የተማረ ሆኖ ዕውቀቱን የማይገልጽ፣ታዋቂው ደራሲ ከበደ ሚካኤል ይህንን ብለውን አልፈዋል። ደራሲው ዕድሜ ለግሷቸው መምህሩም ለማስተማር ተማሪውም ለመማር አለመቻላቸውን ዛሬ ቢያዩ ምን ይሉ? በሃያ አንደኛው መቶ ዓመት ጉግ ማንጉጎች ተፈጥረው የዕውቀት ጮራ በሃገራችን ምድር እንዳይፈነጥቅ ጋርደዋት በጭለማ ውስጥ ትገኛለች።
ባለፀጋ ሆኖ ገንዘቡን የማይሰጥ፣
ደሃ ሆኖ መሥራት የማይሻ ልቡ፣
ሶስቱም ፍሬ ቢሶች፣
ለማንም አይረቡ።
‘እንዳያማህ ጥራው እንደይበላ ግፋው’ እንደሚባለው በአለፉት ሃያ ዓመታት ዩኒቭርሲቲዎች ተከፈቱ ቢባልም፤ የተማሪዎቹ ቁጥር ቢጨምርም፤ ተቋማቱ የመማርና የማስተማር ሥራ የሚካሄድባቸው ሥፍራዎች ሆነው አልተገኙም። የአካዳሚ ነፃነት በሌለበት በዕውቀት እድገት የለም። ተቋሞቹ የዕውቀት መገብያ ሳይሆኑ የካድሬ መፈልፈያ የስለላ ሥራ ማካሄጃ ናቸው። ይህም ሁኔታ በነፃነት መምህሩም ለማስተማር ተማሪውም ለመማር
አላስቻላቸውም። ያ እንዳለ ሆኖ ከዓለም ዙሪያ ለዕውቀት
ማዳበሪ አዲስ ገኝቶችን ለመቃረም መንገዱን ክርችም አርገው ዘግተውታል። ዘመኑ ሣይንስ ያስገኘውን የዕደ ጥበብ ውጤት
ተጠቅሞ ዕውቀትን የሚያስፋፋበት ድንቁርናን የሚያጠፋበት ጊዜ ነው። ዕደ ጥበቡን ተጠቅሞ የዓለም ሕብረተሰብ ከችግር
ለመውጣት በብረሃን ፍጥነት ሲራመድ እኛ ገና በኢሊ ጉዞ ላይ ነን።
ቆመን የጠበቅናቸው የአፍሪካ ሃገሮች የመገናኛ ብዙሃን ተጠቅመው ድንቁርና ሲዋጉ፡ ረሃብንና ቸነፈርን፣ በሽታን
ሲያጠፉ እኛ በሰቆቃ አረቋ ውስጥ ነን። እነርሱ በአሁኑ ጊዜ ተማሪዎቻቸውና አሰተማሪዎቻቸው መገናኛ ብዙሃንን
በመጠቀም የዓለም ሕብረተሰብ አባል ሆነዋል። internet, you tube twitter, face book,
skype, video, radio ,TV etc ዕደ ጥበቡን ተጠቅመው ወራትና ሳምንት የሚፈጁባቸውን ሥፋራዎች
በሰከንድና በደቂቃ ደርሰው ለሕዝባቸው የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ችለዋል። ኢትዮጵያ 90 ሚሊዮን የሕዝብ
የሚኖርባት በነፃነት ሣይንስ ያስገኘው የዕደ ጥበብ ተጠቀሚ አይደለችም። ሱማሊያ 10 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ግን
ተጠቀሚ ናት።የወያኔ መንግሥት በሕጋዊነት ስም ሕገወጥ ተግባር እየፈጸመ ነው።ሰው በመሆናችን ተፈጥሮ የቸረንን የማወቅ መብት በመሣሪያ ኃይል ተቆጣጥሮ ያደነቁረናል። እኛም የፈቀድንለት ይመስላል።ያ አልበቃ ብሎ በቅርቡ በፓለቲካ ታሐድሶና ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ድጋፍ ስም መምህራን እየተገላቱ ነው። አሻፈረኝ ያሉ መምህራን ከሥራ ሲባረሩና አንደአውሬ ሲታደኑ የምናየው ነው። ታሕድሶውን የተቀበሉትም ቢሆኑ ከሥራ ትባረራላችሁ ቤተሰባችሁ ይራባል ተብለው በፍራቻ ላይ ናቸው።ከዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የታወቁ ዩኒቭርሲቲዎች የተመረቁ መምህራን በአንድ በታጠቀ የአጋዚ ወታደር ያለፍቃዳቸው ወደ ታሕድሶ እየተገፉ ነው። ይህንን ያየ ወጣት መማርን እንዴት ያየዋል? በተማሪዎችና በመምህራኑ መካከል መናናቅ ይፈጥራል። መምህራን እንደባለሞያ ሳይሆን እንደሥራ ፈት ቦዘኔ አንድ ለአምስት ተጠናፈጉ መባሉ ውርደት ነው።እንኳስ ለሙሑሩ ለሥራ ፈቱ ቦዘኔም የሚመኙት አይደለም።
ስለዚህ ተቀባይነት ባለው የሞያው መስክ መምህሩም ያስተምር ተማሪውም ይማር።
ታደለ መኩሪያ
tadele@shaw.ca
No comments:
Post a Comment