No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Saturday 11 August 2012

የቤተመንግስት ዜናዎች


 በሙሉነህ ዮሃንስና የዲፕሎማቲክ ምንጮች የተቀናበረ (August 9, 2012)
 የመለስ ዜናዊ ቤተሰቦች ሃዘን ላይ መቀመጣቸው ታወቀ በፍርሃትና በጭንቀትም ተውጠዋል!
 የአዜብ እና የበረከት ጸብ እየተካረረ ሄዷል!
 ውጭ አገር የተመደቡ አምባሳደሮች በሙሉ ለአስቸኳይ ስብሰባ ወደአዲስ አበባ እንዲመለሱ ታዘዙ! አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስካሁን አልተመለሰም! የመለስ ዜናዊ ቤተሰቦች ሃዘን ላይ መቀመጣቸው ታወቀ በፍርሃትና በጭንቀትም ተውጠዋል! ከህዝብና ከሚዲያ ከተሰወረ 45 ቀናት ያሳለፈው የመለስ ዜናዊ መኖርና አለመኖር አሁንም በሰፊው አወዛጋቢ እንደሆነ ቢቀጥልም ከወደ ቤተመንግስት ጓዳ ያገኘናቸው የማያወላዱ መረጃዎች ግን የሰውየውን ህልፈት የሚያረጋግጡ ናቸው። ለዋቢነትም የመለስ ዜናዊ ሚስት እናት የሆኑት ቆንጂት ጎላ ጎሹ እና የመለስ እህት የሆነቸው ዘውዲ ዜናዊ እጅግ በከባድ ሃዘን ተውጠው መሰንበታቸውና ውስጥ ውስጡንም ቅርብ የሆኗቸው ሰዎች እያስተዛዘኗቸው መሆኑ ተረጋግጧል። እነዚሁ ግለሰቦች ስለመለስ ሁኔታ እንዲገለጽላቸው የመንግስት አካላትን ቢጠይቁም አርፋችሁ ተቀመጡ ተብለዋል። መለስንም በስልክም ሆነ በአካል አግኝተው አያውቁም። እኒህ ቤተሰቦች የመለስን በህይወት አለመኖር ተገንዝበው ሌት ተቀን በለቅሶ እያሳለፉ
መሆኑ ታውቋል። የቅርብ ሰዎቻቸውም እያሾለኩ እለቅሶውን እየደረሷቸው ይገኛሉ። የመለስን መሰወር በመደበቁ ባለቤቱ አዜብ መስፍንም እንዳለችበት የተረዱት ቤተሰቦቿ ሃዘናቸውን አክብዶታል ተብሏል። በአጠቃላይ ግን በቤተመንግስት አካባቢ ጭንቀት፤ ፍርሃት፤ አለመረጋጋትና መረበሽ እንደሰፈነበት መረጃውን ያካፈሉን የዛው ሰፈር ሰዎች ጨምረው ገልጸውልናል። የአዜብ መስፍን እና የበረከት ስምዖን ጸብ እየተካረረ ሄዷል! መነሻው ለጊዜው ያልታወቀው የአዜብ መስፍንና የበረከት ስምዖን ጸብ እየተካረረ መምጣቱን የተለያዮ ምንጮች እየገለጹ ነው። ጸባቸው አደባባይ የወጣው ግን ከመለስ ዜናዊ ህመም/ሞት በተያያዘ መሆኑ ታውቋል። አዜብ ምን እንደሆነ በግልጽ ያልታወቀ ትእዛዝ ለበረከት ስታዘው አንቺን እኮ የማውቅሽ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚስትነት ብቻ ነበር የሚል ምላሽ በመስጠቱ የተበሳጨችው አዜብ ይህው ትእዛዝ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲደርሰው ታደርጋለች። በዚህ ናላው የዞረው በረከት አኩርፎ ባህር ዳር መሽጎ ነበር። ለዛውም ነው የመለስን መታመም የምንግስት አፈቀላጤ የሆነው በረከት ይፋ ማድረግ ሲገባው ከባህር ዳር አልመለስም ብሎ ስለነበር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ሰሞን ለህዝብ በይፋ ለመጀመሪያ እንዲገልጽ ግድ የሆነበት። በተያያዘም አማራን እወክላለሁ በሚለው የብአዴን ታጣቂዎች ዘንድ ተወዳጅ ነው የሚባልለት ተፈራ ዋልዋ ከመለስ ጋር በነበረበት የረዥም ጊዜ ውዝግብ ምክንያት ከተገለለበት አመራር ቦታ እንዲመለስ ጥሪ ቀርቦለት እንዳልተቀበለው መገለጹ የባለስልጣናቱ የሃይል አሰላለፍ ጥድፊያ በይፋ እየታየ ነው። በረከትና ተፈራም በክፉ የሚተያዮ ሰዎች እንደሆኑ የብአዴን ውስጥ አዋቂዎች ይገልጻሉ። ውጭ አገር የተመደቡ አምባሰደሮች በሙሉ ለአስቸኳይ ስብሰባ ወደአዲስ አበባ እንዲመለሱ ታዘዙ! የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባስተላለፈው አስቸኳይ ትእዛዝ መሰረት ውጭ ሃገር ተመድበው የሚሲዮኖች ዋና ሃላፊዎች የሁኑት አምባሳደሮች በሙሉ ወደ አዲስ አበባ ባልታወቀ ጉዳይ እንዲመለሱ መታዘዛቸውን የተለያዮ የዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጠዋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስካሁን እንዳልተመለሰ ታውቋል። ብዛት ያላቸው ዲፕሎማቶች ደግሞ ከኢምባሲ እየጠፉ በውጭ ሃገራት ጥገኝነት እያመለከቱ መሆኑ ተረጋግጧል። የመንግስት አለመረጋጋት በግልጽ በሚታይበት በዚህ ወቅት አምባሳደሮቹ መጠራታቸው የሚጠበቅ ነው የሚሉት እኒህ የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠሩት ለብርቱ ጉዳይ በአካል መነጋገር ግድ ስለሚል መሆኑን ጨምረው አብራርተዋል። ይህ ጥሪ በስዮም መስፍን አመራር እየተካሄደ መሆኑ ግን በዲፕሎማቶች አካባቢ ግርታን ፈጥሯል። ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ታማኝ ምንጮችን ጠቅሳ እንደዘገበችው ስዮም መስፍን ከቻይና ተመልሶ መንግስት የመምራት ስራ ላይ እንደተጠመደ ተመልክቷል። ከላይ የጠቀስነው የሃይል አሰላለፍ ጥልፍልፎሽ ሽኩቻው አድጎ ወደ ሃይል መጠቀም ማደጉ አይቀሬ መሆኑን ብዙ ተንታኞች ይስማሙበታል። አስተያየት ወይም መረጃ ካለዎት ያካፍሉን muleur@yahoo.com

No comments:

Post a Comment