No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday, 8 April 2013

መሬት ነጠቃ ለአሜሪካ ም/ቤት ሊቀርብ ነው


በመጪው ሰኞ ሚያዚያ7፤2005ዓም (April 15፣ 2013) በአፍሪካ ስለሚደረገው የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ የአሜሪካ ም/ቤት የፖሊሲ አውጪዎችና በጉዳዩ ላይ የሚሟገቱ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችን እንዲሁም ባለሙያዎችን ሃሳብ ለማዳመጥ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ፡፡
በአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት በአፍሪካ፣ በዓለምአቀፍ ጤና፣ በዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ንዑስኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ክሪስ ስሚዝ ከፍተኛ አማካሪና የአፍሪካ ኤክስፐርት የሆኑት ግሬጎሪ ሲምፐኪንስ ስብሰባውን እንደሚመሩትም ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡
በአፍሪካ የሚካሄደውን የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ በተጠራው ስብሰባ ላይ መግለጫ ከሚሰጡት አፍሪካውያን መካከል ጋናዊው ምሁር ዶ/ር ጆርጅ አዪቴ የሚገኙበት ሲሆን ከኢትዮጵያ ብቸኛው ተጠቃሽ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ናቸው፡፡ ከኦክላንድ ተቋም ጋር በመሆን አቶ ኦባንግ የሚመሩት የጋራ ንቅናቄ በቅርቡ በአማርኛ ተተርጉሞ ይፋ የሚሆነውን ጥናታዊ ዘገባ ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ በመሬት ነጠቃ ላይ የተዘጋጀውን ዘገባ የጠቀሰው የስብሰባው መጥሪያ በጉዳዩ ላይ አኢጋን ያከናወነውን የምርመራ ሪፖርት ጠቅሷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የሥራ ጉዳዮች ላይ በመጠመድ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ የሚገኙትን አቶ ኦባንግን ጎልጉል በስልክ ባነጋገረበት ወቅት እንደተናገሩት ድርጅታቸው መነሻውንና መድረሻውን እንዲሁም የሚያከናውነውን ተግባራት በዕቅድ የሚፈጽም መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የጋራ ንቅናቄው ለዚህ ዕውቅናና ስብሰባ መጠራቱ በራሱ ታላቅ ድል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የሰላማዊ ትግል ከወረቀት የማያልፍና የአቤቱታ ማስፈረም (የፔቲሽን) ትግል ብቻ እንዳልሆነበቅርቡ ሕንድ በመሄድ በዚሁ የመሬት ነጠቃ ጉዳይ ላይ ያደረጉት ስብሰባና ውይይት በኢንቨስትመንት ስም በኢትዮጵያ መሬት እየዘረፉ ላሉት ኩባንያዎች ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረባቸው እንደማስረጃ ጠቅሰዋል፡፡
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ካለበት ድርጅታዊና አገራዊ ግዴታ አኳያ የአሜሪካ ምክርቤት ሕግ አውጪ አካላትን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ እያሳወቀና እየወተወተ መሆኑን የተናገሩት አቶ ኦባንግ፤ በተለይ በቅርቡ የሚካሄደውን ምርጫ፣ የፖለቲካ እስረኞችን ሁኔታ፣ ከየቦታው እየተፈናቀሉ ያሉትን ዜጎች፣ አፋኝ የሆኑትን የመያድና የጸረ-ሽብርተኝነት ሕጎችን እንዲሁም የመንደር ምስረታንና አስገድዶ ማስፈርን በተመለከተ በርካታ ጉዳዮች በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራበት እንደሆነ በተለይ ለጎልጉል ገልጸዋል፡፡ በመጪው ሰኞ በሚደረገው ስብሰባ የሚገኘውን ውጤት ካሁኑ በግልጽ ለመናገር ባይቻልም ስብሰባው ከላይ ከተጠቀሱት ጉዳዮች አንዱ እንደመሆኑ ወደፊት በምክርቤት ለሚደረጉ ውሳኔዎች እንደ ግብዓት እንደሚያገለግል አስታውቀዋል፡፡  
በአፍሪካ እየተካሄደ ስላለው የመሬት ነጠቃ 11የአፍሪካ አገራትን የሚወክሉ 11 ድርጅቶች ኅብረት በመፍጠር ተጽዕኖ ከማድረግ እስከ ፖሊሲ ማስቀየር ሥራ እየሠሩ መሆናቸውና ከእነዚህም ድርጅቶች መካከል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የሰኞው ስብሰባ መርሃግብር ይህንን ይመስላል፡፡
THE LAND-GRAB ISSUE IN AFRICA
A Discussion with Advocates & Policymakers
Monday, April 15 at 2:00PM
U.S. CONGRESS: Rayburn House Office Building
(45 Independence Avenue SW, Washington, DC)
 A SHORT DOCUMENTARY ON LAND GRABBING WILL BE SCREENED
Land grabbing is becoming the single most combative issue in Africa. It involves large-scale land acquisitions by foreign countries and corporations for farming, biofuels, logging and minerals. Unlike land acquisitions in the United States and Europe where purchasers pay the fair market values for land, in Africa unscrupulous deals are displacing thousands of farmers and leaving local communities in abject poverty, while government officials benefit from land sales and leases.
PANALISTS
 BINTA TERRIER
Ms. Terrier is Co-Founder and Executive Director of Partnership League for Africa’s Development (PLAD). PLAD was created to focus on education, health, land-rights and agriculture as the cornerstone to address the human rights problem in Africa. Educated as an economist she is becoming a leading female voice for Africa’s development and governance.
DR. GEORGE AYITTEY
Dr. Ayittey is a distinguished Economist and Professor at the American University, Washington, DC. He is the founder and chair of the Free Africa Foundation and an associate scholar at the Foreign Policy Research Institute. Dr. Ayittey has championed the argument that: Africa is poor because she is not free, that the primary cause of African poverty is less a result of the oppression and mismanagement by colonial powers, but rather a result of modern oppressive native autocrats.
OBANG METHO
Mr. Metho is Executive Director of the SMNE (www.solidaritymovement.org), a social justice movement of diverse Ethiopians that joint-sponsored with the think tank, Oakland Institute, to produce the Ethiopian portion of the comprehensive investigative report, Understanding Land Investment Deals in Africa, published in June 2011. Mr. Obang is a human rights activist who tirelessly advocates for human rights, justice, freedom and environment, enhanced accountability in politics and peace in Africa for over 10 years.
RICK JACOBSON
Mr. Jacobson works on land grab issues in Africa as a Team Leader for International Forest Policy and Environmental Governance for Global Witness.
MODERATOR: GREGORY SIMPKINS
Mr. Simpkins is an Africa Expert and Senior Advisor, to Congressman Chris Smith the Chairman of the U.S. House Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and International Organizations.
Questions: please contact: Binta@allafr.org 301-802-2233 orkwame@rebeccaproject.org 202-406-0911ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡


No comments:

Post a Comment