comment