ትናንት በዩኒቨርስቲያችን ስለ ተደረገው የኢንተርኔት ፕሮክሲ ለውጥ (Intenet use proxy change) ለመረጃ ፍሰት information flow (በሙሁሩ ኣከባቢ) ቁጥጥርና ለፍርድቤት ማስረጃነት (ክስ ለመመስረት ወይ ለማሳሰር) እንዲያስችላቸው ታልሞ የተደረገ ስለመሆኑ ጠቁሜ ነበር።
የገዢው ፓርቲ ሙሁራን ደጋፊዎች (ወይ ሌሎች የሚመለከታቸው ኣካላት) ኣስተያዬቴን ተችተዋል። ሙሁራኑ ያቀረቡት ምክንያት (እኔ የኮምፒተር ወይ ሳይበር እውቀት እንደሚያንሰኝ ጠቁመው) ይሄንን በመቐለ ዩኒቨርስቲ የተደረገው ኢንተርኔት ለመጠቀም በፓስዎርድ (password) subscribe ማድረግ ‘በመላው ዓለም’ (በተለይ በምዕራባውያን) ዩኒቨርስቲዎች የተለመደ ኣሰራር መሆኑና እኔ ግን መረጃ እንደሌለኝ ገልፀውልኛል።
ኣንደኛ
ጉዳዩን ሳነሳ ፕሮክሲውን ለምን መቀየር እንዳስፈለገ (ለምን ሊቀይሩት እንደወሰኑ) መረጃው ስለደረሰኝ እንጂ መቀየራቸው ጥርጣሬ ውስጥ ከቶኝ ወይም የሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ልምድ ስለማላውቅ ኣይደለም። ስለዚ ፕሮክሲው የተቀየረው በምክንያት ነው። ለዚህም ነው የተቃወምኩት። የምቃወመው በፓስዎርድ ወይ በስማችን መጠቀማችን ሳይሆን ከኋላ ያለው ምክንያት (intention) ነው።
ሁለተኛ
በሌላ ሀገሮች ወይ የውጭ ዩኒቨርስቲዎች ኢንተርኔት ለመጠቀም subscribe ማድረግ የሚጠበቅባቸው በዩኒቨርስቲው ያለ resource እንደፈለጉ መጠቀም እንዲችሉ ተብሎ ነው። የዩኒቨርስቲውን ሃብት (resource) መጠቀም ለነሱ ብቻ የተሰጠ privilege በመሆኑ ነው። ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ውጭ በነፃ ስለማይሰጥ እንጂ እነሱን ለመሰለል ታስቦ ኣይደለም።
ሦስተኛ
በሌሎች ሀገሮች ዩኒቨርስቲዎች ስታፍ ኣባላት የprivacy መብታቸው የተጠበቀ ነው። መረጃ የማግኘት ሰብኣዊ መብትም ኣላቸው። በነዚህ ሀገሮች የዜጎች ፕራይቬሲ በሚጥስ መልኩ የሚደረግ ማንኛውም የመረጃ ፍሰት ቁጥጥር ሕገወጥ ነው። ለምሳሌ በምዕራባውን የሰለማዊ ሰዎች ስልክ መጥለፍ (phone hacking) ወንጀል ነው። በኢትዮዽያ ግን ሕጋዊ በሚመስል መልኩ የደህንነት ሰዎች የፈለጉትን ያደርጋሉ (ለፍርድቤት ክስ በማስረጃነትም ያቀርቡታል)።
ኣራተኛ
በሌሎች ሀገሮች የተለያዩ የግል ድርጅቶች የኢንተርኔት ኣገልግሎት የመስጠት ፍቃድ ኣላቸው (ይሰጣሉም)። እነዚህ ድርጅቶች ታድያ የግለሰዎች ፕራይቬሲ የመጠበቅ ግዴታ ኣለባቸው። (ካልሆነ ግን በነፃና ገለልተኛ ፍርድቤት ሊቀጡ ይችላሉ)። በነዚህ ሀገሮች የኢንተርኔቱ ሰርቨር (server) ተቆጣጣሪዎች ባለሙያ ሰራተኞች እንጂ የገዢው ፓርቲ የደህንነት ካድሬዎች ኣይደሉም።
በኢትዮዽያ አንድ ኢንተርኔት ሰጪ ድርጅት (EthioTelecom) ብቻ ነው ያለው። እሱም በመንግስት ቁጥጥር ስር ነው። መንግስትና ገዢ ፓርቲ በተቀላቀሉበት ሀገር የinternet communication የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ይቆጣጠሩታል፤ የኢንተርኔት የመረጃ ፍሰትም ያሰናክላሉ፣ እንደዉጤቱም የሰዎች የፕራይቬሲ መብት ይጣሳል። ይሄን ሁሉ የሚደረገው በ’ደህንነት’ ስም ነው። ግን ይሄን ሁሉ የሚደረገው የማን ደህንነት ለመጠበቅ ነው? የገዢው ፓርቲ ብቻ? ምክንያቱም ከገዢው ፓርቲ ኣልፎ የዜጎች ወይ የሀገር ደህንነት ከሆነ ሁሉንም ይመለከታል። እኛም ለሀገራችን ደህንነት የበኩላችን እንወጣለን።
ባጭሩ የኢትዮዽያና የሌሎች ሀገሮች የኢንተርኔት ኣጠቃቀም ስርዓት ማመሳሰል ተገቢ ኣይደለም። የመቐለ ዩኒቨርስቲ ሁኔታም በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የኣሰራር ልምድ justify ማድረግ ኣይቻልም፣ ዓላማውና contexቱ የተለያየ ነውና።
It is so!!
No comments:
Post a Comment