No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Wednesday 8 August 2012

እነሚሚ ስብሃቱ ጁነዲን ሳዶ እንዲታሰሩ ጠየቁ፤ የእስልምና አማኞችንም ተዛለፉ


(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል የአቶ መለስን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ እንዲሁም በሙስሊሞች ወቅታዊ የመብት ጥያቄ የተነሳ “ፈጣን ሎተሪ” ባለስልጣናት ቱግ ቱግ ማለት ጀምረዋል። ይህን ተከትሎ በኦሮሚያ ፕወዛው ቀጥሏል። ይህን ተከትሎ የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትና በአውስትራሊያ በኢትውዮጵውያን ተዋርደው የተመለሱት አቶ ጁነዲን ጉዳቸው ፈልቷል። ቀድሞው ንጹሃንን ሲያሳስሩ፤ አብረው ሲገርፉ የነበሩት እኚሁ ቱባ ባለስልጣን ሚስታቸው ከታሰረች በኋላ ጉዳዩ ከሙስሊሞች ወቅታዊ እንቅስቃሴ ጋር እየተያያዘባቸው ይገኛል። በአዲስ አበባ በአቶ በረከት ስሞዖን ከፍተኛ ባጀት ተመድቦላቸው የሚሰሩት እነሚሚ ስብሃቱ (ሳምባ) ጁነዲን ሳዶ እንዲታሰሩ በራድዮ እየጠየቁ ነው። ድሮ መንግስት ሊያስረው የፈለገውን በሪፖርተር ጋዜጣ በኩል ነበር መል ዕክቱን ቀድሞ የሚናገረው፤ አሁን ደግሞ በነሚሚ በኩል። በአይዞህ ባይ የሚሰሩት እነሚሚ አቶ ጁነዲንን ደፍረው እንዲህ እያስፈራሩ ባለበት በዚህ ወቅትም በ እስልምና ሃይማኖት ውስጥ ገብተው ያልሆኑ የተሳሳቱ መረጃዎችን በመስጠት ተዛልፈዋል። ጁነዲን ፓርላማው መስከረም ላይ ሲከፈት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ቃሊቲ እንደምናገኛቸው እርግጥ እየሆነ ነው። እዚህ እነሚሚ ተናገሩ ማለት ማን ተናገረ ማለት እንደሆነ እናንተው ገምቱት። በዛሚ ራድዮ አስር ግዜ እየሳሉ (አይታከሙም እንዴ?) ያቀረቡትን ዘገባ ያድምጡት።http://www.zehabesha.com/

No comments:

Post a Comment