No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Wednesday 15 August 2012

መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ መግባቱን ያቁም!

ትኩስ መረጃ
ሙስሊም ሆይ ይህን ጉድ ሰማህን፤ ላልሰማው አሰማ!!!
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒሰተር፤ የኢህአዴግ የድርጅት ጽ/ቤት እና የብሄራዊ ደህንነትኤጀንሲ የዒድን ሰላት ለማጨናገፍ ያለ የሌለ ኃይላችውን አሟጠው እየሰሩ መሆኑንየውስጥ ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ በጣም በሚገርም ሁኔታ ለዚህ ጉዳይ የመንግስትንመዋቅር ከመጠቀም አልፎ ሌላ ስራና ኃላፊነት የሌለባቸው እስኪመስል እያንዳንዱ የመንግሰት ቢሮ የራሱን አክሽን ፕላን አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም የአህለሱና ወል ጀማዓሱፊያ የሚባል የአህባሽ ማ...
ህበር በመላው አ/አበባ በማቋቋም ሰላማዊ ተቃውሞዋችንንለመግታት አስበው ባሳለፍንው ሳምንት በየሰፈሩ እየዞሩ አንድ ለአምስት ተደራጁበማለት ሊከውኑት የነበረው እንቅስቃሴ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በሙስሊሙ የነቃ ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ለአብነት ያክል በኮ/ቀራንዮ ክ/ከተማ ዉስጥ ባሉት 15 ወረዳዎች የኢህአዴግ የየወረዳው ካድሬዎችና በበድኑ የሚንቀሳቀሰው መጅሊስ አባላት በተለይም የቃጥባሬው ሸኽ የልጅ ልጅ የሆኑትን ሙሪድ ሰዒድን በመጠቀም በየወረዳው አንድለአምስት ተደራጁ እና በህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎች ላይ አሸባሪ ናቸው አይወክሉንምብላችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ውጡ በማለት ህዝቡን ለማደራጀት ያደረገው እንቅስቃሴ ፍጹም ሳይሳካ ቀርቶዋል፡፡‹‹ ልፋ ያለው ነጋዴ አያተርፍ›› እንዲሉ አሳዛኞቹ ‹‹ትንንሾቹ›› የኢህአዴግ ካድሬዎች የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ ለማስፈጸም ሌሊት ሲዞሩ፤ ስብሰባ ሲጠሩ፤ አንድ ለአምስት ተደራጁ ሲሉ ቢከርሙም የነቃውን ሙስሊም ፍጹም ከአቋሙ ሊያንቀሳቅሱት አልቻሉም፤ አልሀምዱሊላህ!!! ይህ ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ከዒድ ሰላት በፊት እነዚህን አካላት በማስተባበር ሰልፍ እንዲወጡ በማድረግና በዒዱ ቀን የተቃውሞ መልእክቶችን እንዲያስተላልፉና በህዝበ ሙስሊሙ መሃከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ ታስቦነበር፡፡ ይህም ሆኖ የኢስላም ጠላቶች ተኝተው አልተኙምና የወጠኑት አለመሳካቱን በመረዳት ሰላማዊ ተቃውሞዋችንንና የዒድን ሰላት ለማደናቀፍ ከላይ የጠቀስናቸው አካላት ማለትም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒሰተር፤ የኢህአዴግ የድርጅት ጽ/ቤት እና የብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ የሚከተሉትን እቅዶች ነድፈው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡
1ኛ) የፊታችን ጁሙዓ ሙስሊሙ ተቃውሞ ያደርጋል ብለው በማሰብ ባዘጋጃቸው የደህንነት አባላት እና የአህባሽ ቅጥረኞች በመስጂዱ ኢማም ላይ የድብደባ ወንጀል በመፈጸም ይህንን ተከትሎ ሊፈጠርየሚችለውን ችግር ተገን በማድረግ ብዙ ሰላማዊ ሙስሊሞችን ማሰርና ምናልባትም ጥቂቶችን በመግደል የዒዱን ሰላት በስታዲየም እንዳይሰገድ ማድረግ ፤ ከሂህበተጨማሪ በሙስሊሙ ላይ ፍርሃትን በመንዛት በመስጂድም ጭምር እንዳይሰገድ ማድረግ፡፡
2ኛ) የዒዱ ቀን ከመድረሱ አስቀድሞ ይንቀሳቀሳሉ ወይንም ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸውብሎ የሚያምናቸውን ግለሰቦች እያሳደዱ ማደን ፤ ይህንን ስራ የክልል ከተሞች ሳይቀሩ እንዲሰሩት ትእዛዝ የወጣ ሲሆን ከነዚህም መሃከል በአማራ ክልል በደሴ በባቲና በከሚሴ፤ በኦሮሚያ ክልል በበደሌኢሊባቡር ጅማና ወለጋ-ጊምቢ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
3ኛ) የዒድ ሰላት የሚሰገድበትን ሰዓት ቀድሞ በሚዲያ በማስነገር ህብረተሰቡ ያንን ሰዓት አስቦ ስለሚመጣ ቀድሞ በጠዋት በትንሽ ጀማዓ በማሰገድ አንድነቱን መበተንና ህዝበ ሙስሊሙ ሰላቱአምልጦኛል ብሎ ወደቤቱ እንዲመለስ ማስገደድ
4ኛ) ወደ ስታዲየም የሚጓዘው ህዝበ ሙስሊም ላይ የተለያዩ እክሎችን በመፈጸምወደ ብስጭት መምራት፡ ከዚህ መሃከል ብዙ መኪናዎችን እንደተበላሹና እንደተጋጩ በማስመሰል አውራ ጎዳናዎቹን መሙላትና መተላለፊያ መንገድ ማሳጣት፤ የመኪና ፓርኪንግ የለም በማለት በጠዋት ወደ ቦታው የሚሄደውን ህዝበ ሙስሊም እንዲጉላላ ማድረግ
5ኛ) በስታዲየም ዙሪያ ያሉትን ማይክራፎኖች እና ስፒከሮች እንዳይሰሩ በማድረግ ለህዝቡ ድምጽ እንዳይደርስ ማድረግ
6ኛ) በቃጥባሬ ጀመዓ ስም እና በኑር(በኒ) መስጂድ ምክትል ኢማም የሚነበቡ የህዝበ ሙስሊሙን ኮሚቴዎች የሚያወግዙ ግጥሞችን ማስነበብና ከየሰፈሩ ለተመረጡ ህጻናት ከበሮና ድቤ በማስያዝ መጅሊስንና መንግስትን የሚያወድስ ግጥሞችንና መንዙማዎችን በማስባል በህዝበ ሙሰሊሙ መሃከል ጸብ እንዲፈጠር ማድረግ ይህ ባይሳካ እንኳን የትክክለኛው ሙስሊም አቋም ይህ ነው በማለት ለተለመደው የሚዲያ ፍጆታቸው ግብዓት ማደረግ
7ኛ) በዒድ ሰላት ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ከባባድ መሳሪያ ያነገቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላቶችን በአውራ ጎዳናዎች ላይ በማሰማራት በህዝበ ሙስሊሙላይ ፍርሃትና ሽብር መንዛት ሲሆኑ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን የተከበረው ህዝበ ሙስሊም በመረዳት የተለመደ ሰላማዊነቱን እና ህገመንግስታዊነቱን በመጠበቅ መረጃውን ለመላው ሙስሊም ያስተላልፍ ዘንድ እናሳስባለን፡፡
‹‹ወመከሩ ወመከሩላሃ፤ ወላሁ ኸይሩል ማኪሪን!››!!!

No comments:

Post a Comment