No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Sunday 7 April 2013

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴአባላት በሃሰን ታጁ ድርጊት እጅግ አዝነዋል::


በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግፍ ታስረው የሚገኙት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በኡስታዝ ሀሰን ታጁ የቀረበውን የመፍትሔ ሀሳብ ሳይቀበሉት እንደቀሩ ምንጮች አስታወቁ፡፡ ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ህዝበ ሙስሊሙ የጀመረውን ሰላማዊ ተቃውሞ አሁን ባለበት ሁኔታ መቀጠሉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እንዲሁም ኮሚቴዎቻችንንም ከመንግስት ጋር በማስታረቅ በይቅርታ እንዲፈቱ ለማድረግ ትግሉ መቆም ይኖርበታል የሚል ሃሳብ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግፍ ታስረው ለሚገኙት
ኮሚቴዎቻችን አቅርበው የነበረ ሲሆን ኮሚቴዎቻችን በጉዳዩ ላይ ከተወያዩ ቡሃላ በቀረበው የመፍትሄ ሃሰብ ላይ ሊስማሙ እንደማይችሉ መግለፃቸው ተሰምቷል፡፡ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ይህን የመፍትሄ ሃሳባቸውን የሚያትት ፅሁፍ ያዘጋጁ ሲሆን ይህም ፅሁፍ የመጀመሪያው በየካቲት ወር ቀጥሎም የተለያዩ
ማሻሻያዎች እና ጭማሪዎች ተደርጎለት በስተመጨረሻም አሁን በምንገኝበት በመጋቢት ወር በመንታ መንገድ ላይ ነን የቱን አቅጣጫ እንከተል የሚል 33 ገፆችን የያዘ የመጨረሻ ፅሁፍ ለውይይት አቅርበዋል፡፡ ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ህዝበ ሙስሊሙ እያደረገ ያለው ሰላማዊ ተቃውሞ ከዚህ በላይ መቀጠሉ ላልተፈለገ እልቂት ሊዳርግ ይችላል በሚል እሳቤ እና የተለያዩ መሬት ላይ ያልወረዱ ስጋቶችን በመጥቀስ በመላ ሀገሪቱ እየተቀጣጠለ የመጣውን የመብት ማስከበር ትግል


ከወዲሁ መቆም እንዳለበት በፅሁፋቸው አስፍረዋል፡፡ በዚህ ፁሁፍ ላይ ህዝበ ሙስሊሙ ባደረገው ትግል ውስጥ የተገኙ ድሎች ያሏቸውን የዘረዘሩ ሲሆን በነዚህም መካከል ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳቸው 3 መሰረታዊ ጥያቁዎችም ከሞላ ጎደል እንደተመለሱ ተቆጥረው ሙስሊሙ ካገኘው ድሎች ውስጥ ዘርዝረው
አስቀምጠዋቸዋል፡፡እንደሚከተለው በፅሁፋቸው
አስፍረውታል፡-

1. አህባሽን በሐይል የመጫንን ሂደት ማስቀረት፡- አህባሽ የተሰኘውን አስተሳሰብ በሀይል ለመጫን የተደረገው ሙከራ አግባብ ያለመሆኑን ማስገንዘብ ችሏል፡፡ ዳግም እንዲህ ዒይነቱ ፀረ-ሕገ መንግስታዊ አካሄድ እንዳይታሰብ ትምህርት ሰጥቶ አሌፎል፡፡ ይህን ድል አሳንሶ በማየት በተቃውሞው ምንም የተገኘ ነገር እንደሌለ አድርጎ ማሰብ ትልቅ ስህተት
ይመስለኛል፡፡

2. የመጅሊስን የምርጫ ባህል ማስጀመር፡- የመጅሊስ ምርጫ መጀመሩ በራሱ እንደ ትልቅ ድል ይቆጠራል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከውጤቱ ይልቅ ሂደቱን የምናስበልጥበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ ማንም ይመረጥ ማን ከእንግዱህ ‹‹የእድሜ ሌክ መጅሊስ›› አይኖረንም፡፡

3. የአወሊያ ት/ቤትን ጉዲይ ፈር ማስያዝ፡- ‹‹አወሊያ የአህባሽ ማሰልጠኛ ሉደረግ ነው›› የሚለው ስጋት ሙሉ በሙሉ ሊወገድ ችሏል፡፡ የተባረሩ መምህራን፣ ሠራተኞችና የመስጊድ ኢማምች ተመልሰዋል፡፡ በመምሁራን ቦርድ የሚመራበት ሁኔታም በመመቻቸት ላይ ይገኛል፡፡ በማለት ሃሳባቸውን በፅሁፍ አስፍረዋል፡፡

ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ትግሉ መቀጠል አለበት የሚለውን የመላ ሀገሪቱን የህዝበ ሙስሊሙን(ኮሚቴዎቻችንንም ጨምሮ) አቋም እና ትግሉ መቆም አለበት የሚሉ ወገኖችን(ይህን አቋም መንግስት ከበፊትም ጀምሮ እያራመደው ይገኛል) ሃሳብ በፁሁፋቸው ለማካተት ሞክረዋል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ባደረገው እንቅስቃሴ ወንድሞች(ህጋዊ ወኪሎቻችንን ወይም ኮሚቴዎቻችንን ለማለት ነው) እስኪታሰሩ ድረስ ትርፋማ የነበረ ሲሆን ወንድሞች ከታሰሩ ቡሃላ ግን እንደቀነሰና ብሎም እያሽቆለቆለ እንደሚገኝ ግላዊ ሃሳባቸውን ሰተዋል፡፡ ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ህዝበ ሙስሊሙ በመላው ሃገሪቱ ባሁኑ ሰአት በየሳምንቱ እያካሄደ የሚገኘው ተቃውሞ መቀጠል አለበት ብሎ ህዝቡ ያመነበትን ምክንያቶች አንድ ወጥ አለመሆኑን ለማሳየት የዘረዘሩ ሲሆን እንደሚከተለው አቅርበውታል፡፡

1. መንግስት ለጥያቄዎቻችን መልስ አልሰጠም፣
2. ወንድሞቻችን ታስረው ዝም አንልም፡
3. መንግሥት ለመጣል
4. ሙቀቱ ደስ ይላል
5. መንግሥትን ማናደድ
6. መንግሥት እንዳያጠቃን ተቃውሞው ተገን ሆኖናል
7. የመጣው ይምጣ፡ የሚሉ ምክንያቶችን ይዞ እንደሆነ
በዝርዝር አስቀምጠዋል፡፡

በስተመጨረሻም ኡስታዝ ሀሰን ታጁ ህዝበ ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበር እያካሄደ የሚገኘውን ተቃውሞ ማቆም እንዳለበት ካስቀመጡ ቡሃላ ህዝቡ በቀጣይነት ሊከተለው የሚገባውን የመፍትሄ ሃሳቦቹም እንደሚከተለው አቅርበውታል፡-

1.የዲን ትምህርት መማር፡
2.ራስን ማስተካከሌና መግራት፡
3. ቤተሰብን መግራትና መምራት፡
4. ማህበረሰብን ማገሌገሌ፡
5.በደኒያዊ ሥራዎቻችን ውጤት ማስመዝገብ፡
6.የአንዴነት ስሜትን ማጠናከር፡ የሚሉ የመፍትሄ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን የመፍትሄ ሃሳቦች ለኮሚቴዎችቸን ከቀረበ ቡሃላ መንግስት በሙስሊሙ ላይ እያደረሰ ለሚገኘው በደል እና ግፍ ምላሽ ባይሰጥም ኮሚቴዎችችን ከተመለከቱት ቡሃላ የመፍትሄ ሃሳቡን ፈፅሞ እንደማይቀበሉት እና ስምምምነት ላይ መድረስ እንዳልቻሉ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም በቀረበው የመፍትሔ ሃሳብም እጅግ ማዘናቸውን
ከፊታቸው ይነበብ እንደነበር ምንጮቻችንጨምረው ገልፀዋል፡ Abu Dawd Osman

No comments:

Post a Comment