No one is born hating another person because of the colour of his sikn, or his background or his religion.
People must learn to hate, and if they can learn to hate, they can
be tought to love, for love comes more naturally to the human heart than its opposite. Nelson Mandela.

Monday 15 April 2013

ይህጉዳያችን ካልሆነ ምን ጉዳያችን ሊሆን ይችላል? Gudayachn blog


ኢትዮጵያ መሬት ባከራየቻቸውም ሆነ ከሸጠችላቸው ኩባንያዎች ሃገራት ጋር ክርክር ቢነሳ ጉዳዩ የሚታየው በአለም አቀፍ ገላጋይ ፍርድቤት ነው

ኢጣልያ በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል በኤርትራ ለመጀመርያ ጊዜ ቦታ ማግኘት የጀመረችው በ አሰብ ግዛት ሩባርቲኖ በተባለ የመርከብ ኩባንያ አማካይነት ከአንድ ሱልጣን በ1869 ዓም በገዛችው ትንሽ መሬት መሆኑ ይታወቃል። እንግዲህ ሃገራችንን ከ አንድ መቶ አመታት በላይ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ የቀጠለ ፖለቲካዊም ሆነ ምጣኔ ሃብታዊ ችግር እየፈጠረ መሆኑ ይታወቃል።
አፕሪል 14/2013 ዓም በኢሳት ቴሌቭዥን በቀረበው ”የእሁድ ወግ” የውይይት መርሃግብር ላይ አቶ ዳንኤል ጥላሁን በካናዳ ቶሮንቶ የህግ ባለሙያ ስለ መሬት ለውጭ ባለ ሃብቶች መሸጡ ጉዳይ ያነሱት ሃሳብ ሚዛን የሚደፋ እና ብዙ ኢትዮጵያዊ የሚያውቀው አይመስለኝም። ቀድሞ ስለመሬት ማከራየት ሳስብ ስጋት ይሆናል ብዬ የማስበው ወደፊት መሬት በኪራይ
ወሳጅ ሃገራት ከኢትዮጵያ ጋር የጸብ ማንሻ ምክንያት ቢሆናቸውስ? የሚል ነበር። ይህንን ስጋቴን ግን በማስረጃ ለማስደገፍ አለመግባባቱ እስኪፈጠር መጠበቅ አለብኝ ማለት ነው? ብዬ ያሰብኩበት ጊዜ ነበር።ዛሬ አቶ ዳን ኤል ይህንን ስጋት አጠናክረውልኛል።
የዛሬው የመሬት ኪራይም ሆነ ሽያጭ ነገ ከገዢውም ሆነ ከተከራዩ ሃገር ጋር እስከወታደራዊ ግጭት ድረስ የማድረስ እድል እንዳላቸው የሚያመላክት ሁኔታ መኖሩን ለመረዳት አቶ ዳንኤል በኢትዮጵያ እና በተከራይ የውጭ ኩባንያዎች መካከል የተደረጉትን ውሎች ባህሪ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል።
የኢንቨስትመንት ኮንትራቶች ሲፈረሙ የኢንቨስትመንቱን መብቶች የሚያስጠብቁ ብዙ ነገሮችአሉ።ባይላተራል ኢንቨስትመንት ፕሮተክሽን ትሪቲስ”  መንግስት  ከህንድ ከቻይና ከግብጽ ጋር ሁሉተፈራርሟል።በሌላ በኩል  1966ቱን  ዋሽግተኑን ”ስቴት ኢንቨስተር ዲስፕዩት” ይህ መንግስትተፈራርሟል። እነኚህ ውሎች ምን ያመጣሉእነኚህ ሁሉ ነገሮች ሲደመሩ ስትል መሬታችንንበኮንትራት እየገዙ ያሉ ሰዎች መሬቱን ይይዙና የሚዳኙት ግን  አለም አቀፍ ህግ ነው።በ አለምአቀፍ የግልግል ፍርድቤት ነው የሚዳኙት ከመንግስት ጋር ሙግት ቢገጥሙ በመሬቱ ዙርያ ማለትነው።ይህንን ለማጠናከር ደግሞ ምን ታውጆላቸውል? ”ፕሮክላሜሽን ሰርቲ ሰቨንየሚባል 1996 አዋጅ ታውጆላቸዋል።ይህ ህግ ደግሞ ህዝቡን እያፈናቀሉ መሬቱን ከገዙ ባለሃብቶች ጋር ክርክር ቢነሳጉዳዩ  አለም አቀፍ የግልግል ፍርድቤት እንዲታይ መንግስት ህግ አውጥቶላቸዋል።ይህ ሌላ አስገዳጅህግ ያግዘዋል  1958 ”ኒዎርክ ኮንቨንሽንን” ፈርሟል።እነኚህን ነገሮች ዘርዝረህ ስትመለከታቸው አንድኢትዮጵያዊ ገበሬ በማንኛውም ጊዜ ሊነቀል የሚችል ነው።ምንም አይነት መብት የለውም።መሬታችንንየሚገዛው ባዕድ ግን ከእኛ በላይ መብት አለው።ይህንን መብቱን  አለም አቀፍ ደረጃ ማስከበርየሚችል ነው።እየሆነ ያለው ነገር ዜግነታችንን ተቀምተናል።ከመቀሌ እስከ ሞያሌ ዜግነታችንተገፏል።መሬት ላራሹ ተገቶ የቻይና ፊውዳሊዝም እየሰፈነ እኮ ነው።”ብለዋል።
የአሰብ የቁራሽ መሬት ሽያጭ መዘዝ እስከ አሁን ድረስ የሃገራችን ችግር አንዱ ምንጭ እንደሆነ እንደቀጠለ ሁሉ የዛሬው የመንግስት የመሬት ኪራይ እና ሽያጭ ጉዳይ ካሁኑ እልባት ካላገኘ ብዙ ችግር ማስከተሉ እንደማይቀር አመላካች ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተደቀነ አደጋ ነው።። ይህ ጉዳያችን ካልሆነ ምን ጉዳያችን ሊሆን ይችላል?
አበቃሁ
ጌታቸው, ኦስሎ

No comments:

Post a Comment