No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday 8 April 2013

ድምፃችን ይሰማ አህባሽ በዞረበት ነውጥ አይጠፋም!

ክፍል አንድ

አህባሽ የተባለው ሊባኖስ አፈራሽ አንጃ ከመንግስት በሚደረግለት ድጋፍ የኢትዮጵያ ሙሰሊሞችን ህይወት መበጥበጥ ከጀመረ ከአመት በላይ አልፏል። እስካሁንም ህዝቡ የሰላም አየር መተንፈስ አልቻለም። ይህ ነውጠኛ ሀይማኖት ቅብ አንጃ የሰላማዊ ሙስሊሞችን ህይወት ሲበጠብጥ የሚታየው በአገራችን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት መሆኑ ደግሞ ይበልጥ የቡድኑን ባህሪ ግልጽ አድርጎ ያሳየናል። ለዛሬ የአህባሽ አንጃ ተከታዮች በሌሎች አገራት ከፈጸሟቸው የረብሻ ተግባሮች ጥቂቶቹን ለማስታወስ ያክል ከቀላል ወደከባድ በሚሄድ ቅደም ተከተል ለማንሳት እንወዳለን። አብረን እንያቸው።
ቤት ሰበራና ድብደባ በምድረ አሜሪካ

አሶሲየትድ ፕሬስ በማርች 25 – 1997 እንደዘገበው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በዚያው አመት ማርች 22 በአሜሪካ ቦስተን ማሳቹሴትስ፣ ቼልሲ በተባለው ቦታ በሚገኙት የአድሚራል ሂል ኮንዶሚኒየም ህንጻዎች የሊባኖሱ አህባሽ ድርጅት (AICP) አባላት የሆኑና በካናዳና አሜሪካ የተለያዩ 5 ከተሞች የሚኖሩ ዘጠኝ አህባሾች አህመድ አል አረብ የተባሉትን ግለሰብ ቤት ሰብረው ይገባሉ። ግለሰቡ የማሳቹሴትስ ኢስላማዊ ማህበር ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ከአህባሾቹ ድርጅት ጋር ኤቨሬት በተባለው ክልል በሚገኝ መስጊድ ግንባታ የተነሳ ጸብ የነበራቸው ናቸው።



ዘጠኙ አህባሾች የእኒህን ግለሰብ ቤት ሰብረው በመግባት ፕሬዝዳንቱን እና አል አረብ የተሰኘ ባልደረባቸውን በሽጉጥ ሰደፍ ክፉኛ ይደበድቧቸዋል። የተደብዳቢው ባለቤት ፖሊስ በመጥራቷ ግን እዚያው ተይዘው ክስ ይመሰረትባቸዋል። መጀመሪያ ላይ ዳኛው ተከሳሶቹ ብዙ ግንኙነት ያላቸው በመሆናቸው እያንዳንዳቸው 750 ሺ ዶላር ካላስያዙ የዋስ መብት አላከብርም ብለውም ነበር።


ከብዙ ቆይታ በኋላ በኖቬምበር 23 - 1998 ዳኛው የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጡ በኋላ ወንጀሉን አቀናብሯል በተባለው ሪያድ ናቺፍ የተባለው አህባሽ ግለሰብ ላይ የአንድ አመት ከሶስት ወር እስራት የፈረዱበት ሲሆን ከእስሩ መጠናቀቅ በኋላም ለሶስት አመታት ያክል በአመክሮ እንዲቆይ ወስነውበታል።


ይህ ክስተት በወቅቱ ብዙዎችን ያስደነገጠ የነበረ መሆኑን የሚያሳዩ የዜና ዘገባዎች በርካታ ናቸው። ሙስሊሞች በነውጠኝነት እንዲሳሉ እና እንዲጠረጠሩም አስተዋጽኦ አድርጎ ነበር። ‹‹ዘጠኙ አህባሾች ድርጊቱን የፈጸሙት ሊባኖስ የሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ፕሬዝዳንት በሰጡት ውስጣዊ ትእዛዝ ነበር›› የሚል ወሬ አፈትልኮ መውጣቱ ደግሞ ነገሩን የበለጠ አወሳስቦት ነበር። መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ያለና ራሱን ‹‹የእርዳታ ድርጅት›› እያለ የሚጠራ ቡድን በቀጭን ትእዛዝ ባህር ተሻጋሪ ወንጀል ማስፈጸም መምረጡና ደብዳቢዎቹም በተለያዩ አገራት የሚኖሩ የአህባሽ ድርጅት አባላት መሆናቸው በወቅቱ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።


ላውንቸር ጥቅም ላይ የዋለበት የግሩፕ ጸብ


ኦገስት 24 – 2006 ቤሩት ውስጥ የሚገኘው ቡርጅ አቢ ሀይደር ድንገተኛና ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ አስተናግዶ ነበር። የዚህ ተኩስ ልውውጥ ዋነኛ ተዋናዮች ደግሞ የሊባኖሱ አህባሽ ድርጅት (AICP) አባላት ነበሩ። እኒህ የአህባሽ አባላት በተጠቀሰው ቦታ ላይ ከሂዝቦላ አባላት ጋር በመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ምክንያት በመጋጨታቸው ሰአታት የፈጀ የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ አድርገዋል። በዚሁ ግጭት ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱም በተለያዩ የዜና አውታሮች ተዘግቦ ነበር።

በ 2006 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት በሪሶሊውሽን ቁጥር 1701 ትግበራ ዙሪያ ያወጣው ሪፖርት በ36ኛ ተራ ቁጥር ግጭቱን በአጭሩ ሲያሰፍረው እንዲህ በሚል ነበር፡-

‹‹በኦገስት 24 በሂዝቦላ እና AICP በተባለው የተቃዋሚዎች ፖለቲካዊ አጋር (የአህባሽ አንጃ አለም አቀፍ ድርጅት) ደጋፊዎች መካከል ቤሩት ውስጥ ቡርጅ አቢ ሀይደር በተባለ ቦታ ላይ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። በዚሁ ግጭት አንድን የሂዝቦላ ከፍተኛ አመራር ጨምሮ የሶስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ግጭቱ ወደአጎራባች አካባቢዎች ተስፋፍቶ ለበርካታ ሰአታት ቆይቷል። በግጭቱ ላይ ማሽንገን እና ላውንቸርን የመሳሰሉ ከባድ መሳሪያዎች ጥቅም ላይ የዋሉ መሆናቸው በሊባኖስ ተስፋፍቶ የቆየው ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር ለአገሪቱ ጸጥታና መረጋጋት ምን ያክል አስጊ እንደሆነ ያስታወሰ ነበር።››


የመኪና ማቆሚያን በመሰለ እዚህ ግባ የማይባል ምክንያት ከተማውን ያመሰ እና የሰው ህይወትና ንብረት ላይ ውድመት ያደረሰ ግጭት ላይ አንድ ‹‹ኢስላማዊ ነኝ›› የሚል ድርጅት መሳተፉ በራሱ አስገራሚ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ለግጭቱ ላውንቸርና መትረየስ መጠቀማቸው የቡድኑን አላማ ግልጽ አድርጎ ማሳየት የሚችል እውነታ ነው። የጸቡን ድንገተኝነት ስናስታውስ ደግሞ እኒህ ሰዎች በሰላም ጊዜ እንኳን እስካፍንጫቸው ታጥቀው የመዞራቸውን እውነታ ያሳብቃል። ሰላም በሰፈነበት ከተማ ለሚፈጠር ድንገተኛ ጸብ ላውንቸርና መትረየስ ጥቅም ላይ ዋለ ማለት ቀድሞውንም ታጥቀውት ወይም በመኪናቸው አስቀምጠውት ነበር የሚዞሩት ማለት አይደለምን? አሁንም የቀጠለው የአህባሽ ማስረጫ መርሀ ግብር እና ለዚሁ ተግባር የሚፈሰው ገንዘብ ለአገራችን ምን ይዞ እንደመጣ እያየነው ነው፡፡ ነገንም ለከፋ ሁኔታ እያዘጋጁት ነው፡፡


ለጽሁፉ ግብአትነት የዋሉ ማስረጃዎች ይያያዛሉ


ይቀጥላል

No comments:

Post a Comment