No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Thursday, 16 August 2012

አወዛጋቢው አቶ መለስ ከያራ አግኝተውት የነበረው ሽልማት በሙስና የተገኘ እንደነበር ተጋለጠ



(ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ)
ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ1997 ዓ.ም በማዳበሪያ አምራችነቱ ከሚታወቀው ያራ ፋውንዴሽን ድርጅት የተቀበሉት የእውቅናና የገንዘብ ሽልማት አሁንም እያወዛገበ ነው፡፡
አቶ መለስ ከድርጅቱ የበላይ አመራር ሚስተር ኢንጌር የተቀበሉት የወቅቱ ሽልማት ድርጅቱ በማዳበሪያ ንግዱ ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ያላቸውን የትርፍ ክፍፍል ግንኙነት ለማጠናከር ሆንተብሎ የተሰጠ መሆኑ ተነገረ፡፡
በኖዌይ የሚታተመው አፍተን ፖስት ጋዜጣ ይፋ ባደረገው ስሞነኛ መረጃው ድርጅቱ ከሚያገኘው የተጣራ ትርፍ 30 በመቶ፣ የተፈጥሮ ሀብቱን ለተጠቀመበት (royalty) 4 በመቶ ለባለስልጣናቱ የሚከፍል ሲሆን፣ ካላቸው ድርሻም 5 በመቶ እንደሚያገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እንደ ጋዜጣው ዘገባ አንድ ሦስተኛው የድርጅቱ ትርፍ በአፍሪካ ተወዳዳሪ ወደ ሌለው ጨካኝ ስርዓት ኪስ እንደሚገባ ነው፡፡ የያራ ድርጅት የመረጃ ዳይሬክተር ኤስባን ቱማን ጋዜጣው ስለአዋጭነቱ ለጠየቀው ጥያቄ ሲመልሱ “ይሆናል ብለን እንገምታለን፤ አሁን በጅማሮ ላይ በመሆናችን መገመቱ ግን ያስቸግራል” ብለዋል፡፡



የያራ የማዳበሪያ ምርት ከአመራረቱ ጀምሮ ችግር ያለበት መሆኑ የተነገረ ሲሆን በተለይ አሰረጫጨቱ ላይ በገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ቁማር እንደሚስተዋልበት እየተነገረ ነው፡፡
‹‹ያራ ምርቱን በቀጥታ ለባለስልጣናት ይሸጣል፤ ይህም የማዳበሪያ ሽያጭ የባለስጣኖቹ የተቀናቃኞች የማንበርከኪያ ስልት ነው›› ያለው ሂውማን ራይትዎች በበኩሉ የገጠር አመራሮችን ጨምሮ የማዳበሪያ ስርጭት ዋነኛ የስርዓቱ የማንበርከኪያ መንገድ መሆኑን ገልፃል፡፡ አቶ መለስን የሸለመው ድርጅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ እየያዘ የመጣ ሲሆን የማዳበሪያ አቅርቦትን በሚመለከት የትኛውንም ጨረታ ማሸነፍ እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ በሌላ በኩል ድርጅቱ ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር እንዲህ አይነቱን የጥቅም ግንኙነት መኖሩን አስተባብሎ ሽልማቱም ከዚህ ጋር እንደማይያያዝ ገልጧል፡፡ ሽልማቱ በኮሚቴ ደረጃ የተሰጠ
መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
የኖርዌይ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ መንግስት የማዳበሪያ ንግድን ለፖለቲካዊ አጀንዳ እንደሚጠቀም የሚሰሙ መሆኑን ያመኑ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዩኒ በርግ በበኩላቸው ‹‹አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ጉዳዩን እንዲያጣሩ ቢንጠይቅም ስለጉዳዩ መረጃ አልደረሰንም ›› ብለዋል፡፡ ሽልማቱ ለአቶ መለስ ያለአግባብ የተሰጣቸው መሆኑ ከተረጋገጠ የተቀበሉትን ገንዘብ የሚመልሱና እውቅናውም የሚሰረዝ መሆኑን ለአጣሪ ቡድኑ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ በ1997 ዓ.ም ጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ የያራ ሽልማትን ሲቀበሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ የያራን ድርጊት ማጣጣላቸው አይዘነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment