የጠቅላይ
ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ለሕዝብ በግልጽ ባልተገለጸበት በዚህ ወቅት፤የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ
ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን ትእዛዝ መሰጠቱንና፤ ላለፉት ሶስት ቀናት ተግባራዊ ሆኖ መቀጠሉን የመከላከያ ምንጮች
ገለጹ።
መንግስት የመከላከያ ሰራዊቱ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን ትእዛዝ የሰጠው ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ መሆኑ ለሰራዊቱ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ፤ ወታደራዊ ባለሙያዎችና አንዳንድ የመከላከያ ምንጮች፤ ማስጠንቀቂያው ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ ይልቅ፤ ከአቶ መለስ ጤና ሁኔታ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ግምት ሰንዝረዋል::
መንግስት የመከላከያ ሰራዊቱ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን ትእዛዝ የሰጠው ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ መሆኑ ለሰራዊቱ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ፤ ወታደራዊ ባለሙያዎችና አንዳንድ የመከላከያ ምንጮች፤ ማስጠንቀቂያው ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ ይልቅ፤ ከአቶ መለስ ጤና ሁኔታ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ግምት ሰንዝረዋል::
በዚህ
ሳምንት የኢትዮጵያ ምድርና የአይር ሀይል አባላት፤ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑ ከመከላከያ ሚኒስቴር
በወረደ ትእዛዝ መሰረት፤ በአዲስ አበባ ከተማና በደብረዘይት አየር ሀይል ግቢ፤ ሰራዊቱ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ
በስራ ገበታው በተጠንቀቅ ሆኖ ተግባሩን እንዲቀጥል መታዘዙ ታውቋል።
በተለይም በዘመቻ መምሪያ እንዲሁም ስንቅና ትጥቅን፤ በሚቆጣጠረው ድርጅት መምሪያ ከፍትኛ እንቅስቃሴ በመታየት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ምንጮች፤ በሀገሪቱ የጦር መሳሪያ እና የጥይት ማከማቻ ዲፖዎች ጥበቃው መጠናከሩ ታውቋል።
የመከላከያ ሚኒስቴር እና በተዋረድ ያሉ የሰራዊቱ መዋቅሮች፤ በይበልጥም በዘመቻ መምሪያና በድርጅት መምሪያ ከፍተኛና መስመራዊ መኮንኖች፤ 24 ሰኣታት ቢሮዎቻቸውን ክፍት አድርገው፤ በየተራ የበላይ ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ተመልክቷል።
ይህ ለሰራዊቱ የአደገኛ ደረጃ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው፤ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ፤ አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ሊሰነዝሩ ስለመዘጋጀታቸው፤ መረጃ ደርሶናል በሚል እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ወታደራዊ ባለሙያዎች በመንግስት በኩል የቀረበው ምክንያት የማያሳምን እንዳልሆነ ይናገራሉ። ለአክራሪ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ አየር ሀይል በተጠንቀቅ የሚቆምበት ምክንያት ምንድር ነው? ሲሉም አክለው ጠይቀዋል።
ይህ ሁኔታ፤ መንግስት አቶ መለስን በተመለከተ የማይቀረውን ጉዳይ ለመግለጽ መዘጋጀቱንና ይህንን ተከትሎ የሚፈጠር አለመረጋጋትን ለመቆጣጠር የተወሰደ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል የመከላከያ ምንጮች ግምታቸውን ያሳርፋሉ። ሁኔታዎች ኤርትራ እንድትወረን መንገድ ይከፍታል በሚል ስጋት የሚደረግ ዝግጅት ሊሆን ይችላልም ብለዋል።
No comments:
Post a Comment