ተሻለ መንግሥቱ
1.“ኤርትራ ከየት ወዴት” –
የኢትዮጵያዊው መለስ ዜናዊ መጽሐፍ ፡፡ ስለ‹እናት ሀገሩ› ኢትዮጵያ አንድም አንቀጽ አለመጻፉን ልብ ይሏል፡፡
1.“በእናንተ ወገብ ላይ ያለው ቁስል በእኔም ወገብ ላይ አለ፡፡”
2.መለስ ዜናዊ እነ ንጉሤ አስገልጠውን የመሰሉ ሆዳም አማሮችን አሥመራ ላይ አስጎንብሶ ሻዕቢያን ይቅርታ ባስጠየቀበት ዘመን በትግርኛ ተናግሮት ወዳማርኛ ከተመለሰው፡፡
3.“የአማራ ተረትና የሶማሌ በጀት ነው ያስቸገረን፡፡” መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የተናገረው፡፡
4.“ከእንግዲህ ኤርትራ አንድም ጥይት አትተኩስብንም፡፡ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር አንድም ጥይት አይጮህም፡፡” መለስ ዜናዊ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በፊት የተነበየው ግን ያልያዘለት ትንቢት፡፡
5.“ ከአሥር ዓመት በኋላ የኢትዮጵያን ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እንዲመገብ ማስቻል ነው፡፡” መለስ ዜናዊ ሥልጣን በያዘባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት አካባቢ ከጋዜጠኞች ለተጠየቀው የአሥር ዓመት ዕቅድ ጥያቄ የመለሰው መልስ፡፡
6.“ባድመ ለኢትዮጵያ ተፈርዳልናለች፡፡…” ሥዩም መስፍን በመስቀል አደባባይ ለተሰበሰበ ሕዝብ የተናገረው የውሸት ብሥራት፡፡
7.“ከእንግዲህ የገበሬው ችግር የርሃብ ችግር ሳይሆን የሚያመርተውን የተትረፈረፈ ምርት በርካሽ እንዳይጥለውና በገንዘብ መልክ የሚኖረው ገቢ እንዳያንስበት ነው፡፡” መለስ ዜናዊ ቀደም ባለ አንድ ወቅት የወሻከተው -
8.“ኢሕአዴግ ጦርነትን መዋጋት ብቻ ሳይሆን ጦርነት መሥራትንም ያውቅበታል፡፡…” የቀድሞው የሕወሓት አባል አቶ ስዬ አብርሃ የተናገረው
9.“ አማራን እንዳያንሠራራ አድርገን ወደታች አርቀን ቀብረነዋል፡፡…” ኤርትራዊው የ‹ኢትዮጵያ› የጦር ኤታ ማዦር ሹም ‹ጄኔራል› ሣሞራ የኑስ እንደውዳሤ ማርያም ዘወትር የሚደግመው ጸሎትና አማራ በታሰበው ቁጥር አቦሬ አፉን የሚያሟሽበት፡፡
10.“ኢትዮጵያ በታሪኳ አንድም ጦርነት አሸንፋ አታውቅም፡፡…” በአሁኑ ወቅት ከፖለቲካ መድረክ ድራሹ የጠፋው የቀድሞው በአሜሪካን ሀገር ታክሲ አሽከርካሪ ዳዊት ዮሐንስ በጌቶቹ እንትን ሲፎክር የተናገረው፡፡
11.“ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት የበለጠ ታሪክ የሌላት የቅርብ ዘመን የአፄ ምኒልክ ግኝት ናት፡፡…” የሕወሓት ማዕከላዊ አቋም፡፡
12.“ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም የዘመናት ብሶት የወለደው ጀግናው የኢሕአዲግ ሠራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የአዲስ አበባ ሬዲዮ ጣቢያ ለሕዝብ ጥቅም ሲል ተቆጣጥሮታል፡፡ (ከዚያን ጊዜ ጀምሮም) የአማራው ገዢ መደብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሥልጣን ተወግዷል፡፡ በምትኩም ለአፍሪካ ሀገራት አርአያ የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሠርቷል፡፡…” የወያኔ ኢሕአዴግ ወትዋች የዘወትር ዲስኩር፡፡
13.“እንኳዕ ካባሁም ተፈጢርና… እንኳን (ከወርቁ ሕዝብ) ከእናንተ ተፈጠርን፡፡ ..” የ‹ኢትዮጵያ›ው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቀደም ሲል የተናገረውና ሁልጊዜም የሚያምንበት የሕዝብ ግርድና አመሳሶ እዬለዬ የሚያበላልጥበት የሚሌኒየሙ ቆሻሻ ንግግር(ታሪክ በማይደበዝዝ የወርቅ ብዕር መዝግቦ የያዘለት)፡፡
14.“አንቀጽ 39ም ይሁን ሌሎች የሕገ መንግሥት አንቀጾች [ሕዝብ ጠላቸውም ወደዳቸውም ማለት ነው] የሚሠረዙት በኢሕአዲግ ከርሠ መቃብር ላይ እንጂ ኢሕአዲግ ሥልጣን ላይ እያለ አይታሰብም፡፡…” የወያኔ የማይዛነፍ አቋም፡፡
15.“መለስ የአምስትና የአሥር ብር ኖቶችን እንኳን ለይቶ የማያውቅ በገንዘብ ረገድ ምንም ዕውቀት የሌለው ድሃ ነው፡፡ …” የአቶ መለስ አባት አቶ ዜናዊ አስረስ በ1997ዓ.ም አካባቢ ለአንድ መጽሔት ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተገኘ፡፡
16.“ በነዚህ መደርደሪያዎች ካሉኝ መጻሕፍት ሌላ በባንክም ሆነ በቤት ምንም ተንቀሳቃሽ ሀብትና ተቀማጭ ገንዘብ የለኝም፡፡…” ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አንድ ወቅት ስለሀብቱ ሲጠየቅ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ፡፡
17.“እኛ የምንኖረው መንግሥት በሚከፍለን አነስተኛ ደመወዝ ወር እስከወር እንደምንም እያብቃቃን ነው እንጂ ሌላ ገቢ የለንም፡፡ (እንዲህ እየተቸገርን የምንኖረው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባለን ፍቅር እንጂ) የመለስ ጭንቅላት ገበያ ወጥቶ ቢሸጥ ከዚህ በተሻለ ጥሩ ኑሮ ልንኖር በተቻለን ነበር፡፡…” ቀዳማዊት እመቤት አዜብ ጎላ ከወሻከተችው የተወሰደ – (‹ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ይቀዳል›)
18.“ለኤርትራ ነጻነት ከኢሕአዴግ ይበልጥ የተዋጋ ማንም የለም፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት እንድትወጣና ነጻ ሀገር እንድትሆን ኢሕአዴግ የከፈለው የደምና የአጥንት መስዋዕትነት ማንም ሊያስበው ከሚችለው በላይ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን የኤርትራን ነጻነት የሚጋፋ የውጭም ሆነ የውስጥ ጠላት ቢነሳ የኢትዮጵያ ጦር እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም፤ ገብተን እንደለመድነው ድባቅ እንመታዋለን፡፡ በኤርትራ ነጻነት ቀልድ የለም፡፡…” ኤርትራዊው የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚያቦካውና የሚጋግረው አቶ ስበሃት ነጋ (ውስጥ አዋቂዎች ሴት አውልና ሠካራም ይሉታል) የተናገረው( በኢትዮሚዲያም ተዘግቧል – (http://anonymouse.org/cgi-bin/anon-www.cgi/http://www.ethiomedia.com/atop/mercenary_tplf_rule.html)
19.“ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ፋሲል የኔ ዓለም፣ ብርሃኑ ነጋ፣ ኦባንግ ኦ. ሜቶ፣ ሲሳይ አጌና፣ ኢትዮሚዲያ፣አቡጊዳ፣ዘሐበሻ፣ኢትዮላዮን፣ኢትዮጵያዛሬ፣ቋጠሮ፣ኢካድፍ፣አንድነት፣ግንቦት7፣ኢሣት፣አውራምባታይምስ፣ አዲስ ነገር፣ፍትህ፣ጽናት፣አፍሪካሆርን፣… በጠቅላላው ኢሕአዲግ የሚከተለው ዴሞክራሲያዊ መንገድ የማይጥማቸው ግለሰብ ኢትዮጵያውያንም ሆኑ የፖለቲካና የሚዲያ ተቋማት ሁሉ አሸባሪዎች ናቸው፤ እንደተባለው ሆኖ የማይገዛ ሕዝብና የሕዝብ ወገንም እንደዚሁ አሸባሪና በሀገር ክህደት ወንጀል መከሰስ ያለበት ጥፋተኛ ነው፡፡…” ከእውነተኛ የወያኔ/ኢሕአዴግ ተፈጥሯዊ ጠባይ ተቀምሞ የተበጀ የክፍለ ዘመኑ መሪር እውነት፡፡
20.“ኢትዮጵያ ከየትኛውም የዓለም ሀገር በተለዬና በበለጠ መልክ ኢኮኖሚዋ በዓመት በ11 በመቶ ፍጥነት እያደገ የምትገኝ ፌዴራላዊት ዴሞክራሲያዊት ሀገር ናት፡፡…” የአቶ መለስ ዜናዊ የዘወትር ልብ አውልቅ ንግግር፡፡(ሞኝ እንዴት ይረታል ቢሉ እምቢ ብሎ ይባላል)፡፡
21.“አቶ መለስ ዜናዊ መጠነኛ ዕረፍት ስለሚያስፈልጋቸው በግል ሀኪማቸው በተነገራቸው ምክር መሠረት ዕረፍት ላይ ናቸው፤ በጥቂት ቀናት ውስጥም ወደ መደበኛ ሥራቸው ይመለሳሉ፡፡…” አቶ በክት ማለቴ በረከት ስምዖን ሰሞኑን የተናገረው፡፡ (ለጊዜው በሃያ አንዱ የወያኔ የአገዛዝ ዓመታት ላቁም እንጂ እነሱ ያላሉትስ የለም፡፡)
(ለነገሩ አቶ መለስ ካልተመለሰ እሰዬው፣ ከተመለሰ ግን እምቢዬው … ይሄ ‹ለፍርድ ሳይቀርቡ በፈጣሪ እጅ ሄዱ› እየተባለ የሚሠራጨው የካንገት በላይ እዬዬና ቁጭት አያምረኝም – ወንዝ የማያሻግር ወይም ውኃ የማያነሣ ነገር ነው፤ ‹የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው› በሚለው ብሂላችን ነው መስማማት የሚኖርብን፡፡ ይህ ዓይነቱ መቆላጨት የሌለ ነገር ነውና ይታሰብበት፡፡ በሃያ አንድ ዓመት ውስጥ ያልነበረ ፍርድ አሁን ከየት ሊመጣ ሆነና ነው ይህ ዓይነቱ ሚዛን የማይደፋ አመክንዮ የሚስተጋባው? ይልቁንስ ብልጥ ልጅ የሰጡትን እየበላ እንደሚያለቅስ እግዜሩ የሰጠንን ሲሳይም በቅጡ በተጠቀምንበት፡፡ ሲዳሩ ማልቀስ ወግ የሚሆነው በሠርግ ወቅት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ሣሙኤል ፈረንጅ በእንግሊዝኛ የጻፍከውንና አቡጊዳ ላይ የተመለከትኩትን ይህን መሰሉን ጠጠት ‹አፉ በሉኝ› በልና ይልቅየስ አሁን ምን እናድርግ በሚለው ላይ ገምቢ አስተሳሰቦችን ማፍለቁ ላይ እንበርታ፤ ያ ነው ይበልጥ የሚጠቅመን፡፡ መለስን ከሥልጣን ለማስወገድ የሚጠይቀን ወጪ ካለፍርድ ከነወንጀሉ በፈጣሪ መሞቱ ከሚያደርስብን ጸጸት በእጅጉ የሚበልጥ መሆኑን ተገንዝበን መቀናጣቱን እንተው፡፡ ፈጣሪ ረድቶንም እኛ ሰው በሆንና ብዙ ሳይመሽና ዕድሉ ሳያመልጠን በጊዜ የሚበጀንን በጋራ በሠራን፡፡)
ለማንኛውም አሁን ለጊዜው ትዝ ያሉኝ የክፍለ ዘመናችን ድንቃ ድንቅ የባለ ሥልጣኖቻችንና የጎጠኛ ገዢ ፓርቲያችን ታሪካዊ ንግግሮች እነዚህ ናቸው፡፡ እባካችሁ የምትችሉ እንደነዚህ ያሉ አጫጭር ትውስታዎችን ለአግራሞታችን ያህል ባጭር ባጭሩ አጋሩን፡፡
“We fought for Eritrean independence from the colonial rule of Ethiopia. Even now, if Eritrea is attacked, EPRDF would jump into Eritrea, join the Eritrean people and engage the enemy.” – Sebhat Nega on Radio Woyane (May 28, 2007) source: ethiomedia.com, ibid

No comments:
Post a Comment