ከስምንት ወር በላይ የያዘው የእስልምና ተከታዮች ይሄው የድምጻችን ይሰማ ፣የምንፈልገውን እኛው እንመርጣለን መንግስት በሃይማኖቶች ጉዳይ ጣልቃ አይግባብን የሚለው ጥያቄ አሁንም እንደቀጠለ ዉሏል በዛሬው ዕለት በደሴ ከተማ ከፍተኛውን የተቃወሞ ሃሳባቸሃንውን ሲያሰሙ የዋሉ ሲሆን ከባለፈው ሳምንት በተሻለ መልኩ ድምጻቸውን ለማሰማት እንደቻሉ ሪፖርተራችን ያሬድ ከስፍራው ዘግቦአል ።የባለፈውን ሳምንት የፌደራል ፖሊሶች በንጹን ዜጎች ላይ ያደረሱትን ዘገባ ጠቅሶ ሁለት ወጣቶች በከፍተኛ ደረጃ ከመደብደባቸውም በላይ በአሁን ሰአት አንደኛው በደሴ ሆስፒታል በህክምና ላይ ሲሆን አንዱ ግን የደረሰበት አልታወቀም ሲል በዘገባው ላይ ገልጿል።በተመሳሳይ ዜና ሲገልጽ በነዚህ ወጣቶች ላይ የተፈጸመው ድብደባ ሰበአዊነት እና ርህራሄ የጎደለው ከመሆኑም በላይ ራሳቸውን ስተው መንገድ ላይ ለሁለት ሰአታት ሲደበድቧቸው ተመልክቼአለሁ ከዚያም በኋላ በፖሊስ መኪና ጭነዋቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል እኔም ሪፖርቴን ለማጠናቀር ስል ተከታትዬ ብሄድ ከፖሊስ ጣቢያው ሊያደርሱኝ ባለመቻሌ ያሉበትን ለማወቅ አልቻልኩም ነበር ሲል የጠቆመ ሲሆን ነገር ግን ከተደብዳቢዎቹ ወገን የሆነ አንድ ጓደኛው ወዳጁ የት እንደአለ ጠቁሞኝ በትላንትናው እለት ሆስፒታል ሄጄ ጠይቄዋለሁ ደህንነቱ በከፋ ሁኔታ ላይ ነው ሲል ገልጾ ስለሌላኛው ወገን ግን ምንም ነገር የተሰማ ፍንጭ የለም ጓደኛውንም ስጠይቀውም የማውቀው ነገር የለኝም በማለት በሚያቃስት እና በደከመ ድምጽ ገልጾልኛል ሲል የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ያሬድ ከስፍራው ዘግቦአል።
No comments:
Post a Comment